31 ዓመት ፣ ሁለት መንግሥት፣ ብዙ ምኞት፣ ብዙ ጥረት ብዙ ሙከራ፣ ብዙ ሽንፈት…..ሶስት ዓሥርት ዓመታትን የዳፈነው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ለራሱም የናፈቀውን ድል ለኢትዮጵያ ህዝብም ያለውን የእግር ኳስ ፍቅርና ድል ከትውልድ ወደ ትውልድ ከመንግሥት ወደ መንግሥት ሲቀያየር የነበረውን ጉጉቱን ጥቅምት 4 ቀን 2005 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እስታዲየም ከቀኑ ዓሥር ሰዓት ጀምሮ ከሱዳን አቻው ጋር ያደረገውን ትንቅንቅ በ2ለ0 90 ደቂቃውን ሲያጠናቅቅ በየቤቱና በየቦታው ድምፁን አጥፍቶ በድጋፍና በጉጉት ሲከታተል የነበረውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር ዳር እንዲነቃነቅ አድርጐታል፡፡ ዋልያዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለአገር ክብር፣ ለትውልድ ታሪካዊ የሆነውን ድል ለማስመዝገብ የቻሉት ከተለያየ ቡድን ተውጣጥተው በአንድ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሠልጥነው አሥራ አንድ በመሆን ተጫውተው በኢትዮጵያ ህዝብ ድጋፍ በጨዋታና በግብ ብልጫ ኢትዮጵያን ለአፍሪካ ዋንጫ በደቡብ አፍሪካ እንድትሳተፍ አብቅተዋታል፡፡
ብሔራዊ ቡድኑ ጐል አስገብቶ ማሸነፍ አሸናፊነትን ማሥቆጠር ብቻ አልነበረም የሠራው:ለ31 ዓመታት የተዳፈነውን የተናፈቀውን ለአፍሪካ ዋንጫ
መሳተፍ፣አንገት ደፍተንበት ተስፋ ቆርጠንበት የነበረውን የእግር ኳስ ነገር በቃ አከተመለት የተባለውን ዋልያዎቹ አባቶቻችን የፈፀሙትን
በታሪክ የሠማነውን መላው ኢትዩጵያዊ የናፈቀውን እኛም ናፍቆናልና ለድል ደርሰናልና አይዞሽ አንገትሽን ደፍተሽ ካቀረቀርሽበት ቀና
እናደርግሻለን፣ የጓጓሽውን እናሳይሻለን በማለት ቃል ገብተው ቃላቸውን ጠብቀው ቃላቸውን ፈፅመው አኰሯት ህዝቧን አስደሰቱት፡፡
በግማሽ 45 ደቂቃ ያልታየው ተስፋ የደበዘዘው ድባብ ዳግም አንገታችንን
የሚያስደፋ አስመስሎት ነበር የአዳነ ግርማ ሙከራውን ለጐል አለማብቃትም ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍለንም ነበር፣ ነገር ግን ያ ከዋልያዎቹ
ሲጠበቅ የነበረው የሁለት ግብ አብላጫ ድል የማታ ማታ እውን ሆኖ ወንዱን ከሴት፣ወጣቱን ከአዛውንቱ ከምሽቱ አሥራ ሁለት ሠዓት ጀምሮ
ከእስታዲዮም አንሥቶ በቴሌቭዠንና በሬድዮ ሲከታተል የነበረውን ሁሉ አስፈንጥዞታል፡፡
የአገር ኩራት የሆኑትን ዋልያዎች ለመደገፍ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ብቻ
ሣይሆን ከመላ አገሪቱ የመጡ ወጣቶችና አዛውንቶች ነበሩ፣ በዋዜማው
ከምሽቱ 5 እና 6 ሰዓት ጀምሮ የእስታድየም መግቢያ ትኬት ለመግዛት ተራ ሲጠብቁ ያደሩ ጥቂት አልነበሩም፡፡ ከሃያ ሁለት ሺ የማይበልጡ ተመልካቶችን የመያዝ አቅም ያለው የአዲስ አበባ
እስታድየም እስከ 30 ሺ የሚጠጉ ተመልካቶችን ተጨናንቆ በመያዝ ሲያስተናግድ
ከዚያ በላይ ብዙ ጊዜ እጥፍ በጉይዋ የያዘችው አዲስ አበባ ዳግም በቴሌቭዠን መስኮት ለዘጠና(101) ደቂቃ ስታስኮመኩም ነበረች፡፡ አመሻሽ ላይ ግን በውስጥም በውጭም የነበረውን ህዝብ ጮቤ አስረገጡት ዋልያዎቹ፡፡
ዋልያዎቹ አገርን ወክለው ሲጫወቱ ሌላ ጊዜ በዚሁ አዲስ አበባ እስታድየም እንደጠላት እየተያዩ የሚፋለሙ የተለያየ ቡድን ተጫዋቾች ዛሬ ግን የጋራ አገራቸውን ጉዳይ በአንድነት በመሆን ጉዳየቸው በማድረግ አንዱ ከሌላ ቦታ
መጥቶ አጥቂ ፤ ሌላው ተከላካይ ፤ሌላኛው ወገን አማካይ ከአንደኛው ቡድን የመጣው ዳግም በረኛ የቀረው ደግሞ ተጠባባቂ በመሆን አገርን
ለድል ህዝብን ለደስታና ለኩራት በአንድነት አደባባይ ወጥተው እንዲዘምሩና እንዲጨፍሩ አድርገዋል አንድ ሆነው ለአገር በመስራትና
ውጤትን በማምጣት እምዬ ኢትዮጵያ አንገቷን ያስደፋት ለዘመናት የናፍቋት ህዝቦችን በሰቀቀን በጉጉት እንዲያልቁ ያደረጋቸው ከዛሬ
ነገ ታሪክ ይቀየራል እያለ ዓመታት በተቀየረ ቁጥር የሚያስናፍቃቸው ብዙ አገር አለ ከጫፍ ጫፍ አንድ ሆነን ልንወጣበትና ድል ልናደርገው
የሚገባ ጥንተ ጠላታችን ድህነት፣ ጦርነት፣ እርስበርስ መጠላላትና መከፋፋል፣ በሽታ…. እነዚህ ሁሉ እንደ እግር ኳስ ድል በአገራችን
በኢትዮጵያ ከተናፈቁ ዘመናት ተቆጥረዋል መገላጫዋ በረሃብ ህዝቦቿ የሚረግፋ በእርስበርስ ጦርነት የምትታመስ በሽታ የሚያጠቃት፣
በመከፋፍል ያለቁ…… የሚለው መለያችን ከሆነ ሰነበቱ፡፡ ይህን ዘመናት ያስቆጠረ ታሪክ ለመቀየር፣ የናፈቀንን አንድነት ለማምጣት፣
ስማችንን ለማደስ አንገታችንን ቀና አድረገን ደርታችንን ነፍተን በዓለም አደባበይ ለመታየትና ለመናገር፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ነን ርሃብ ጦርነት በሽታ የትናንት ታሪካችን እንጂ የዛሬ ማንነታችን አይደለም
ዛሬ እኛ ኩሩ ህዝብ ነን፣ ትናንት ተከፋፍለን እርስበርስ ብንዋጋም ዛሬ ግን እጅ ለእጅ ተያይዘን በፍቅራችን ለዓለም ምሳሌ መሆን
የምንችል ነን፣ ትናንት የዓለም ቁንጮ እንዳልነበርን ዛሬ የዓለም
ጭራ ብንሆንም ነገ ግን ታሪካችን ተቀይሮ ሁላችንን ለልማት ጠንክረን በመነሳታችን የትናንቱ ቦታችን የዓለም ቁንጮነትን
እንይዛለን በድህነታችን ብዙዎች ጣታቸውን እንዳልቀሰሩብን ነገ ግን ለዓለም የምንደርስና ተምሳሌት የምትሆን ኢትዮጵያን እንፈጥራታለን ለማለት ኢትዮጵያዉያን በልባችን የሞላውን ልዩነትና
ክፋት በማስወገድ ለአንድ አገራችን/ኢትዮጵያ/ዓላማ ስንል ሁሉን ወደ ጐን በመተው እንደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ
ቡድን ተግትን ቀሪውን አርባ አምስት ደቂቃ ልንጫወት ግድ ይላል ያለፈው 45 ደቂቃ አርኪ ተስፋሰጪ አልነበረም ንጉሱ በደርግ ደርግ በኢህአዴግ ኢህአዴግ ደግሞ በእርስበርስ መተካካት ጊዜው ባክኗል እንደ አዳነ
ግርማ ሙከራን ለጐል አለማብቃተና መሳሳት ብዙ ዋጋ ሲያስከፍል እነደነበረ በደርግ ጊዜ በጦርነት በምርጫ 1997 ዓ.ም. በወጣቱ
ሞት እስርና እንግልት የኢትዮጵያ ራዕይ ለማሳካት ብዙ ተከፍሏል ዛሬም እንዲሁ፣ አሁን ግን ረጋ ብለን የምናስብበት የዕረፍት ሰዓት
የሚተኙበት የሚቀመጡበት ሳይሆን እርስ በርስ የሚመክሩበት ደካማን
የማያጠነክሩበት ተቀያሪ የሚቀይሩበት ከአሰልጣኝ ምክርና ተግሣፅ ማበረታቻ የሚያገኙበት ጊዜ ላይ ነው፡፡ ያለነው ሆኖም ጊዜው አጭር ነው፡፡
ለቀሪው
45 ደቂቃ ተግትን ለመሥራት ታሪክ ለመቀየር የጠፊውን የኢትዮጵያ ህዝብ ጥም በአንድነት የምናረካበት ለአገር የምንሰራበት ልዩነትን
አጥብበና ወደጐን በመተው ለአገር ክብርና ጥቅም ሲባል አንድነትን በመፍጠር አንተ የእገሌ ነህ አንተ የእንቶኔ ነህ ውጤት ልመባባሉን
ትተን መድረክ ቅንጅት አንድነት ፣ኢህአዴግ፣ኦነግ፣ ኦብነግ….. ወዘተ የሚባሉት ድርጅታዊ ስሞች ትተን ኢትዮጵያዊነትን ይዘን ለአንዱ
አገራችን ለሠፊው ህዝባችን ቅድምያ በመሥጠት ልንሥራ ናስመዘግብ ይገባል እንደ ከዚህ ቀደሙ ሆድ የሚነፋ ተስፋ ህበረተበቡ አያሻውም
አገርም አያስፈልገውም፡፡
የኢትዮጵያን ህዝብ እንደምናየው ለአትሌቱም፡ ለእግር ኳሱም፡ ለአባይም…..
ድጋፉን በነቂስ ያሳያል ባለሀብቱም ለድጋፍ እጁን ይዘረጋል፡ቃል ይገባል፡ከዚህ ቀደም እንዳስለመዱት ለተጫዎችቹ የተለያዩ ስጦታዎችን
ለማበርክት ቃል የገቡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ታዲያ የፓለቲካ መሪዎቻችን፣
የሃይማኖት አባቶቻችን መከፋፈሉን ትተው እርሰ በርስ መነቋቆሩን አቁመው በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘው በአንድ አላማ ለአንዲት
አገራቸው ለሠፊው ህዝባቸው ቢተጉ እውን ኢትዮጵያ ሥሟ በርሃብና በእርስበርስ ጦርነት ይነሳ ነበር በፍፁም ሃያ እና ሰላሳ አባላት የያዘ አንድ ቡድን የደገፈና ለድል ያበቃ ህዝብ፣ ቡድኑን በመምራትና በማሰልጠን
ለድል ያበቃ አንድ አሰልጣኝ ሰ31 ዓመታት በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ካቀደጀና ለአፍሪካ ዋንጫ ካበቃ አንድ የአገር መሪ ደግሞ ከሚኒስተሮችና በተለያየ ደረጃ ላይ በመሆን የሚሰሩትን
ባለስልጣናት በመያዝ 80 ሚሊዮን የሚሆነውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከጐኑ በማሰለፍ ኢትዮጵያን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ ማሰለፍ ፣ ህዝቦቿን ደግሞ እስር በርስ
የሚፋቀሩ አገርን ለማልማት ጠንክረው የሚሰሩ ዜጐች ማድረግ ይችላል፡፡
የፓለቲካ ልዩነትን ወደ ጐን በመተው አገርንና ህዘብን
በማሰብ መከፋፈል ያሳደጋት አገር፣ እርስ በርስ ጦርነት
ያለማት አገር የለችም ስለዚህ ትናንት አልፋል በትናንት በሬም ያረሰ
የለም ዛሬ ደግሞ 45 ደቂቃ ግማሹ ዘመናችን ተጋምሷል በቀሪው ጊዜአችን አመርቂ ውጤት ለማምጣት የጐሪጥ መተያየቱን ትተን ተናበን
ወደ ድል ለማምራት አንዱ እንሁን ህዝቡን ለጦርነት ሣይሆን ለልማት እንጠቀምበት በድጋሜ ዛሬ ላይ ሆነን የምንሥተው ሥተት እንደትናንቱ
በቸልታ የሚታለፍ ሣይሆን ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍለን ከተለወጥን ዳግም ከድህነት ታሪክ ወደ መካከለኛ ገቢ የምንሸጋገርበት አለበለዚያ
ግን ባለንበት የምንረግጥ ባስ ካለም እጅግ ወደታች የምንዘግጥበት ሰዓት ነው፡፡
በአገራችን ላይ የተንሰራፋው ችግር የጐልማሳ ዕድሜ የያዘው በተተኪው ትውልድ
በጐረምሣው ታሪክ ሆኖ ሊቀር ጊዜው አሁን ነው የመተካካቱ ጅማሬ አኩሪ በሆነ
መልኩ ሊቀጥል ግድ ይላል አሰልጣኝ ሠውነት ቢሻው በጥንካሬ ቡድናቸውን በታክቲክ በቴክኒክ በሞራል በአካል ብቃት በአሰላለፍ…… ወዘተ ብቁ በማድረግ ከድል እንደበቁት ሁሉ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር
ኃይለማርያም ደሳለኝ ብሔራዊ የአገር ተወካዮች ምክር ቤት አባላትን፣ ክቡራት ሚኒስተሮችን አምባሳደሮችን፣… ወዘት ለልማቱ ለዕድገትና
ትራንስፎርሜሽን ብቁና ትጉህ ቀና ቡድን ሊያበቁ የሚገባበት ሰዓት አሁን ሉ፡፡ ለአገር ዕድገት የተናጠል ሣይሆን የጋራ /የቡድን/ ሥራ የሚሠራበት ሠዓት
ላይ እንደሚገኙ ልብ ሊሉት ይገባል፡፡
አሁን ጊዜው የፓለቲካ ልዩነት ወደጐን የሚባልበት የአገር አንድነትንና
ልማትን አንግበን የምንነሣበት ሰዓት ላይ ነው ያለነው እገሌም እንቶኔም ማንመ ይሁን ምንም በጥላቻ መፈራረጅ አቁመን በፍቅርና በአንድነት
መንፈስ ለአንዲት ኢትዮጵያ ለሠፊው ህዝብ ጥቅም ሲባል መሥራትና ማልማት
ብቻ በግብ ብልጫ ለድል መብቃት እገሌ የሚባል ድርጅት አባል ግብ አስቆጠረ መሆኑ ቀርቶ ኢትዮጵያ አሸነፈች የሚለው ሊቀድም ይገባል፡፡ የባከነ ሰዓት ላይ ነውና ያለነው ጠላትን በመከላከል ክፍተትን በመሸፈን አስተማማኝ
ውጤትነ ለማምጣት መከላከልን መሠረት ያደረገ ጥቃት በድህነት ላይ
በጦርነትና በረሃብ ላይ በድንቁርና እና በበሽታ ጥቃት መፈፀም ግዴታ ነው ፡፡
ብሔራዊ ቡድናችን ለዚህ ድለ እስከሚበቃበት በብሔራዋ ቡድኑ ብዙ አጥቂዎች
ተከላካዮች አማካዮች ነበሩት ይበልጡኑ ደግሞ ግብ በማግባት የሚታወቁ ነገር ግን በጉዳት በተለዩበት ሰዓት እነርሱን ሳናሳልፍ እንዴት
ብሔራዊ ቡድኑን ለጨዎታ እናሰልፋለን ብሎ ህዘቡ ሲጨነቅ ቡድኑ ግን አጥቂያችን ቢጐዳ አንበላችን መካከላችን ባይኖር እኛም ግብ ማስቆጠር
እንችላለን አምበልም ከመካከላችን ማፍራትና መተካት እንችላለን፣ የቡናው ባይኖር የጊዮርጊሱ ከዚያም ቢጠፋ የደደቢቱ ወይም የስኳር
ፋብሪካው አለ በማለት በልብሙሉነት የአገራቸው ታሪክ እንደቀየሩና
የ31 ዓመቱን ክብሯን መልሰው ለማምጣት እንደበቁ መላው ኢትዮጵያዊ በክቡር ጠቅለይ ሚኒስትሩ እና በብፁዕ ፓትራያሪኩ ድንገተኛ ህልፈት
ህይወት ቢደናገጥና ተስፋ ቢቆርጥ የተያዘው ልማት እንደማይደናቀፍ እኛም አለን በማለት ከየድርጅቱ የጐደለውን አሟልተውና የተሻለ
ቡድን በመፍጠር የአገርን ሥምና ታረክ መጠበቅ ግድ ይላል ኢትዮጵያዊነት የሚለካበት ጊዜው አሁራ ነውና እነዚህ ሠዎች ቢኖሩ መልካም ነበር ባይኖርም ግን እንሰራለን እንለወጣለን የአንድ ሠው አስፈላጊነት አለ የማይባል
ቢሆንም አገር ግን በአንድ ሠው ራዕይና ግብ የትም አትደርስም በህብረትና በአንድነት እንጂ እነዚሀ ሠዎች ለአገር ያላሠለሰ ጥረት
ቢያደርጉም ዛሬ የሉም እነርሱ የሉምና አገር እጃን አጣጥፋ ትቀመጣለች ማለት አይደለም ተጫዋቶቹ የብሔራዊ ቡድኑ አባል ናቸው እንጁ
ብሔራዋ ቡድኑ የነርሱ /የግለሰቦች/ ነው ማለት እንዳልሆነ እንዲሁ እነዚህ መሪዎች የአገርና የህዝብ ሀብት ናቸው እንጂ አገር የነርሱ
የግል ጥቅም የነርሱ የአዕምሮ ውጤት ናት ማለት አይደለም ምናልባት የላቀ አስተዋፅኦ አድርገው ይሆናል አድርገዋልም ነገር ገን በነርሱ
ህልፈተ ህይወት የአገር ጉዳይ ተዳፈነ ማለት አይደለም ጥቂቶች ቢያልፋ በብዙሃን ይተካልና፡፡
በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ አጥቂው በጉዳት ከሜዳ ስለወጣ አለበለዚያም በቅያሬ
ከሜዳ ስለወጣ ተከላካዩ መከላከሉን በረኛው ግብ መጠበቁን አማካዩ አቀብሎ ተተኪው ግብ አያስቆጥርም ማለት እንዳልሆነ እንዲሁ የተያዘውን
መርኃ ግብር ልማት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት የቀድሞዎቹ ባለድርሻ አካላት አዲሶቹም ተሻሚዎች ነባሮችን ተክተው
ዕቅዱን አያስፈፅሙም ማለት አይደለም፡፡ በእግር ኳስ ሜዳ አጥቂው ሲወጣ ሌላ አጥቂ ይመጣል እንጂ የማጥቃት ሞያውን ለብሔራዊ ቡድኑ ይዞ የግድ የአጥቂውን የማልያ ቁጥር ይዘህ ካልመጣህ ሥምህን ካላስቀየርክ እንደማይባል እንዲሁ የጠቅላይ ሚንስትሩን ሥም ብሔር
አስተሳሰብ እምነት አቋም፣ ቋንቋ፣…… ይዘው መምጣት አይጥበቅባቸውም ዋናው አላማቸው ግብና ውጤት እንጂ፣ ተቀያሪው ሲመጡ ያሰሩትን ሊፈቱ፣ የነፈጉትን ሊሰጡ፣ የሾሙትን ሊሽሩ፣ ያጥላሉትን ሊወዱ፣ ያራቁት ሊያቀርቡ፣
የሠቀሉትን ሊያወርዱ… ህጉ ይፈቅድላቸዋል የርሳቸው ለምድ ለብሰው ሊመጡ አይገደዱም ተተኩ ሳይሆን የሚባለው በምትሃተዊ መንፈስ ተቀየሩ
እንጂ ስለዚህ ብሔራዊ ቡድን ጨወታ ላይ የቡድን ውጤት አሳምሮ አገርን ለድል ለማብቃት የመተካካቱን ሥራ በጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል
ምናልባት እንደብሔራዊ ቡድናችን ተጫዎቻችን በጉዳት አለበለዚያም በቀይ ካርድ ከሜዳ ስናጣ ባለሙያውን በረኛ መቀየር አቅቶን ተጫዎች
ውጤቶን ለማስጠበቅ ለቁጥር ያህል ብቻ ሲባል ሙያው ያልሆነውን ተጫዎች
በመተካት ታሪክ ሊያበላሽ የሚችል ዋጋ ልንከፍል እንችላለንና ብሔራዊ ቡድኑም ፓርላማውም ይህን ልብ ይበሉት፡፡
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEj89l3k7YwrEQx75OanfkPEmaWeBOhW74joxKQBnF2wLvBCTojic0HW127T2G4CbrjpcNgchi_V4qEfosXWsOgqICek07dQzt7Aeu-y3OWhPx1ri0YLWc1Qs8dXBoGwnZ61H32XpnCUERM/s320/560839_477174525649179_1994989402_n.jpg)
![](https://blogger.googleusercontent.com/img/b/R29vZ2xl/AVvXsEj89l3k7YwrEQx75OanfkPEmaWeBOhW74joxKQBnF2wLvBCTojic0HW127T2G4CbrjpcNgchi_V4qEfosXWsOgqICek07dQzt7Aeu-y3OWhPx1ri0YLWc1Qs8dXBoGwnZ61H32XpnCUERM/s320/560839_477174525649179_1994989402_n.jpg)
ወደ ማጠቃለያው ማንሳት የምሻው ዐብይ ጉዳይ የብሔራዊ ቡድናችንን ደስታ
የህዝባችንን ተሰፋ ታሪክን እንደነበር ሊያስቀጥልና የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ህልማችንን ሊያደበዝዝ የነበረው የመጨረሻ የሱዳን አቻችን
ሙከራ ግብ መሆን ነበር ሴኔጋላዊዉ ዳኛ የጫወታውን ፍፃሜ ማብሰሪያ ፊሽካ ባይነፋ ኖሮ ይህ የሚያመለክተው አሁንም በእግር ኳሳችን ላይ ምንም አንኳን ድልን መጐናፀፍ ብንችል ጠንክረን ያልስራነውና
ያልደፈነው ክፍተት እንዳለ ያሳየናል ስለዚህ የብሔራዊ ቡድኑ ዛሬም
ለደቡብ አፍሪካው የዋንጫ ትንቅንት የበለጠ ሊራ ህዝቡም ከሜዳ ውጭም ሊያበረታቸውና ሊደግፋቸው ሊመክራቸውና ሊገስፃቸው ለድል ሊያበቃቸው
የሚገባውን ሁሉ ሊያደርግ ይገባል፡፡ ልብ ብለን ልናጤነው የሚገባው
ይህ ትውልድ ሊቀይረው ያልቻለውን ጉዳይ ዋጋ እንከፍልበት ነበር የተዘናጋንባት
የመጨረሻ ግብ ታሪክ ታዝባ፣ ደስታን ታጨልም፣ ሌሎች ችግሮችንም ታመጣ ነበር፡፡
እንዲሁ ደግሞ የአገራችንን ልማት፣የድህነት ቅነሣ የበሸታን ማስወገድ፣
የጦርነትን በሰላም መተካት…… ሁሉ ትናንት መልካም ጅማሬ ሊኖረው ይችላል፣ ይህ ግን አስተማማኝ አይደለም በአገር ጉዳይ ተዘናግተን
ሌላ ነገር ላይ አትኩሮታችን ከተሰረቀ በግለሰብ ጉዳይ ላይ ከደረግን አርን ወደኃላ ልናስቀራት የትናንት ታሪካችንን ልንደግም የህዝቡን
የረጅም ዘመን ናፎቆት ተስፋ ልናጨልምበት ነው ማለት ነው ይህን ድህነት ጐልማሣውን በጐረምሣው ጥረታችን ታሪክ እናድርገው እስኪ
ጠቅለል አናድርገው የአይናለምንና የአዲስህንፃን የበረኛነት እኔ ነኝ
እኔ ነኝ የአገርን ድል ለማስጠበቅ የነበረ ትንቅንቅ መቃኘት ይቻላል፡፡ በረኛችን ደማል ተጐድቶ ከሜዳ መውጣት እንዳለበት አሠልጣኝ ሠውነት ቢሻው
እንደሰማ ዓይናለም በረኛ መሆኑን ከዚህ ቀደም በነበረው ታሪኩ ያውቀው ስለነበር ጓንት አጥልቆ ማልያ ቀይሮ ካጠናቀቀ በኃላ አዲስ
ህንፃ በልበ ሙሉነት በመምጣት እኔኮ በበረኛነት አሪፍ ነኝ በመለት ክፍተቱን ሊሞላ ዝግጁ መሆኑን ለሠውነት ይነግረዋል፣ ሠውነትም
በቃ አንዴ መድቤአለሁ አላለም ተነጋገሩበት ብሎ አድሉን ለተጫዎቶቹ ሠጠ ዓይናለም ከእኔ አዲስ ይበልጣል በማለት ማልያውን አወለቀ
ተጫዎቶቹን አዲስን ደገፋ ጨዋታውን ቀጠሉ በድል ተጠናቀቀ፡፡
ይህ አጋጣሚ በአሜሪካ የኘሬዘዳንታዊ ምርጫ በ2001 ዓ.ም. ሲካሄድ የነበረውን
ቅስቀሳ ለኘሬዘዳንትነት ዕጩ የነበሩት ማኬይ ከእኔ ባራክ ኦባማ ይበልጣል በማለት ከግል ሥልጣን ይልቅ አሜሪካንን
አስቀድመው ነበር፡፡ ዓይናለምም ከእኔ አዲስህንፃ ይበልጣል በማለት
ታሪክ ደገመ፡፡ ኢትዮጵያን በመጪው ዘመን ታሪኳን ለመቀየር ዉጤታማ
ለማድረግ ፍቅር እንጂ ፀብ አይጠቅማትም አንተ ትብስ አንች ትብስ ከኔ አንተ ትሻለለህ አንተ ትክክል ነህ መባባል አንጂ መናቆር
የጐሪጥ መተያየት የትም አያደርሳትም እንደ ዓይናለም ያ ተጫዎች፣ መሪ፣ የፓለቲካ አራማጅ፣ የሃይማኖች ሰባኪ፣ የለውጥ አርበኛ፣
ኢንቨስተር፣የመንግሥት ሠራተኛ፣ አባወራና እማወራ …..ወዘተ ነው የሚያስፈልጋት የግል ክብር ማድመቂያ ማለያችንን አውልቀን፣ የሥልጣን
ዘመናችንን በቃ ብለን፣ ከተቆናጠጥነው መድረክ ወርደን ማይኩን ለሌላ በማቀበል ከአኔ ወንድሜ/እህቴ ይሻላል ትሻላለች፣ ከዚህኛው
የፓሊተካ ፖርቲ ይኸኛው ይልቃል ከዚህኛው ያኛው ይሻላል እርሱ ስልጣኑን ይረከብ እኛ ደግሞ በመደገፍ አብረን እንስራ ልንል ይገባል፡፡
የህዝብን ድጋፍ ሳይዙ ሥልጣን ለመቆናጠጥ መጣር፣ በራስ መተማመንን ሣይዙ ለሥልጣን መደናበር በቃ ህዝቡን የልማት ሠራዊቱን በተለያዩ
ነገሮች ማደናቀፍና ማሸማቀቅ ጣልቃ ገብነት ይቁም እንደ ሠውነት ቢሻው ራስን ዝቅ በማድረግ እናንተ በፍቅር አድርጉት ከእኔ አናንት
ትሻላላችሁና፣ ጉዳዩ የጋራችን ነውና በማለት ድሉን በፍቅር የሚያደምቅ መር፣ ባለሥልጣን፣ የሥራ ኃዥለፊ፣ የቡድን መሪ ያሻናል፡፡
ከእንግዲህ ኢትዮጵያን በጦርነት በአንባገነንነት እኔ ብቻ አውቅለተለሁ በሚል መንፈስ መምራት ሊያከትም በፍቅርና በህብረት የምንመራበት የምናስተዳድርበት ሰዓት ነው ይህን የሚደግፍ
ማልያውን አውልቆ ለሚሻለው ብቁ ለሆነው ይስጥ፡፡
ጆሮ ያለው ይስማ ልብ ያለው ልብ ይበል ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!፡፡
ጆሮ ያለው ይስማ ልብ ያለው ልብ ይበል ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ