ይሕ ፅሑፍ ጳጉሜ 3/2004 ዓ.ም. የተጻፈ በመሆኑ የተፈጠሩ ስሕተቶች ግምት ዉስጥ ይግባልኝ!
“የምናብ ለውጥ”
ክቡር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ በተጠባባቂነት የሚሰሩበትን የጠቅላይ ሚኒስተርነት በትረ ሥልጣን በቃለ መሐላ ሙሉ በሙሉ ሲረከቡ ያደርጉታል ተብሎ ከሚጠበቀው ንግግር መካከል አንዱ፡-
ክቡር የኢፌዴሪ መንግሥት ኘሬዜዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ክቡር የኤፌዴሪ መንግሥት የተወካዮች ምከር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ክቡራት ሚኒስተሮችና አምባሰደሮች እንዲሁም የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ክቡራን ጥሪ የተደረገላችሁ የውጭ አገር አምባሳደሮች ኮር ዲኘሎማቶች የሐይማኖት መሪዎች የአገር ሽማግሌዎች የተቃዎሚ ፓርቲ ተወካዮች ከሁሉም በላይ እጅግ የማከብርህና የምወድህ ልታዘዝህና ላገለግልህ በዛሬዋ ዕለት በቃለ መሐላ አረጋግጨ በትረ ሥልጣኑን የተረከብኩህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡፡
በየአላችሁበት የእግዜአብሔር ሠላም ይብዛላችሁ፡ ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና እኛ ህዝቦቿን ይባርከን!
Yes We Can Change!
Yes we can!
Yes we need change !
“ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ አዎ መለወጥ እንችላለን! መለወጥ ያስፈልገናል፡፡”
የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ለብዙ ዘመን ለረጅም ወራት ሥትረገጥ ሥትጨቆን ብትኖርም ኢህአዴግ የድልን ካባ ከተጐናፀፈ ማግሥት ሥትናፍቅ የኖረከውን ያንን ነፃነት፣ ዕድገት ፣ ብልፅግና ሰላም……..ለማምጣት ድፍን ሁለት ዓሥርት ዓመታት አልፈውታል፡፡ ይህንንም ግሥጋሴ በፅናትና በትጋት ሲመሩት የነበሩት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትራችንን በሞት ቢለዩንም ይኸውና ዛሬ በህይወት ዘመናቸው የቀረፁኝ የመንፈስ ልጃቸው ተተክቼ በትረ ሥልጣኑን ተረክቤአለሁ ፣ ቃል የምገባልህ የተጀመረውን ማስቀጠል እንደምንችልና ለውጥ ማምጣት እንደምንችል ነው፡፡
ክብራትና ክቡራን ሚኒሰተሮች፣ የፓርላማ አባላት በየደረጃችሁ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጥያቄ አለን የመለወጥ ዓላማ አለን ወይስ ዓላማችን ምንድን ነው መለወጥ መለወጥ ሥላችሁ /አንዴ ለ ን አጥብቃችሁ እንዴ አላልታችሁ ይሁንልኝ/ መቀየር /ማሳደግ/ ቀ ን አጥብቋት መቀየር /ማደግ/ / ቀ ን ላላ አድርጓት /ያለብን ይመስልኛል ይመስለኛል አይሰራም መቀየር ወይም መቀየር አለብን፡፡
ዓለማችን መለወጥ ማስተካከል ወይም ማስተካከለ ካልሆነ የእኔ የለውጥ ሂደት በእናንተ የመለወጥና/ የመለወጥ አስተሳሰብ ካልታጀበ የእኔ ዕቅድ የእናንተም የጋራችን ካልሆነ የእኔ የለውጥ ሂደት ጎምዛዛ እና ደብዛዛ ይሆናል፡፡ ለዘመናት የእኛን ለውጥ ሲጠብቅ የኖረው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ መና ይሆናል የእኛም ዕጣ ፈንታ በታሪክ ተወቃሾች መሆን ነው፡፡
ክብራት ሚንስተሮች ክቡራን የፓርላማ አባላት ለውጥን ለማምጣት የምንችለው ሰውን በማምጣት ሰውን በመቀያየር ብቻ አይደለም ፓሊሲዎቻችን አፈፃፀምቻችንንም መፈተሽና መቀየር ግድ ይላል የማንቀይረው ሰው የማንቀይረው ፓሊሲ የለም ሁሉም ይቀየራለ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እኔም እቀየራለሁ መንግሥታችንም ይቀየራል፡፡ የሄድንበት መንገድ ትክክል አይደለም አያዋጣም ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሣይቀሩ በሚያመጡት መልካም ኃሳብ ፈትሸንና አስተካክለን እንጓዛለን ማለት አለብን፡፡
እንደ እህአዴግም የተጓዝንበት መንግድ ትክክለ ነወይ እንደ መንግሥትስ የቀየስነው ዓላማ ጠንካራ ነው አፈፃፀማችንስ እንዴት ነው ብለን ራሳችንን እስከ ታችኛይቱ የቀበሌ እና የጎጥ ጽ/ቤት ድረስ ልንፈትሽ አገራዊና ህብረተሰበአዊ ግዴታችን ነው ደካማ ጐናችንን ማመኑ ጥፋታችንን መረዳቱ የለውጥ ሂደታችን አንዱ አካል ነውና፡፡ ግትርንት አይሰራመ ለአገራችን ለኢትዮጵያ እኔ ብቻ አውቅለታለሁ የምንልበት ዘመን አብቅቷል የበረሃ ታጋይነት ብቻ በቂ አይደለም ከፈቃደ ሥጋችንና ከያዝነው የዛፍ ላይ እንቅልፍ ሥልጣናችን ጋር ልንታገል ግድ ነው፡፡
የማከብራችሁ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የምወዳችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆይ እኔ ዛሬ ከፊታችሁ ቆ ሜ ቃለ መሐላ የፈፀምኩር ኩራት አይደለም የሚሰማኝ ሥጋት እንጂ ይህን ሥጋቴን ዳግመ ወደኩራት መለወጥ የምችለው ከፊታችን ባስቀመጥንው ሶስት ዓመታት ውስጥ በሥራ እና በለውጥ ነውና እናንተን ከእኔ ጋር በመሆን አብረን ከእርሱ ጋር እየሠራን እንየው እንለወጥ ልትሉ ይገባል፡፡
መንግሥት መሥርተን በጋራ የምንሠራ በተለያየ የድርጅት አባልነት ያለን አለን በአጋር ድርጅትም ታቅፍችሁ ያላችሁ ሳስገነዘባችሁ የምፈልገው አንድ ጥብቅ ጉዳይ አለ፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚናገሩትን ከእንግዲህ ልንሠማ ቦታም ልንሠጣቸው ግድ ይለናል ልንለውጣት ለቆምንላት አገራችን ኢትዮጵያ እንርሱም እንደዜጋም ይሁን እንደተቃዋሚ የለውጥ አጋሮቸችን ቻውና፡፡ ወሀትመ ለአገር ለውጥና እድገት ለሠዎች ልጆች ሠላምና እኩልነት የሚሠጕ የካበተ ልምድ ካላቸወ ተለውጠው ከመጡ የደርግ ባለሥልጣናት ሣይቀር በህይት ካሉ በንጉውም ዘመን ያሉ ካሉ እንቀበላለን”፡ ያቋቋምነው ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ምህደሩ እዚህ ድረስ ሠፈና ጥልቅ ነው፡፡
የተከበራችሁ የምክር ቤት አባላት ባለፋት የሁለት ዓመት የዚህ የምክር ቤት የሥራ ዘመናችን የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሚዲያዎች በሥራችን ላይ ምስጋና ነው ወይስ ወቀሳ ነው የሚያቀርቡት ክስ ነው ወይስ እርካታ ነው ያላቸው ምንድን ነው እየተሰማ ያለው ሰማንያ ሚሊዮን የኢትዮጵያን ህዝብ እንደመወከላችን መንግሥታችን ዲሞክራሲያዊ እንደ መሆኑ መጣን ምን መረጃ አለን እኛስ ምን መስራታችንን ነኁወ የምናውቀው እንደ አንደ ግለሰብ እንደ አንድ ኢትዮጵያዋና የምክር ቤት አባልነቴ ምን አስተዋፅኦ አድርጌአለሁ ብለን ራሳችንን ፈትሸናል ይህ ቀን ግን ራሳችንን ቆም ብለን የምንፈትቨበት ቀን ነው፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝና የምክር ፀበት አባላት በሙሉ አንድ ግዜ ከመቀመጫችሁ ብድግ በሉልኝ አመሰግናለሁ በዚያው እስኪ እጃችሁን ወደ ኪሶቻችሁና ወደ ገንዘብ ቦርሳችሁ ከታችሁ
ተመልከቷቸው /ጠቅላይ ሚኒስትሩም እጃቸውን ወደ ኪሳቸወ ከተቱ የገንዘብ በርሳቸውንም ፈተሹ የማን ገንዘብ ነው ኪሶቻችን ውስጥ ያሉት መልስልኝ ጉርምርምታ ነገሰ በአዳራሹ ጓዳች ፀጠታ መልሰን እኔ እመለሰዋለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው የኢትዮጵያ ሃብት ነው ለመሆነ ምን ያህል ሰርተን ነው ይህን ያህል የተከፈለን የፀዳ የላባችን ውጤት ብቻ ነው ኪሳችን ውስጥ ያለው በየግለ ሥማችን የተፃፋ የገንዘብ ማዘዥ ቼኮች የሉም በኪሳችንና በቤታችን ጐበዝ በቃ አካሄዳችንን እንገምግም ችግር ካለብን በቃኝ ተነቅቶብኛል የጀመርኩር መንገድ አያስቀጠልኝም በማለት የለውጡን ጉዳና ለመቀላቀል የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ እንጠይቅ በአገሪቷ ላይም እርቀ ሰላም እናውርድ፡፡
ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ የፓለቲካ ድርጅቶች የሃይማኖት ተቋማት፣………ወዘተ ሁላችሁመ አንድ የጥሪ መልዕክት አለን እንደማመጥ መስማት ወይመ ማዳመጥ ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች ውስጥ አንድ ነውና፡፡መደማመጥ ለመንግሥታችን ፋይዳው ከዚህ በላይ ነው ለለውጥ የተነሳ ትውልድ አዳማጭ ካጣ ልፋቱ በጠቅላላ ዋጋ ቢስ ይሆናል ስለዚህ ለዚህ ለውጥ መሳካት መዳመጥም ሆነ ማዳመጥ ትልቁን ሥፍራ ይይዛልና እንደማመጥ ሰዎች በየእመነታቸው ወደ ፈጠረን በፀሎት የምንጨኸው የፈጠርን ይሰማናል ያዳምጠናል መልስም ይሰጠናል ያሰብነውን ያለምነውን ያቀድነውን ያሳካልናል ብለንኮ ነዉ ታዲያ ትልቅ ራዕይ ሰንቀን ረጅሙን ጐዳና ከፈታችን አስቀምጠን ሳንደማመጥ እንዴት ይሆናል፡፡
ምንም እንኳን ለውጣቸው እስከዚህም ቢሆን የድሮ ነገሥታት (መሪዎች) የህዝባቸው የልብ ትርታ ለማዳመጥ ‘’እረኛው ምን ይላል’’ እሰከ ማለት ታች ድረስ ወረደው ያዳምጡ ነበር፡፡ ታዲያ መደማመጥ ክፉ ነገር ከሌለው ለዚያውም በመረጃ መራብ ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ለምን አንደማመጥም? መዳማመጥ አለብን፡፡ አለቃ ምን ይላል? ብቻ ሣይሆን ወደታች በመውረድ ሠራተኛው፣ ህዝቡ፣ ደጋፊው፣ ተቃዎሚው ምን ይላል? ማለት ይገባል፡፡ ህዝቡ ዝም ካለ አደጋ ላይ ነንና ባለፋት ሥርዓት እንዲሁም በኛም ዘመን የሚናገሩ ብዙዎች የሚያዳምጡ ጥቂቶች በመሆኑ መፍትሔ እና ለውጥ ሣይመጣ ቀርቷል፡ ዛሬ ግን ያ ዘመን ይብቃ! መስማት (ማዳመጥ) የመፍትሔው ዋነኛ ቁልፍ ነውና የተከበራችሁ ሚኒስተሮች ማዳመጥ ከማይችሉ መሪዎች ጋር የሠራ ሠራተኛ የመደማመጥን ባህል ማዳበር አይችልምና መደማመጥን ባህላችን እናድርግ ብዙ ሥናዳምጥ ብዙ መረጃ ይኖረናልና፡፡
የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ይብዛም ይነስም ይህቺን አገር በድለናታል፣ ተበዳይ ደግሞ ካሣ ያስፈልገዋልና ይህ ጊዜ ምንም አጭር ቢሆንም ባለን አጭር ጊዜ አገራችንንና ህዝባችንን የምንክስበት እንጂ የምንከስበት ሰዓት ላይ አይደለም ያለነው ምን ያህል ነው ያጠፋሁት ሣይሆን ጥፋቱ መኖሩን ማመን የጥፋቱ ምክንያት እኛው መሆናችንን ማመን በራሱ አንድ የለውጥ መጀመሪያ ነው ሌላው ዓብይ ጉዳይ የሚያጠፋትን ሠዎች ለመቅጣት ሥንል የምንዘረጋቸው መንግዶች በአገራችን ላይ ቂም እና በቀልን እንዳያሠፍኑ የተቀጣው ሠው ተምሮ ወደ ማኀበረሰቡ ተቀላቅሎ ልማትን እና የዕድገቱን ለውጥ የሚያፈጥንበትን መንገድ ልንቀይስ ይገባል፡፡ በዘመናችን ሠዎች የሚቀጡበት የእስር ቤት ግንባታዎችን ከማስፋፋትና የሌለንን የሠው ኃይል ለዓመታት በአንድ ቦታ ያለ ጥቅም ከማዋል አስቀድመን ሠዎችን ከጥፋት ማራቁ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው ስለዚህ በዚህ የሶስት ዓመት የሥራ ዘመናችን እንዚህ እስር ቤቶች የልማት ሀይሎች መፍለቂያ ማድረግ አንዱና ዋነኛ ሥራችን ይሆናል ሌላው አገራችን በፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች ብቻ የምትመራ ሣትሆን በፍቅር በዕድገት እና በለውጥ ጐዳና የምንመራት ኢትዮጵያ መሆን አለባት፡፡
ወገኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ተከፋፍሎና ተቃቅሮ መኖር ከዚህ ቀደም በቅርበት ያየናቸው የአፍሪካ ህዝቦች ታሪክ ብዙ ነገር ያስተምረናል ብዬ አስባለሁ የተደረጉት ክፋ ድርጊትና ብቀላዎች አህጉሪቷን ለልማት አላነሳሳትም ከጥፋትና ከረኃብ፣ ከበሽታና ፣ ከእርሰ ብርስ ጦርነትና ኃላቀርንት፣ ከትውልድ እልቂትና ከመበታተን / ከስደት/ አልታደጋትምና ከዚህ ክፋ አጋጣሚዎች የመለያየትንና የክፋትን ነገር ልንማርበት ይገባል፡፡ ከቂም እና ከበቀል ይልቅ ታሪካችንን በዕርቅ የምንቀይር ታሪክ ሠሪዎች እንሁን፡፡ ትናንት የተሠራውን ጥፋት እና መጥፎ ታሪክ እየዘረዘርን የአጥፊውን ወገን በክፋ ዓይን ማየት ይቅር መካሰስ የትኛውን አገር ገነባ? የየትኛውን አገር ኢኮኖሚ አሳደገ?
ትናንትናን መለወጥ ባይቻል ከትናንት መማር ግን ይቻላል አይደል የሚባለው ከተስማማንና በግልጽ ከተነጋገርን በአንድነት እና በቁርጠኝነት ለእምዬ ኢትዮጵያና ህዝቧ ለህዝቧ ታሪክ ለመሥራት ዝግጁ ከሆንን ነገሮችን ሁሉ እንደምንፈልገው ማድረግ እንችላለን ታሪክ ለመቀየር ክፋ ነገሮችን ወደ በጐ ለመገልበጥ የተነሳን ከሆንን ህዝባችንና የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ከጐናችን ሆኖ ብርታትና ሞገስ ይሆነናል፡፡ በትናንት መጥፎ ታሪካችን ላይ ሥንጣላ ሥንጨቃጨቅ ጥሩው ቀን ዛሬ ግን እንዳያልፍብን ጥሬዬን አቀርባለሁ፡፡
ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝቦችን ብሔር ብሔረሰቦች ዛሬ የምንተራረምበትና ጥሩ ሥራ ለመሥራት የምንመካከርበት ቆርጠን የምንነሳበትና ቃል የምንገባበት የለውጥ ብሥራት ዕለታችን ናት ፣ ከመላው የእትዮጵያ ህዝቦች ብሔር ብሔረሰቦች ልቡና ልትጠፋ የማትችል ተከባብረንና ተዋደን ልንኖርበት ቃል የምንገባበት የደስታ ቀን ናት ተራርመን ጥሩ ሥራ መሥራት የማንችል ዜጐች ካልሆንን እንደ ህዝብ ብዛታችን እና ብዙ የብሔር ብሔረሰብ ሥብጥር ውጤት እንደመሆናችንን መጠን ትናንት የነበሩት ካጠፋት፣ ሌሎችም የአፍሪካ አገራት ላይ ከጠፋው ጥፋትና ከደረሰው ውድቀት የከፋ ነገር ያጋጥመናል የበለጠ ነገርም ልናጠፋ እንችላለን፡፡ በውኑ የትናንትናዎቹን በምንወቅሳቸው ሚዛን ብንመዘን እኛ ምን የተሻለ ሥራ ሠርተናል እነርሱን ያጋጣማቸው ነገሮች ቢያጋጥሙን እነርሱ ካጠፋት የተሻለ ሥራ እንደምንሠራ ምን ማረጋገጫ አለን በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ሥናጠፋ ታግሶን ስናለማ አጋራችን በመሆን ከጐናችን ላልተለየ ህዝባችን ምስጋናዬና አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው፡፡
በመጨረሻም የተከበሩ የኢፌዴሪ ኘሬዘዳንት፣ የተከበሩ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ እና የተከበራችሁ የምክር ቤት አባላትና የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ባለፋት ሁለት ዓመታት የተጀመሩትን የልማት ሥራዎች ማስቀጠል እንዳለብንና ሌሎችንም ሥራዎች ማቀድና መተግበር እንዳለብን ላሳስብ እወዳለሁ፡፡ ይልቁንም ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከዳር ማድረስ እንዳለብን በአጽንኦት አሳስባለሁ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ እምቅ እውቀቱን ይዞ በተለያየ አጋጣሚ ጉልበቱን ጭምር ይዞ እንደ ዓባይ ለሌላው ዓለም ሲሳይ የሚሆነውን ህዝባችንን ልንታደገው እንደሚገባና እንደ ወንዛችን ዓባይ ሁሉ ከአባይ ወንዝ በላይ ጥቅም ያለውን ህዝባችንን በአንድነት ልንገድበው ይገባል፡፡ የዓባይ ወንዝ በገንዘብና በጉልበት ሊገደብ ይችላል ህብረተሰብ ግን በጉልበት አይገደብም በጥበብ እና በፍቅር እንጂ ስለዚህ አደራ የምለው በጥበብና በፍቅር በመከባበርና በመተባበር በስደት ላይ ያለውን በመሰደድ ላይ ያለውን እምቅ ሐብት ህዝባችንን ለእምዬ ኢትዮጵያ እናውለው እንገድበው!!!
በእኔ በኩል የሥደት ምክንያት የሆነውን በነፃነት የመኖር መሠረታዊ ነገሮችን፣ የሚዲያ እና የነፃ ኘሬስ ነፃነትን፣ የመንግሥትን በሀይማኖቶች ጣልቃ ገብነት ገለልተኛ መሆንና እና ሌሎችን በራሴና ከምክር ቤቱ አባላት ጋር ታምኜ ልሰራ እና ላገለግላችሁ እንድትሰሩ ላመቻችላችሁ ቃለ እገባለሁ ፡፡(ንግግሬን እዚህ ላይ አበቃለሁ በክብር ለህዝብ ጥቅም ከድል በኃላ ለተሰውት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መለስ ዜናዊ ከመቀመጫችን ተነስትን በድጋሚ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናድርግ፣ አመሠግናለሁ፡፡)
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !
ኢትዮጵያለዘለዓለምትኑር!
ክቡር ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለኝ እንኳን ለዚህ አበቃዎት!
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ኃ/ማርያም ቢሉ ኖሮ ጥሩ ነበር ለኢትዮጵያ ህዝብ፤ ለኢህአዴግ ግን ፣….
ምላሽ ይስጡሰርዝ