በክፍል
ሁለት ትዝታችን ነቢዩ ዳንኤልን የሥራ ባልደረቦቹ የሆኑ ሹማምንት በስልጣን ጥማት እና በሹመት ቅናት ከንጉሡ ጋር መክረዉ ህግ አዉጥተዉ
ለርሱ ለመገዛት ወስነዉ ነገር ሸረቡ ዳንኤልም እንደጠበቁት ከወጥመዳቸዉ ገባላቸዉ፤ እዉን ንጉሥ ዳርዮስ እና ንግስተቱ ዳንኤልን
እንደተባለዉ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ይከቱት ይሆን? አናብስቱስ ይበሉት ይሆንን?
‘’
ንጉሡም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ በጣም አዘነ ያድነዉም ዘንድ ልቡን ወደ ዳንኤል አደረገ፤ ሊያድነዉም ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ደከመ፡፡
‘’ ዳንኤል 6÷14
ዳርዮስ
ያስብ እንጂ አልተሳካለትም፤ አጣብቂኝ ዉስጥ አስገብተዉታልና፡፡
ዳንኤል
ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣለ፡፡
በስተመጨረሻ
ንጉሡም ዳንኤልን የሚያመልከዉ አምላኩ እንደሚያድነዉ ያምናልና
‘’ሁል
ጊዜ የምታመልከዉ አምላክህ እርሱ ያድንህ አለዉ’’
ሹማምንቱም
ጉድጓዱን እንዳይከፈት የሚቻላቸዉን ሁሉ አደረጉ፤ ንጉሡም እያዘነ ወደ ቤቱ ሄደ እራትም ሳይበላ እንቅልፍም በአይኑ ሳይዞር አደረ፡፡
ዳንኤል
ምን አይነት ሰዉ ቢሆን ይሆን ንጉሡ ሳይቀር እንዲህ የሚጨነቅለት እና የሚያስብለት? በብልጣሶር ዘመነ ንግሥና ጀምሮ ዳንኤል በንግሥቲቱ
ሳይቀር ̎የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት ሰዉ …̎ የተመሰከረለት
ነበረ፡፡ ዳንኤል ከዚህም በላይ አስቀድመን እንደተመለከትነዉ መልካም መንፈስ፣እዉቀትም፣ ማስተዋልም፣ሕልምንም መተርጎም፣እንቆቅልሽንም
መግለጥ፣ የተቋጠረዉንም መፍታት… የሚችል ጠቢብ ነበረ፡፡
በዚህም
ጥበቡ ያገኝ የነበረዉን ከንጉሥ የተበረከተለትን ሐምራዊ ግምጃ፣ የወርቅ ማርዳ፣ የገዥነት ሥልጣን እምቢ ያለ ሰዉ እንደነበረ መጽሐፍ
ይመሰክርለታል፡፡ ትንቢተ ዳንኤል 5÷16 - 17
በበነጋታዉ
ንጉሡ ማልዶ ተነሳ ልቡ በሐዘን እንደተሰበረ ፈጥኖም ወደ አንበሶች ጉድጓድ ሄደ፡፡ በቀረበም ጊዜ ዳንኤልንም በህይወት ያገኝ እንደሆነ
በማሰብ፡- የሕያዉ አምላክ ባሪያ ዳንኤል ሆይ ÷ ሁል ጊዜ የምታመልከዉ አምላክህ ከአንበሶች ያድንህ ዘንድ ችሎአልን?̎
አለዉ፡፡
ዳርዮስ
ጀማሪ አማኝ ነዉ ቢሉ በእምነቱ እንዲፀና ፅኑዕ ነዉ ቢሉ ፍፁም እንዲሆን የሚረዳዉ አጋጣሚዉ ነበረ፡፡
ዳንኤል
ንጉሥም እንደመሰከረለት ተግባሩም እንደሚነግረን በምድራዊ ሥልጣኑ እንዳለ ሆኖ ሕያዉ አምላኩን ያመልክ ዘንድ አንዳች ማንገራገር
እንዳልታየበት፣ አልፎ አልፎ ሳይሆን ሲመቸዉ እና ጊዜ ሲያገኝ አልያም
ሥራ በሌለዉ ሰአት ሳይሆን ሁል ጊዜ አምልኮቱ ፍፁም እንደነበረ፣ የሚያመልከዉ አምላክ ሶስቱን ጓደኞቹን (ሰለስቱ ደቂቅን፡- በባቢሎን
አዉራጃ የተሸሙት ሲድራቅ፣ ሚሳቅ፣ አብድናጎም) እንዳዳናቸዉ እርሱንም ከአንበሶች ጉድጓድ አድኖታል፡፡
ዳንኤልም
በጉድጓዱ ዉስጥ በመሆን በቅንነት ለሚታዘዘዉ እና ለሚያገለግለዉ ንጉሡ እንደተለመደዉ ትናንት ሹማምንትህን ሰምተህ፣ ስልጣንህን ተመክተህ፣
እኔን ሳትሰማ፣ የነበረንን መልካም ግንኙነት ሁሉ ዘንግተህ በአንበሶች ጉድጓድ ብትጥለኝም ይብላኝ ላንተ እንጂ … ሳይል ያለ አንዳች
ትምክህት እና ትዕቢት መለሰለት፡፡
ንጉሥ
ሆይ÷ ሺህ አመት ንገሥ፡፡
̎ በፊቱ ቅንነት ተገኝቶባኛልና÷ በአንተም
ፊት ደግሞ ንጉሥ ሆይ አልበደልሁምና÷ አምላኬ መልአኩን ልኮ የአንበሶችን አፍ ዘጋ÷ እነርሱም አልጎዱኝም ̎አለዉ፡፡ ዳንኤል 6÷22
ቅንነት፣
አለመበደል፣ ትህትና፣ በቦታ ያልተገደበ ፍፁም እምነት፣ ወዘተ … ከሚመጡብን ከተሰወረም ይሁን ከተገለጠ ክፉ ነገር እንደሚያድነን
ዳንኤል ቀዳሚ ምስክር ነዉ፡፡
ንጉሡም
የተሰበረ ቅስሙ ተጠገነ፣ ሐዘኑ ወደ ደስታ ተቀየረ፣ ምግብ እና እንቅልፍ በማጣት የተጎሳቆለ ፊቱ ሲበራ ታየ፤ ዳንኤልንም ከጉድጓድ
ያወጡት ዘንድ አዘዘ፡፡ ዳንኤልም በአምላኩ ታምኖ ነበረና አንዳችም ጉዳት ሳይደርስበት ይበሉት ዘንድ ለቀናት ተርበዉ የከረሙ አንበሶች
ሳይበሉት ይልቁንም ሲያጫዉቱት አደሩ፡፡
በቀለኛ
ነኝ ያለ አምላካችን ለዳንኤል ጠላቶቹን በንጉሡ በኩል ተበቀለለት፤
እነርሱንና
ልጆቻቸዉንም ሚስቶቻቸዉንም በአንበሶች ጉድጓድ ጣሉአቸዉ … አንበሶቹም ያዙአቸዉ አጥንታቸዉንም ሁሉ ሰባበሩ፡፡
ነብዩ ዳንኤል ላይ ሹማምንቱ ለምን አሴሩበት? ያልን እንደሆነ ዳንኤል ከናቡከደነፆር
ዘመን ጀምሮ በህልም ፈቺነቱ እና መልካም አገልግሎቱ በተነሱት ነገሥታት ዘንድ ሁሉ ተወዳጅ በነገስታቱ ሚስቶች ዘንድ ሳይቀር ስለ
ጉብዝናዉ ምስክርነት ያገኘ ነዉ፡፡ በዚህም የተነሳ ለሥልጣን የተመረጠ በቅን አገልግሎቱም የተነሳ በየጊዜዉ በየደረጃዉ ለሥልጣን
እየታጨ ያለ፣ የመንግሥት እኩሌታ ሳይቀር ተሰጥቶት እምቢ እያለ ያለ ሰዉ ከመሆኑ የተነሳ ቅናት አድሮባቸዋልና እንዲህ እንዲያደርጉ
ያነሳሳቸዉ ያለዉ ቅናት ነዉ፡፡
ዳንኤልን
እንዲህ ትንሽ ትልቁ ሳር ቅጠሉ የሚወደዉ እና ለርሱ ጥብቅና የሚቆም ለምስክርነት የሚሰለፍ ከሆነ ሹማምንቱ ንጉሡን ወጥመድ ዉስጥ
ማስገባት ለምን ፈለጉ? ንጉሥ ዳርዮስ በቀጥታ ለክስ ስለ ዳንኤል ክፉ ነገር ይዘዉ ቢቀርቡ ንጉሡ ምን ብሎ እንደሚመልሳቸዉ እና
ክሱም እንደሚከሽፍባቸዉ ስለሚያዉቁና ይህንን አስቀድመዉ ስለተገነዘቡ ሌላ ዘዴ ፈለጉ፡፡ ይህ እንኳን ባይሳካ ንጉሡን በዳንኤል የተነሳ
ከህዝቡ ጋር ቅራኔ ዉስጥ እንከተዋለን ከተሳካልንም እናጣላዋለን በማለት ማሴራቸዉ ለዚህ ነበረ፡፡
ንጉሡም
እንዲህ ይሆናል ብሎም ስላላሰበ አንድም መዉጫ ቀዳዳዉ ስላላሰበ አንድም የእግዚአብሔር መልአክ የዳንኤልን በእግዚአብሔር አጋዥነት
መዳን አመላክቶት ይህንን ወጥመድ ሊያመልጥ ችሏል፡፡
ዳንኤልም
ከአንበሶች ጉድጓድ ተጥሎ አንበሶቹም ሳይበሉት ይልቁንም ሲያጫዉቱት አድረዉ ከሞት ትርፏል፤ በእርሱ እግር የተራቡት አንበሶች ሸረኞቹን
መኳንንት እና ቤተሰብ ለቁርስ አድርገዋቸዋል፡፡
አሣ
ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል የሰዉ ፈላጊ የራሱን ያጣል እንዲሉ፤
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ