በአዲስ
አበባ ከተማ ሲኖሩ ከመጠለያ ችግር አስከትሎ የትራንስፖት ችግር ደረጃውን በመቀጠል ይይዛል፡፡ የመኖሪያ ችግር ዛሬዛሬ መንግሥት
እየሰራ ካለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሻገር የተለያዬ ሪል እስቴቶች ችግሩን ለመቅረፍ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ቢገኙም በመዲናይቱ የተለያዬ
አቅጣጫ የሚገኙ አከራይና ተከራይን በማገናኘት የሚተዳደሩ “ደላላዎች” የመኖሪያ ችግሩን እያጦዙት ይገኛ፡፡ ይኽንንም ችግር ከዕለት
ወደ ዕለት እያባባሱት የሚገኙት ርህራሄ በጎደለውና ሰብአዊነት በራቀው ተግባራቸው ተከራይን በየጊዜው ከተከራየበት ቤት ለአከራይ
ሻል ያለ ክፍያ ነገር ግን የተቸገረ ተከራይ ሻል ያለ ክፍያ እንዲከፈል በማድረግና አከራይን በጥቅም በማማለል ችግረኛውን ተከራይ
ገንዘቡን ከፍሎ እስከ ቤተሰቦቹ እንዲጉላላና እንዲሰቃይ ያደረጉታል እቃውን ተሸክሞ ላይ ታች ሲል ዘመኑን ይፈጃል መላው ቤተሰብ
እግዚአብሔርንና መንግሥትን ሲያማርሩና ሲወቅሱ ይኖራሉ፡፡ ይሁን እንጂ እ/ርም መንግሥትም ዝም ያሉ ይመስላ ነገር ግን ሁለቱም ያልታየንን
ብዙ ነገር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ መንግሥት ካለበት የዜጎች ኃላፊነት አንፃር አስፈላጊውን የአከራይና የተከራይ፤ የአከራየነ የደላ፤
የደላላ እና የተከራይ….. ግንኙነትን በተመለከተ ህግ ሊያበጅ ቁጥጥሩንም ቢያጠናክር የተሻለ ነው እላለሁ ምክንያቱም በመንግሥት ሥራ ላይ ተቀጥረው የሚገኙት ተከራይተው
ነዋሪዎች በየጊዜው ቤት በለቀቁ ቁጥር ለሚከራይ ቤት ፍለጋ የሚያባክኑት ጊዜ ዞሮ ዞሮ ከመንግሥት የሥራ ሰዓት ላይ ነውና፡፡ አንድም
ችግሩን ሽሽት ራቅ ብለው ሲከራዩም ከዚህ ተነስተው ወደ ሥራ ገበታቸው በሚጓዙበት የዕለት ዕለት የሥራ ሠዓታቸው አርፍደው የሚገቡት
ሲሰላ የባክነውና የሚሰረቀው ጊዜ የመንግሥት የሥራ ሰዓት ነውና፡፡ በሌላ ጎኑ ከተመለከትነውም በአከራይ በተከረይና በደላላዎች መካከል
እየተፈጸመ ያው መጨካከን መቸስ አገር ሰላም ለሕብረተሱም ፍቅርና አያዳብርም ፍፃሜውም ሠላምና ፍቅር አይጠፋ በሄደ ቁጥር ለመንግስት
ትልቅ የራስ ምታትና የቤት ስራ ይሆንበታል ስለዚህ መንግሥት የመጠለያን ችግርና የዳላሎችን ከመጠን ያፈ ሥገብግብነት አጥብቆ ሊከታተለውና
መጠን ሰፊ ስራን ሊሰራበት ግድ ይለላ፡፡ ከዕለት ወደ ዕለት የተከራይ
መጠን እየጨመረ እየሄደ ነውና መጨካከኑም የዚያኑ ያህል ጨምሯልና፡፡
ከመጠለያ
ባሻገር የትራንስፖት ችግር ዓብይ ጉዳይ ነው ይህ ደግሞ ተከራይንም
የቤት ባለቤቶችንም ደላላውንም ሥራ ያለውንም የሌለውንም ተማሪውንም የቤት እመቤቶችንም ሁሉ ያካተተ የማኀበረሰብ የዕለት ተዕለት
ሳይሆን በየደቂቃዎቹ የሚፈጠር ችግር ነው መንግሥት ችግሩን በደንብ ተመልክቶት የባቡር ትራንስፖርትን እንደ መፍትሔ አስቀምጦ እየሰራ
ቢሆንም እስከ አሁን በተደረጉ በግሉ ዘርፍም ይሁን በመንግስት በኩል እተደረጉ ያሉት ጥረቶች አመርቂ ውጤት ሊያመጡ አልቻሉም፡፡
የከተማ አውቶብስ (አንበሳ).፤ ሚኒባሶች፤ ሀይገር (ሚዲባስ)፤ ባጃጆች፤ ጋሪዎች ፤ የተለያዩ የሠራተኛ ሰርቪሶች…… ወዘተ ብዙ ጥረዋል ደክመው ከመሸነፍ በስተቀር ችግሩን
ሊቀረፉት አልቻም፡፡ ከእጥረቱምባሻገር ከጥቂት ጊዜወዲሀ እንደ መፍትሄ የቀረበው የስምሪት ስራ ችግሩን አባብሶታል የሚሉ ጥቂቶች
አይደሉም፡፡
ከምንም
በላይ ጠዋትና ማታ በሥራ መገቢያና መውጫ ሠዓት ችግሩ በጣም ጎልቶ ይታያል ወቅቶች ሲቀያየር ደግሞ ችግሩን የባሰ ጎልቶ እንዲወጣ
ያድገዋል በተለይ ክረምት ሲመጣ፡፡ በመጠለያም ሆነ በትራንሰፖት ችግር ተጠቂዎች ውስጥ አንዱ እኔ ነኝ፤ የተለያዩ ችግሮች ሲገጥሙኝ
የተለያዩ ገጠመኞችም እንዲሁ አስተናግዳሁና ከዕለታት በአንደኛው ቀን ያጋጠመኝን የትራንስፖት ላይ ገጠመኝ እነሆ!
ከስራ
ወጥቼ ወደቤቴ በመሄድ ላይ ነኝ አንደኛውን ትራንስፖት ተጠቅሜ የሚቀጠለውን በመጠባበቅ እገኛለሁ ወቅቱ ክርምት ስነበር ሰዓቱ ገና
ቢሆንም ጨላሟል በዚህ ላይ ከባድ ዝናብ እየመጣ ስለሆነ ጨለማውን እጥፍ ድርብ አድርጎታል፡፡ ለዓይን የሚታይ የትርንስፖርት መገልገያ
አንድም መኪና አልነበረም የትራንፖርት ፈላጊና ጠበቂ ቁጥ ግን በየደቂያቆቹ ልዩነት ይጨምራል፡፡ ለትራንስፖርቱ መጥፋት ምክንያት
ይሆናል የሚለውን ግምት ከተሳፋሪዎች ብዙ ብዙ ነገር ይሰማል ነዳጅ ሊጨምር ስለሆነ ነው የጠፉት፣ ታፔላ ስለሚቀይሩ ነው ጾም ስለሆነ
ነው…..ወዘተ ጊዜውም እየገፋ ነው ሰውም ከመጠን በላይ ጨምሯል ድንግት
“ልዬ” የሚል የከተማ አውቶብስ ከየት መጣ ሣንል ከፊታችን ተገተረ ያለወትሮው የታክሲዎች መጫኛና ማውረጃ ቦታ ላይ መጥቶ ሲያቆም
ለሁለታችንም መገረምን ፈጥሮብና፡፡ ይህ ጉዳይ የኛ ስላልነበረ ሁላችንም ወደ ትኬት ቆራጩ እጃችንን ዘረጋን ሁለት ብሮችን ከኪሳቸን
እየመዘዝን አንዳንድ ብራችንን እና ትኬታችንን ይዘን ወደ ውስጥ አመራን አንድ ብር ነበርና፤ ያለማጋነን ያ የከተማ አውቶብስ ከመቶ
በላይ ሠዎችን በውስጡ ይዟል ያለውን መጨናነቅ የሠውን በሠው ላይ መረማመድና መገፋፋት መግለፅ ይከብዳል፡፡ ደቂቃዎች እየጨመሩ በሄዱ
ቁጥር ትንፋሸ እያጠርዎት ይሄዳል፡፡ ገና መኪናው ጭኖ ሳይጨርሽ ትንፋሽ አጠረኝ መቆም አቃተኝ መውደቅ አማረኝ አስጠግቶ የሚያስቀምጠኝ
ሰው በዓይኔ አማተርኩ ማን ሠው ና! ቁጭ በል ይበለኝ መባልም ካለበት ከኔ በዕድሜ የሚልጡ አባቶችም እናቶችም ብዙ ናቸው ሆኖም
ግን የኔ ድካምና መዛል አቅም አሳጣኝ ጥርሴን ነክሼ ሃሳቤን ወደሌላ ቦታ ወስጄ ቆሚያሁ የሆነ እጅ ሲናካኝ ታወቀኝ ዐይኔን ወደ ነካኝ እጅ ወርወር አደረኩ አንዲት ወጣት ልጃገረድ
እየተጠጋች እንድቀመጥ ጋበዘችኝ ብቻዋን ተቀመጠችበት የአንድ ሰው
መቀመጫ ወንበር ላይ አልተግደረደርኩም ለማንም ዕድሉን አልሰጠሁም ፈጥኜ ተቀመጥኩ ከዚያ በኋላ ያለውን ልንገራችሁ አልችለም በጣም
ደስ አለኝ ፊቴ ላይ ያለውን የደስታ ፀዳ በቃላት መግለጽ ከምቸለው በላይ ነው፡፡
መልስ
ብዬ ታክሲ ከምንጠብቅበት ሥፍራ ህሊናዬን ላኩት እስከ አሁን እዚያው ብቆምስ አልኩኝ አሁን ከተቀመጥኩ በኋላ ያለውን ቀሪ ድካሜን
እያስብኩ፡፡ የኔን ድካምና የሌሎችንም ድካም አሰብኩ ዘወር ብላ ተመለከተችኝ የምንተ ፍረቴን “አመስግናሁ” አልኳት፡፡
“ለምኑ
ነው ምስጋናው ?”
“ሥላስቀመጥሽኝ!
በኋላኮ
ለቅቄው እወርዳለሁ!?
ቢሆንም
ይህንንስ ማንስ አስቦ ያደርገዋል
“ደስ
አለህ ማለት ነው ያደረኩልህ ነገር”
አዎ!
በጣም …. አልኳት፡፡
“ደስታውን
እስኪ አጣጥመው” አለችኝ ግራ ቢገባኝም ወደ ማጣጣም ሄድኩኝ ድካሜንና ደስታዬን ተመላለስኩበት ይበልጥ ከድካሜ መበርታቴን ፤መቀመጫ
ማግኘቴን፤ ቀንንቷን፤ ጥሩ አሳቢነቷንን ባደረገቸውመልካም ነገር አለመመፀደቋን፤ ….. ሁሉ አሰብኩ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ሆነ መልካምነትን
አስተማረችኝ፡፡
“አጣጣምከው?”
አዎ!
“በጣም
ደስ ብሎሀል?”
አዎ!
“ደስታ
ምን ያህል ደስ እንደሚል አየኸው?”
አዎ!
“ሠው
ማስደሰትስ ምን ያህል ደስ እንደሚል ታውቃለህ?”
በጭራሽ
አስቤው የማላውቀው ነገር ለነበር ግራ ገባኝና ማሰብ ጀመርኩ የማውቀውን ነገር መመለስናመዋሸት አልፈልኩም ዝም አልኳት
“አትጨነቅ
እኔ እነግርሃለሁ በጣም ደስ ይላል ከሠው ከምታገኘው ደስታ የበለጠ ደስታን ታገኝበታለህ እኔ ባደረኩልህ ጥቂት ደስታ ከልብህ ተደስተህ
ከሆነ አንተም እንደዚሁ አድርግ ያኔ እውነተኛውን ደስታ ትደሰታለህ”
አንተም
እንደዚሁ አድርግ አንተም ….ደጋግሜ ለራሴ ነገርኩ የበለጠ ማብራሪያ የህይወት ተሞክሮ ፈለኩኝ ምን ላድረግ?
“አየህ
የማያውቁትን መጠየቅ፤ ምን ማድረግ እንዳለብን ማወቅ ብልህነት ነው፡፡ ከምናውቀው ጥቂት እውቀት የማናውቀው ብዙ ነገር ነው ህይወታችንን
የሚጐዳንን መምህራችን መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ሲመላለስ የአገሩ ሠዎች ሥለራሱ ማወቅ መሥማት አይፈልጉም ነበር
የእጅን በረከት ማየት የቃሉን ትምህርተ መሥማት አይፈልጉም ነበር፡፡ እናውቀዋለን የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ እይደል እናቱሰ ማርያም
አየምተባለዋ አይደለች ይሉ ነበር…. እናውቀዋን ይላሉ አንጂ አያውቁትም ቢያውቁትማ ኖሮ አዳኝነቱን አውቀው ይከተሉት ነበር፣ እውነተኛ
መምህርነቱን አውቀው የቃሉን ትምህርት ተከትለውት ይማሩ ነበር፣ አድርጎ የተባሉትንም ያድርጉ ነበር፤ …… እንኳንስ ቀርበው ያልተማሩ
ሲማሩ የነበሩት የእጁን በረከት የተቋደሱት እንደ ይሁዳ ያሉት ገና አላወቁትምና ሸጡት፣ አሳልፈው ሰጡት የዘለዓለም ህይወትን በሞት
ለወጡት፡፡ እርሱ ግን በመጨረሻው ሳምንት የእውቀትን መጨረሻ ሲያስተምራቸው
እግራቸውን አጥቦ ሲያበቃ……” እናንተም እርስ በርስ እንዲህ አድርጉ” ብሎ አስተማራቸው እውቀት የሚለካው በተግባር ነውና እኔም
እንደዚሁ አንድታደርግ ነገረኩህ፡፡ እኔ ያደርኩልህን መልካም ነገር፤ ሠዎች ያድጉልህን መልካም ነገር፤ አምላክህ ያስተማረህን (ያደረገልህን)
መልካም ነገር ያለ አንዳች ዋጋ እንዲሁ ያለዋጋ (ውለታ) አድርገው ያኔ እውነተኛውን ደስታ በነፍስም በሥጋም ትደሰታለህና፡፡”
በሥሜት
ይሁን እውቀቱ ከልቤ ዘልቶ ገብቶ ይሁን እንጃ ትንሽ ፌርማታ ቢቀርም ከፊት ለፊቴ ቆመው የነበሩትን የዕድሜ ባለፀጋ እናት እንዲቀመጡ
ተነሳሁላቸው እያመሰገኑኝ እየመረቁኝ ተቀመጡ መምህሬም ተነሰችላው የበለጠ እንዲመቻቸው አሁንም ወደጆሮዬ ቀርብ ብላ “እውነታኛውን
ደስታ የበለጠ አሁን ታገኘዋለህና አጣጥመህ ልዩነቱን ንገረኝ፡፡” ደግሜ ደጋግሜ አጣጥምኩት ልዩነቱን ተመለከተኩት ልዩነቱ የሰማይ
እና የምድር ያህል ነበር፡፡ “እንዴት ነው?” አለች መልስ አልነበረኝም መግለጫ ቃላት አጣሁ ምን እንደምላት ግራ እየተጋባሁ እያለሁ
“አየኸው አይደል ልዩነቱን ጣዕሙን ለየኸው አይደል? ከኔ ያገኘኸውን ደስታ በቃላት ገልፀኸዋል ከራስህ ያገኘኸውን ደስታ ግን የሥራህ
ውጤት ሥለሆነ መግለጽ ከበደህ?”
“በጣም
ትልቅ ትምህርት ነው ያስተማርሽኝ በጣም ነው የማመሰግነው”
“መማር ከፈለክ የሁላችን መምህር እግዚአብሔር በህይወት ዘመንህ በሙሉ ያስተምርሃልና
እንደ ሣሙኤል “ባሪያህ ይስማልና ተናገር” በለው ይነግርሃል”
የፌርማታው
መጨረሻ ላይ ደርሰን ሥለነበርን ወረደች እኔም ወረድኩ ሠላምታ ተለዋውጠን ተለያየን ከዓይኔ እይታ ርቃ እስከምትሰውር ድረስ ቆሜ
በአይኔ ሸኘኋት ገና ወጣት ነች ግን በሳልና አስተዋይ ዕድሜዋን ለቁም ነገር የተጠቀመችበት አንድ ነገር አስታወስኩ “Be a
man of your age” የእድሜህ ሰው ሁን! የዕድሜ ሠው መሆን እንደዚሁ ነው ምን ዋጋ አለው የእድሜን ዘውድ በእናታቸው ላይ
ደፍተው የማያስተውሉ የጉብዝና ዘመን ጠንካራ ጉልበት ይዘው የሚዝሉ በሞሉባት ዓለም እንዲህ ዕድሜን መጠቀም ሲቻል ደስ ይላል፡፡

God bless Ethiopia!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ