መፅሐፍ ስለምርኮ በሚናገረዉ በዘመኑ ስለተደረጉት
ዋና ዋና ድርጊቶች ሲተርክ በባቢሎን በስደት መኖርን ሲያነሳ ታላላቅ ሰዎች ብሎ ካነሳቸዉ መካከል ሕዝቅኤልና ዳንኤል ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡
ብልጣሶር፡- ትርጉሙ ቤል (የባቢሎን ጣኦት) ንጉሥን ይጠብቀዉ ማለት ነዉ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ
46÷1
1)
የናቡከደነፆር የልጅ ልጅ
የናቡናዲስ ልጅ፡፡ የአዲሲቱ ባቢሎን መንግሥት የመጨረሻ ንጉሥ፡፡
በመጠጥ ግብዣ ጊዜ በቤቱ ግንብ ላይ ፅሕፈት
የምትፅፍ እጅ ታያቸዉ ፅሕፈቱም ፡- ̎ማኔ ቴቄል ፋሬስ̎ የሚልነበረ፡፡
ንጉሡም ደንግጦ ትርጉሙን ሲፈልግ ዳንኤል እንዲህ
ብሎ ተረጎመለት፡፡
̎ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቆጠረዉ፣ ፈፀመዉ፣
በሚዛን ተመዝነህ ቀለህ ተገኘህ፤ መንግሥትህም ተከፈለ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ፡፡̎ ዳንኤል 5÷25-28
በዚያ ሌሊት የባቢሎን መንግሥት በፋርስ እጅ
ወደቀ፡፡ ይህም የሆነዉ በ539 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነዉ፡፡ ዳንኤል 5÷1-30፣ 8÷1
2)
ለዳንኤልም የተሰጠ ሥም ነዉ፡፡
ዳንኤል 1÷7 በሥም እኩል በግብር ሥንኩል ማለት እንዲህ ነዉ፡፡
ዳንኤል ማን ነዉ?
የስሙ ትርጓሜ ፡- ̎ እግዚአብሔር ፈራጅ ነዉ̎ ማለት ሲሆን
ትዉልዱ፡-
መጻሕፍት እንደሚሉት የተወለደዉ በ618
ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ትዉልዱም ከይሁዳ ነገድ ስለሆነ ከንጉሳዊ/ከመሳፍንት
ቤተሰብ እንደሆነ ይገመታል፤ የዮናኪር የልጅ ልጅ ነዉና፡፡ ምነዉ ቢሉ ዮናኪር የንጉሡ የኢዮአቄም (የእስራኤል ንጉሥ) ልጅ ስለሆነ፡፡
የኢዮአቄም ዘመነ ንግሥናዉም ከ609 እስከ 598 ከክርስቶስ ልደት በፊት ማለት ሲሆን የነገሠዉም በ18 አመቱ እንደሆነ ይነገራል፡፡
አንዳንዶችም በ25 አመቱ እንደነገሠ ይናገራሉ፡፡ ዳንኤል ግን መሾሙን መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ዳንኤል 1÷6
ችሎታዉ፡- ብዙ ችሎታ እንዳለዉ ይነገራል፣ የከለዳዊያንን ቋንቋ እና ትምህርትም ተምሯል፡፡ ዮሴፍ
ወልደኮርዮን እንደሚገልጠዉ ከሆነ የለየለት አርክቴክት ነዉ፡፡እጅግ ጥበበኛ፣ ንቁ አስተማሪ፣ ዉብ እና በአካል ጠንካራ ነዉ፡፡
ሌላ ስሙ፡- ብልጣሶር የበአል ልዩ መስፍን ምስጢሩንም የሚያዉቅ ማለት ነዉ/በአል፡-
የባቢሎን ዋናዉ ̎አምላክ̎ ጣኦት ነዉ/፣ የሰማይ መላዕክት ̎እጅግ የተወደደ ሰዉ̎ ብለዉታል፡፡
የህይወት ታሪኩ፡- በምርኮ ወደ ባቢሎን የመጣ ሲሆን ( አልጋ ወራሽ /ገና አልነገሰምና/
ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት፡፡ በኋላም የተወሰኑ ነዋሪዎቿን ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸዉ ፣ ሰለስቱ ደቂቅን ጨምሮ
ዳንኤል የተማረከዉ እንዲህ ነበረ )፤ በባቢሎንም እንደተሸመ ያመለክታል፡፡ ዳንኤል 1÷17-21 ከ618 እስከ 534 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በመኖር በ84
ዓመቱ በዚያዉ በባቢሎን አርፏል፡፡ እድሜዉን አንዳንዶች 70 የሚሉትም አሉ፤ ዕድሜዉ አያጣለላንም ምግባሩን ለመጨበጥ እንጂ፡፡ ባቢሎን
ማለት የአሁኗ የኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ 80 ኪ.ሜትር በስተደቡብ የነበረች ከተማ ነች፡፡
እስከ 536 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ናቡከደነፆር፣
ብልጣሶር ፣ ዳርዮስንና ቄሮስንም በማስተማር ሕልም በመፍታት ጽሑፍንም በመተርጎም አገልግሏል፡፡ ለእግዚአብሔርም ህዝብ እየጸለየ
ብዙ ራእይ ተመልክቷል፡፡
የሕይወት ገጠመኞቹ፡- ጣኦት ባለማምለኩ በአንበሶች ጉድጓድ ተጥሏል÷ እግዚአብሔር
ግን አዳነዉ፡፡
ባህርይዉ፡- ዳንኤል በመልካም አካሄዱ የታወቀ
ሰዉ ነበር፡፤ ትንቢተ ሕዝቅኤል 14÷14-20
ሥራዎቹ፡- ብዙ ሕልሞችና ራእዮችን የተመለከተና የተረጎመ ነዉ፡፡ ትንቢቶችንም ተናግሯል/ የትንቢተ
ዳንኤል ጸሐፊ ነዉ፡፡ መጽሐፉም በአስራ ሁለት ምእራፎችም የተከፈሉ ናቸዉ፡፡
ማንነቱ፡- ለአምላኩ ታማኝ በመሆኑ በባቢሎን ቤተመንግሥት ያለዉ ምቾትና ቅንጦት ማንነቱን እንዳያረክሱት
እጅግ ከመጠንቀቁ የተነሳ በንጉሡ ምግብ እና መጠጥ እንዳይረክስ ይጠነቀቅ ነበረ፡፡ መናኛ ምግብ ይመገብ ዉሃን ብቻ ይጠጣ ነበረ፡፡ፆመኛና
ጸሎተኛ ነበረ፡፡
ናቡከደነፆር እና ብልጣሶር የገዟትን ምድር ከብልጣሶር
ሞት በኋላ ዳርዮስ እንደነገሰ ከ120ዎቹ መሣፍንት አንዱ አድርጎ ዳንኤልን ሾሞታል፡፡ ዳንኤል 6÷1-2 ከ120ዎቹ ሶስት የበላይ
አለቃ ሲሾም አንዱ ዳንኤል ነበረ፡፡
̎ዳንኤልም መልካም መንፈስ ስላለዉ ከአለቆችና
ከመሣፍንት በለጠ፣ ንጉሡም በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ይሾመዉ ዘንድ አሰበ፡፡̎
በዚህን ጊዜ አለቆችና ሹማምንት ምንም እንኳን
ስህተትና በደል ባያገኙበትም ዳርዮስ በዳንኤል ላይ ባለዉ ፅኑ እምነት ለበለጠ ሥልጣን እርሱን ማጨት ዐይናቸዉ ቀላ ቅናትም አሳረራቸዉ፤
በርሱ ላይም ከጓዳ እስከ አደባባይ ክፉ ወሬን ማዉራትና ማስወራት ጀመሩ፡፡ነገር ግን ከንጉሥ ፊት ሞገስን አግኝቷልና ከዳርዮስ ጋር
የሚያጋጨዉ ሥልጣኑን የሚያሳጣዉ የተመኘለትንም የሚያስከለክለዉ አንዳች ነገር ታጣበት፡፡
ሆኖም ግን ክፋት አያስተኛምና አልተኙለትም፤
ምንስ አንዳች ሰበብ እንደሚያገኙ መፈለግ ጀመሩ እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኑበት፡፡ ነገር ግን እንዳሰቡት
ቀላል አልነበረምና የልባቸዉ አልሆነም፡፡ በስተመጨረሻ ምክራቸዉን በአንድ ነገር ቋጩ፡፡
መጽሐፍ እንደሚነግረን ፡- ̎ እነዚያም
ሰዎች፡- ከአምላኩ ሕግ በቀር በዚህ በዳንኤል ላይ ሌላ ሰበብ
አናገኝበትም አሉ፡፡ ̎ ትንቢተ ዳንኤል
6÷5
ይህንንም ተንኮልና ደባቸዉን የንጉሱ ወዳጅ በመምሰል
የክፋት ወሬያቸዉን ለንጉሱ ነገሩት እርሱም ሰማቸዉ ሹማምንቶቹ ናቸዉና የተባለዉ ነገር ይፀና ዘንድ የተነጋገርነዉም ነገር እንደ
ሜዶንና እንደ ፋርስ ሕግ እንዳይለወጥ ትእዛዙን አጽና ብለዉ የንጉሱን ነፍስ አስጨነቁም በሸረቡትም ወጥመድ ዉስጥም ከተቱት፡፡ ትዕዛዙም
እንዲህ ይል ነበር፡-
̎ ንጉሥ ሆይ ÷ከእንተ በቀር ማንም እስከ ሰላሳ ቀን ድረስ ልመና ከአምላክ ወይም ከሰዉ
ቢለምን በአንበሶች ጉድጓድ ዉስጥ ይጣል፡፡ ̎ የሚል ነበር፡፡ ዳንኤል 6÷7
ይህንን
ይበሉ እንጂ ማንም የምትለዉ ለዳንኤል እንደሆነ ከአምላክ የተሰኘችዉ ቃል ለዳንኤል መሆኑ ልባቸዉ ያዉቀዋል፤
ከእርሱ በቀር ከነርሱ መካከል ፅኑ ቁርኝት ከአምላኩ ጋር እንደርሱ ያለዉ የለምና፡፡ ልብ ሲያዉቅ ዶሮ ማታ እንዲሉ፡፡
እንዲህም
ሆነ ፡- ዳንኤል ወደ ቤቱ እንደተመለሰ ̎ የእልፍኙ መስኮቶች ወደ ኢየሩሳሌም አንፃር ተከፍተዉ ነበር፤ ቀድሞም ያደርግ እንደነበረ
በየእለቱ ሦስት ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት ጸለየ አመሰገነም፡፡ ̎ ዳንኤል 6÷10
ዳንኤል
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰዉንም የሚያፍር እንጂ ክፉ የሚገኝበት አልነበረም፡፡ ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል
የሚለዉ አባባልም በአጠገቡ አያልፍምና፡፡ በባዕድ አገር ስላለሁ፣ በፈለኩት ሰአት ምግብ ስለማላገኝ፣ ንጉሡ ያቀረበዉን ምግብ እንቢ
ማለት ስለማልችል፣ ንጉሡን እንዳይከፋቸዉ፣ የመንግሥት ተሿሚ ነኝና ህዝብን ስለማገለግል፣ ሥራ ስለሚባዝብኝ ጊዜ ስለሌለኝ፣ ወዘተ
ብሎ አምላኩን የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ጊዜዉን እና ማንነቱን በአግባቡ የሚጠቀም ትክክለኛ ሰዉ እንጂ፡፡
ሹማምንቱ
ግን በአንድነት ሆነዉ አሴሩበት ፤ በዳንኤልም የተነሳ ንጉሡን ሣይቀር ወጥመድ ዉስጥ ከተቱት፡፡
ይቆየን፡፡
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ