ቅዳሜ 29 ሴፕቴምበር 2012

መልካም በዓል


በመላዉ ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያን እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ  በሰላም አደረሳችሁ፡፡በጦማሩ ላይ ስለ ጦማሪው ያላችሁን አስተያየት በ e-mail:-lovelydere@gmail.com መላክ ወይም በፖስታ ቁጥር 25476 አዲስ አበባ ደረሰ ረታ በማለት መላክ ይቻላል፡፡አመሰግናለሁ፡፡ለተጨማሪ ንባብ
www.deressereta.blogspot.com ይጠቀሙ፡፡


ዓርብ 28 ሴፕቴምበር 2012

“የምናብ ለውጥ”


ይሕ ፅሑፍ ጳጉሜ 3/2004 ዓ.ም. የተጻፈ በመሆኑ የተፈጠሩ ስሕተቶች ግምት ዉስጥ ይግባልኝ!
የምናብ ለውጥ
ክቡር የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ በተጠባባቂነት  የሚሰሩበትን የጠቅላይ  ሚኒስተርነት በትረ ሥልጣን በቃለ መሐላ ሙሉ በሙሉ ሲረከቡ ያደርጉታል ተብሎ ከሚጠበቀው ንግግር መካከል አንዱ፡-
ክቡር የኢፌዴሪ መንግሥት ኘሬዜዳንት አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ክቡር የኤፌዴሪ መንግሥት የተወካዮች ምከር ቤት አፈ ጉባኤ  አቶ አባዱላ ገመዳ ክቡራት ሚኒስተሮችና አምባሰደሮች እንዲሁም የተወካዮች  ምክር ቤት አባላት ክቡራን  ጥሪ የተደረገላችሁ የውጭ አገር አምባሳደሮች ኮር ዲኘሎማቶች የሐይማኖት   መሪዎች የአገር ሽማግሌዎች የተቃዎሚ ፓርቲ  ተወካዮች ከሁሉም በላይ እጅግ የማከብርህና  የምወድህ  ልታዘዝህና ላገለግልህ በዛሬዋ ዕለት በቃለ መሐላ አረጋግጨ በትረ ሥልጣኑን የተረከብኩህ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡፡
በየአላችሁበት  የእግዜአብሔር ሠላም ይብዛላችሁ፡ ጌታ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና እኛ  ህዝቦቿን ይባርከን!

Yes We Can Change!
Yes we can!
Yes we need change !

“ የኢትዮጵያ ህዝብ  ሆይ አዎ መለወጥ እንችላለን! መለወጥ ያስፈልገናል፡፡”
 የተከበርከው የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ለብዙ ዘመን ለረጅም  ወራት ሥትረገጥ ሥትጨቆን  ብትኖርም ኢህአዴግ የድልን ካባ ከተጐናፀፈ ማግሥት ሥትናፍቅ  የኖረከውን ያንን ነፃነት፣ ዕድገት ፣ ብልፅግና  ሰላም……..ለማምጣት ድፍን  ሁለት ዓሥርት ዓመታት  አልፈውታል፡፡  ይህንንም ግሥጋሴ በፅናትና በትጋት ሲመሩት የነበሩት  ክቡር ጠቅላይ  ሚንስትራችንን በሞት ቢለዩንም ይኸውና ዛሬ በህይወት ዘመናቸው የቀረፁኝ የመንፈስ ልጃቸው ተተክቼ በትረ ሥልጣኑን ተረክቤአለሁ ፣ ቃል የምገባልህ የተጀመረውን ማስቀጠል  እንደምንችልና ለውጥ ማምጣት እንደምንችል ነው፡፡
     ክብራትና ክቡራን ሚኒሰተሮች፣ የፓርላማ አባላት  በየደረጃችሁ  የመንግሥት ባለሥልጣናት  ጥያቄ አለን የመለወጥ ዓላማ አለን ወይስ ዓላማችን ምንድን  ነው  መለወጥ መለወጥ  ሥላችሁ /አንዴ ለ ን አጥብቃችሁ እንዴ አላልታችሁ  ይሁንልኝ/ መቀየር /ማሳደግ/ ቀ ን አጥብቋት መቀየር /ማደግ/ / ቀ ን ላላ አድርጓት /ያለብን ይመስልኛል ይመስለኛል አይሰራም  መቀየር ወይም መቀየር አለብን፡፡
ዓለማችን መለወጥ ማስተካከል ወይም ማስተካከለ ካልሆነ  የእኔ  የለውጥ ሂደት በእናንተ የመለወጥና/ የመለወጥ አስተሳሰብ ካልታጀበ የእኔ  ዕቅድ የእናንተም የጋራችን ካልሆነ  የእኔ የለውጥ ሂደት ጎምዛዛ እና ደብዛዛ  ይሆናል፡፡ ለዘመናት  የእኛን ለውጥ ሲጠብቅ የኖረው መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተስፋ መና ይሆናል የእኛም ዕጣ ፈንታ በታሪክ ተወቃሾች መሆን ነው፡፡
ክብራት ሚንስተሮች ክቡራን የፓርላማ አባላት ለውጥን  ለማምጣት የምንችለው  ሰውን  በማምጣት ሰውን በመቀያየር ብቻ አይደለም ፓሊሲዎቻችን  አፈፃፀምቻችንንም መፈተሽና መቀየር ግድ ይላል የማንቀይረው ሰው የማንቀይረው ፓሊሲ የለም ሁሉም ይቀየራለ አስፈላጊ  ሆኖ ከተገኘ እኔም እቀየራለሁ  መንግሥታችንም ይቀየራል፡፡  የሄድንበት መንገድ ትክክል አይደለም አያዋጣም ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ህዝብ ተቃዋሚ ፓርቲዎች  ሣይቀሩ በሚያመጡት መልካም ኃሳብ ፈትሸንና አስተካክለን  እንጓዛለን ማለት አለብን፡፡
እንደ እህአዴግም የተጓዝንበት መንግድ ትክክለ ነወይ እንደ መንግሥትስ የቀየስነው ዓላማ ጠንካራ ነው አፈፃፀማችንስ እንዴት ነው ብለን ራሳችንን እስከ ታችኛይቱ የቀበሌ እና የጎጥ ጽ/ቤት ድረስ ልንፈትሽ አገራዊና ህብረተሰበአዊ ግዴታችን ነው ደካማ ጐናችንን ማመኑ ጥፋታችንን መረዳቱ የለውጥ ሂደታችን አንዱ አካል ነውና፡፡ ግትርንት አይሰራመ ለአገራችን ለኢትዮጵያ  እኔ ብቻ አውቅለታለሁ የምንልበት ዘመን አብቅቷል የበረሃ  ታጋይነት ብቻ በቂ አይደለም ከፈቃደ ሥጋችንና ከያዝነው የዛፍ ላይ እንቅልፍ ሥልጣናችን  ጋር ልንታገል ግድ ነው፡፡
የማከብራችሁ የመንግሥት  ባለሥልጣናትና የምወዳችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች ሆይ እኔ ዛሬ ከፊታችሁ ቆ ሜ ቃለ መሐላ የፈፀምኩር ኩራት አይደለም የሚሰማኝ ሥጋት እንጂ ይህን ሥጋቴን ዳግመ ወደኩራት መለወጥ የምችለው ከፊታችን ባስቀመጥንው ሶስት ዓመታት ውስጥ በሥራ እና በለውጥ ነውና እናንተን ከእኔ ጋር በመሆን አብረን ከእርሱ ጋር እየሠራን እንየው እንለወጥ ልትሉ ይገባል፡፡
መንግሥት መሥርተን በጋራ የምንሠራ በተለያየ የድርጅት አባልነት ያለን አለን በአጋር ድርጅትም ታቅፍችሁ ያላችሁ ሳስገነዘባችሁ የምፈልገው አንድ ጥብቅ ጉዳይ አለ፡፡  ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚናገሩትን ከእንግዲህ ልንሠማ ቦታም ልንሠጣቸው ግድ ይለናል ልንለውጣት ለቆምንላት አገራችን ኢትዮጵያ  እንርሱም እንደዜጋም ይሁን እንደተቃዋሚ የለው  አጋሮቸችን  ቻውና፡፡ ወሀትመ ለአገር ለውጥና እድገት ለሠዎች ልጆች ሠላምና እኩልነት የሚሠጕ የካበተ ልምድ  ካላቸወ ተለውጠው ከመጡ የደርግ ባለሥልጣናት ሣይቀር  በህይት ካሉ በንጉውም ዘመን ያሉ ካሉ እንቀበላለን”፡ ያቋቋምነው ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ምህደሩ እዚህ ድረስ ሠፈና ጥልቅ ነው፡፡
የተከበራችሁ የምክር ቤት አባላት ባለፋት የሁለት ዓመት የዚህ የምክር ቤት የሥራ ዘመናችን የኢትዮጵያ  ህዝብ እና ሚዲያዎች በሥራችን ላይ ምስጋና ነው ወይስ ወቀሳ ነው የሚያቀርቡት ክስ ነው ወይስ እርካታ ነው ያላቸው ምንድን ነው እየተሰማ ያለው ሰማንያ ሚሊዮን የኢትዮጵያን ህዝብ እንደመወከላችን መንግሥታችን ዲሞክራሲያዊ እንደ መሆኑ መጣን ምን መረጃ አለን እኛስ ምን መስራታችንን ነኁወ የምናውቀው እንደ አንደ ግለሰብ እንደ አንድ ኢትዮጵያዋና የምክር ቤት አባልነቴ ምን አስተዋፅኦ አድርጌአለሁ ብለን ራሳችንን ፈትሸናል ይህ ቀን ግን ራሳችንን ቆም ብለን የምንፈትቨበት ቀን ነው፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝና የምክር ፀበት አባላት በሙሉ አንድ ግዜ ከመቀመጫችሁ ብድግ በሉልኝ አመሰግናለሁ በዚያው እስኪ  እጃችሁን ወደ ኪሶቻችሁና ወደ ገንዘብ ቦርሳችሁ ከታችሁ
ተመልከቷቸው /ጠቅላይ ሚኒስትሩም እጃቸውን ወደ ኪሳቸወ ከተቱ የገንዘብ በርሳቸውንም  ፈተሹ የማን ገንዘብ ነው ኪሶቻችን ውስጥ ያሉት  መልስልኝ ጉርምርምታ ነገሰ በአዳራሹ  ጓዳች  ፀጠታ መልሰን እኔ እመለሰዋለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው የኢትዮጵያ  ሃብት ነው ለመሆነ ምን ያህል ሰርተን ነው ይህን ያህል የተከፈለን የፀዳ የላባችን ውጤት ብቻ ነው ኪሳችን ውስጥ ያለው በየግለ ሥማችን የተፃፋ የገንዘብ ማዘዥ ቼኮች የሉም በኪሳችንና በቤታችን  ጐበዝ በቃ አካሄዳችንን እንገምግም ችግር ካለብን በቃኝ ተነቅቶብኛል የጀመርኩር መንገድ አያስቀጠልኝም በማለት የለውጡን ጉዳና  ለመቀላቀል የኢትዮጵያ  ህዝብ ይቅርታ እንጠይቅ በአገሪቷ ላይም እርቀ ሰላም እናውርድ፡፡
ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ የፓለቲካ ድርጅቶች የሃይማኖት ተቋማት፣………ወዘተ ሁላችሁመ አንድ የጥሪ መልዕክት አለን እንደማመጥ መስማት ወይመ ማዳመጥ ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ ነገሮች ውስጥ አንድ ነውና፡፡መደማመጥ ለመንግሥታችን ፋይዳው  ከዚህ በላይ ነው ለለውጥ የተነሳ ትውልድ አዳማጭ ካጣ ልፋቱ  በጠቅላላ ዋጋ ቢስ ይሆናል ስለዚህ ለዚህ ለውጥ  መሳካት መዳመጥም ሆነ ማዳመጥ ትልቁን  ሥፍራ ይይዛልና እንደማመጥ  ሰዎች በየእመነታቸው ወደ ፈጠረን በፀሎት የምንጨኸው የፈጠርን ይሰማናል ያዳምጠናል መልስም ይሰጠናል ያሰብነውን ያለምነውን ያቀድነውን ያሳካልናል ብለንኮ ነዉ ታዲያ ትልቅ ራዕይ ሰንቀን ረጅሙን ጐዳና ከፈታችን አስቀምጠን ሳንደማመጥ እንዴት ይሆናል፡፡
ምንም እንኳን ለውጣቸው እስከዚህም ቢሆን የድሮ ነገሥታት (መሪዎች) የህዝባቸው የልብ ትርታ ለማዳመጥ ‘’እረኛው ምን ይላል’’ እሰከ ማለት ታች ድረስ  ወረደው ያዳምጡ ነበር፡፡  ታዲያ መደማመጥ ክፉ ነገር ከሌለው ለዚያውም በመረጃ መራብ  ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ለምን አንደማመጥም? መዳማመጥ አለብን፡፡ አለቃ ምን ይላል? ብቻ ሣይሆን ወደታች በመውረድ ሠራተኛው፣ ህዝቡ፣ ደጋፊው፣ ተቃዎሚው ምን ይላል? ማለት ይገባል፡፡ ህዝቡ ዝም ካለ አደጋ ላይ ነንና ባለፋት ሥርዓት እንዲሁም በኛም  ዘመን የሚናገሩ ብዙዎች  የሚያዳምጡ ጥቂቶች በመሆኑ መፍትሔ እና   ለውጥ ሣይመጣ ቀርቷል፡ ዛሬ ግን ያ ዘመን  ይብቃ! መስማት (ማዳመጥ) የመፍትሔው ዋነኛ ቁልፍ ነውና የተከበራችሁ ሚኒስተሮች ማዳመጥ ከማይችሉ መሪዎች ጋር የሠራ ሠራተኛ የመደማመጥን ባህል ማዳበር አይችልምና መደማመጥን ባህላችን  እናድርግ ብዙ ሥናዳምጥ ብዙ መረጃ  ይኖረናልና፡፡
     የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦችና የመንግሥት ባለሥልጣናት በእርግጠኝነት የምነግራችሁ ይብዛም ይነስም ይህቺን አገር በድለናታል፣ ተበዳይ ደግሞ ካሣ  ያስፈልገዋልና ይህ ጊዜ ምንም አጭር ቢሆንም ባለን አጭር ጊዜ  አገራችንንና ህዝባችንን  የምንክስበት እንጂ የምንከስበት ሰዓት ላይ አይደለም ያለነው ምን ያህል ነው ያጠፋሁት ሣይሆን  ጥፋቱ መኖሩን ማመን የጥፋቱ ምክንያት እኛው መሆናችንን ማመን በራሱ አንድ የለውጥ መጀመሪያ ነው ሌላው ዓብይ ጉዳይ የሚያጠፋትን ሠዎች ለመቅጣት ሥንል የምንዘረጋቸው መንግዶች በአገራችን ላይ ቂም እና በቀልን እንዳያሠፍኑ የተቀጣው ሠው ተምሮ ወደ ማኀበረሰቡ ተቀላቅሎ  ልማትን እና የዕድገቱን ለውጥ የሚያፈጥንበትን መንገድ ልንቀይስ   ይገባል፡፡ በዘመናችን ሠዎች የሚቀጡበት የእስር ቤት ግንባታዎችን ከማስፋፋትና የሌለንን የሠው ኃይል ለዓመታት  በአንድ ቦታ  ያለ ጥቅም ከማዋል  አስቀድመን ሠዎችን ከጥፋት ማራቁ አማራጭ የሌለው መንገድ ነው ስለዚህ በዚህ የሶስት ዓመት የሥራ ዘመናችን እንዚህ እስር ቤቶች  የልማት ሀይሎች መፍለቂያ ማድረግ አንዱና ዋነኛ ሥራችን ይሆናል ሌላው አገራችን በፓለቲካ ፓርቲ መሪዎች ብቻ የምትመራ ሣትሆን በፍቅር በዕድገት እና  በለውጥ ጐዳና የምንመራት ኢትዮጵያ መሆን አለባት፡፡
     ወገኔ የኢትዮጵያ  ህዝብ ሆይ ተከፋፍሎና ተቃቅሮ መኖር ከዚህ ቀደም በቅርበት ያየናቸው የአፍሪካ ህዝቦች ታሪክ  ብዙ ነገር ያስተምረናል ብዬ አስባለሁ የተደረጉት ክፋ ድርጊትና ብቀላዎች  አህጉሪቷን ለልማት  አላነሳሳትም ከጥፋትና  ከረኃብ፣ ከበሽታና ፣ ከእርሰ ብርስ  ጦርነትና ኃላቀርንት፣ ከትውልድ እልቂትና ከመበታተን / ከስደት/ አልታደጋትምና ከዚህ ክፋ  አጋጣሚዎች የመለያየትንና የክፋትን ነገር ልንማርበት ይገባል፡፡ ከቂም እና ከበቀል ይልቅ  ታሪካችንን በዕርቅ የምንቀይር ታሪክ ሠሪዎች  እንሁን፡፡  ትናንት  የተሠራውን ጥፋት እና መጥፎ ታሪክ እየዘረዘርን  የአጥፊውን ወገን በክፋ ዓይን ማየት ይቅር መካሰስ የትኛውን አገር ገነባ? የየትኛውን አገር ኢኮኖሚ  አሳደገ?
     ትናንትናን  መለወጥ ባይቻል ከትናንት መማር ግን ይቻላል  አይደል የሚባለው ከተስማማንና በግልጽ ከተነጋገርን በአንድነት እና  በቁርጠኝነት ለእምዬ ኢትዮጵያና ህዝቧ ለህዝቧ ታሪክ ለመሥራት ዝግጁ ከሆንን   ነገሮችን ሁሉ እንደምንፈልገው ማድረግ እንችላለን ታሪክ ለመቀየር ክፋ ነገሮችን  ወደ በጐ ለመገልበጥ የተነሳን ከሆንን ህዝባችንና የኢትዮጵያ  አምላክ እግዚአብሔር ከጐናችን ሆኖ  ብርታትና ሞገስ ይሆነናል፡፡  በትናንት መጥፎ ታሪካችን  ላይ  ሥንጣላ ሥንጨቃጨቅ ጥሩው ቀን ዛሬ ግን እንዳያልፍብን ጥሬዬን አቀርባለሁ፡፡
      ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝቦችን  ብሔር  ብሔረሰቦች ዛሬ የምንተራረምበትና  ጥሩ ሥራ ለመሥራት  የምንመካከርበት ቆርጠን የምንነሳበትና ቃል  የምንገባበት የለውጥ ብሥራት ዕለታችን ናት ፣ ከመላው የእትዮጵያ ህዝቦች ብሔር ብሔረሰቦች ልቡና ልትጠፋ  የማትችል ተከባብረንና ተዋደን  ልንኖርበት ቃል የምንገባበት  የደስታ ቀን ናት ተራርመን ጥሩ ሥራ መሥራት የማንችል ዜጐች ካልሆንን  እንደ ህዝብ ብዛታችን እና ብዙ  የብሔር ብሔረሰብ ሥብጥር ውጤት እንደመሆናችንን  መጠን ትናንት የነበሩት  ካጠፋት፣ ሌሎችም የአፍሪካ አገራት ላይ ከጠፋው ጥፋትና ከደረሰው  ውድቀት  የከፋ  ነገር ያጋጥመናል የበለጠ ነገርም ልናጠፋ እንችላለን፡፡ በውኑ የትናንትናዎቹን በምንወቅሳቸው ሚዛን ብንመዘን እኛ  ምን የተሻለ  ሥራ  ሠርተናል እነርሱን ያጋጣማቸው ነገሮች ቢያጋጥሙን እነርሱ ካጠፋት የተሻለ  ሥራ እንደምንሠራ ምን ማረጋገጫ አለን በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ሥናጠፋ ታግሶን ስናለማ አጋራችን በመሆን ከጐናችን ላልተለየ ህዝባችን ምስጋናዬና አክብሮቴ ላቅ ያለ ነው፡፡
    በመጨረሻም የተከበሩ የኢፌዴሪ ኘሬዘዳንት፣ የተከበሩ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ እና የተከበራችሁ የምክር ቤት አባላትና የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ባለፋት ሁለት ዓመታት የተጀመሩትን የልማት ሥራዎች ማስቀጠል  እንዳለብንና ሌሎችንም ሥራዎች ማቀድና መተግበር እንዳለብን ላሳስብ እወዳለሁ፡፡  ይልቁንም ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከዳር ማድረስ እንዳለብን በአጽንኦት  አሳስባለሁ፡፡  ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ እምቅ እውቀቱን ይዞ  በተለያየ አጋጣሚ ጉልበቱን ጭምር  ይዞ እንደ ዓባይ ለሌላው ዓለም ሲሳይ  የሚሆነውን ህዝባችንን ልንታደገው እንደሚገባና እንደ ወንዛችን ዓባይ ሁሉ ከአባይ ወንዝ በላይ ጥቅም ያለውን ህዝባችንን በአንድነት ልንገድበው ይገባል፡፡  የዓባይ ወንዝ በገንዘብና በጉልበት ሊገደብ  ይችላል ህብረተሰብ ግን በጉልበት አይገደብም በጥበብ እና በፍቅር እንጂ  ስለዚህ አደራ የምለው በጥበብና በፍቅር በመከባበርና በመተባበር በስደት ላይ ያለውን በመሰደድ  ላይ ያለውን እምቅ ሐብት  ህዝባችንን ለእምዬ ኢትዮጵያ እናውለው እንገድበው!!!
በእኔ በኩል የሥደት ምክንያት የሆነውን በነፃነት የመኖር መሠረታዊ  ነገሮችን፣ የሚዲያ እና የነፃ ኘሬስ ነፃነትን፣ የመንግሥትን በሀይማኖቶች ጣልቃ  ገብነት ገለልተኛ መሆንና እና ሌሎችን በራሴና ከምክር ቤቱ አባላት ጋር ታምኜ ልሰራ እና ላገለግላችሁ  እንድትሰሩ ላመቻችላችሁ ቃለ እገባለሁ ፡፡(ንግግሬን እዚህ ላይ አበቃለሁ በክብር ለህዝብ ጥቅም  ከድል በኃላ ለተሰውት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን መለስ ዜናዊ ከመቀመጫችን ተነስትን  በድጋሚ የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት እናድርግ፣ አመሠግናለሁ፡፡)

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !
ኢትዮጵያለዘለዓለምትኑር!
ክቡር ጠ/ሚ ኃ/ማርያም ደሳለ እንን ለዚህ አበቃዎት!

 

ሐሙስ 20 ሴፕቴምበር 2012

አንጥፋ



          ሁላችንም ወደዛዉ ነን!
        በጉብዝናችን ሰአት ከቤቱ አንጥፋ፡፡
God bless Ethiopia!

ዓርብ 7 ሴፕቴምበር 2012

“ወይንና ቀበሮ”


በአንድ ወቅት ነው አሉ ቀበሮ እስከማንዘሮቿበወይን ፍሬ ትተዳደራለች ልጆቿን ታሳድጋለች(የልጆቿን ነፍስ ትታደጋለች) እናም ከዕለታት አንድ ቀን የወይኑ ጌታ ለወይኑ ቅፅር/ አጥር/ ቀጠረለት ማስገቢያ ቀዳዳዎችን ደፈነ፤ ቀበሮ መግቢያ አይደለም የትንኝ መግቢያ መንገድ አልተገኘም ነበር፡፡ ነገር ግን ከጊዜ ብዛት ሾልካ የምትገባበትን ቀዳዳ መንገድ አገኘች መግባትም ጀመረች ነገርግንእንደድሮው ወይም እንደምትጠብቀው አልነበርም ወይኑ ከመብሰሉ የተነሳ እንዳይበላሽ በአውሬም እንዳረጋገጥና እንዳይበላ ተደረጎ በባላ ከፍ ተደርጎ ተሰቅሏል፡፡ እስከ ልጆቿ የመጣቸው ቀበሮ በመደናገጥ መዘየድ ጀመረች ይባስ የተራቡ ልጆቿ እየተንጫጩ እያቀለሱአስጨነቋት የነርሱ ርሃብና ልቅሶ ደግሞ የበለጠ ግራ አጋባት፡፡ የወይኑን ዘለላ እያየች ምራቋን ትውጥ እየዘለለች እየፈረጠች ለማውረድ መጣር ጀመረች፤ ጥረቷ ግን ሊሰምር አልቻለም የወይኑ ተክል ረጅም ቁመቱ አጭር ሆነባት፡፡ ዘለለች ዘለለች …. ምንም ሊሆንላት አልቻም፡፡ ተስፋ ስትቆርጥ ወደ ልጆቿ ዘወርበማለት እንዲህ አለቻቸው “ወይኑ አልበሰለምና አይረባም እንሂድ ሌለ የሚበላ ጥሩ ምግብ እንፈልግ” አለቻቸው ነገር ግን እንኳን ጥሩ ነገር ረሃባቸውን ሊያስታገስ የሚችል ምግብ አልሰጠቻቸውም፡፡ወይንን “አይረባም” ብሎ ስም ከማጠፋት በስተቀር፡፡
ይህ የቀበሮ ህይወታችን ዛሬ ዛሬ በአብዛኛውህብረተሰብ ህይወት ይንጸባረቃል ይህ ማለት ግን “የማይረባን “ ነገር አይረባም ከማለትየዘለለ አማራጭ ባይኖረውም የማይረባን ነገር የሚተካ ረሃብን የሚያስታግስ መልካም ነገር እስካልመጣ ድረስ ከመንደር ወሬነት ባለፈ መፍትሔ አይሆንም ምን አልባት የተወሰነ ነገር ያመለክት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ትችት ለበዛበት አገራችን መፍትሔ መጠቆምና ሥራ መሥራት እንጂ የሚረባት ጣት መቀሰርና አይረባም ማለት አይፈይዳትም፡፡ ለምሳሌ አይረቡም ከሚባሉት ተቋት ፓርላማው አይረባም፣ ሲኖዶሡ/ቤተክህነቱ/ አይረባም፤ ትምህርት ሚኒስትር /የትምርት ፖሊስው/ አይረባም፤ ማኀበረ ቅዱሳን አይረባም፣ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቨዝን አይረባም፣EBS አይረባም፣ ESAT አይረባም፣  የመንግሥት ሚዲያ አይረባም፣የግ(የእንቶኒ) ጋዜጣ አይረባም፣ የግል ዩኒቨርስቲዎች አይረቡም፣ወንዶች አይረቡም፣ ሴቶች አይረቡም፣ መ/ርእገሌ አይረባም፣ ፓስትረ እገሌ አይረባም፣ የነ እገሌ የዕምነት ተቋም አይረባም፣ አርቲስት እገሌ አይረባም፣ህገ መንግስቱ አይረባም፣ ዳኞች አይረቡም፣ ጠበቆች አይረቡም፣ ብሄራዊ ቡድኑ አይረባም፣ አትሌት እገለወእገሊት አይረቡም፣NGO አይረባም፣ የሃይማኖት ተቋም አይረባም፤ ዕድር አይረባም፤ ዕቁብ አይረባም፣ ፌዴሬሽኑ አይረባም፣ የቻይና እቃ አይረባም፣የእንትና መንግሥት አይረባም፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፓሊሲው አይረባም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች አይረቡም፣ የፖለቲካ (የዲሞክራሲ) ስርዓቱ አይረባም፣ የፍርድ ሂደቱ አይረባም፣ አስተሳሰባችንም አይረባም….. ወዘተ ብቻ የማይረባ ነገር የለንም ምክያቱም ከምናመሰግነው ይልቅ የምንነቅፈው ስለሚበዛ ነገር ግን ከዚህ ነቀፋ በስተጀርባ ጸሐፊው የታዘበው ነገር ሰልነበረ ይህን ጽሁፍ ለመፃፍ ተገዷል ብዙዎችን አይረባም ከማለት ባሻገር ምን ፈየድን ምን መፍትሔ ምንስ የተሻለ ነገር አቀረብን? ምንም፡፡ አወራን እንጂ ምን ሰራን?ምንም ለአገራችን ማደግ ለህብረተሰባችን መለወጥ ስራ/ድርጊት/ እንጂ ወሬ አላጠረውም፡፡ ማውራት ማስረጃ አይጠይቅምና እናወራለን ሥራ ግን ትልቅ አቅምና ትልቅነት ይጠይቃል ታዲያ ለምን ራሳችንን አንመዝንም? በመሥራት!
እስኪ የወቀስነውን የትምህርት ፖሊስ እንመልከት እንኳን እኔ/እኛ/ መንግሥትም እንደማይረባ መሻሻል እንዳለበት ያምናል ነገር ግን አይረባም ከማለት የዘለለ ምን አደርግንለት? ምንም፡፡ ነገር ግን ይህ የትውልድ ምንጭ የዜጋ መቅረጫ ሥፍራ ሊወራበት ሳይሆን ሊሰራበት የሚገባ ነበር፡፡ በቃ! መንግሥት ሊሠራ የሚችለውን አደረገ ከኛስ የሚጠበቅ ነገር የለም? ትናንት የተማርንበት ነገር ልጆቻችን ዕውቀትን የሚቀስሙበት የትምህርት ፖሊስያችን የፖሊስ ለውጥ ከእኛ ይጠብቃል ከወሬ ይልቅ ሥራ ይናፍቀል፡፡ ፓርላማውም እንዲሁ ገብቶ የሚተኛ የሚያስቅ ነገር ሲነገር የሚባንንና የሚያጨበጭብ እጁን የማውጣትና የማውረድ የሚቆጠር ሳይሆን ውሳኔ ሰጪ፣ ጥሩ አቋም ያለው፣ ራዕይ ያለው፣ የተቀመጠበትን ዓላማ ግብን የሚመታ ማኀበረሰብን ማዕከል ያደረገ ሥራ የሚሰራ የፓርላማ አባል ያስፈልጋል ከዳር ተቀምጦ አይረባም ከማለት ረሃባችንን ሊያስታግስ ስደታችንን ሊቀንስ የሚችል መፍትሔ የሚያመጣ አባላት ያስፈልጉናል፡፡
ሲኖዶሱ/ቤተክህነት/ አይረባም ሲባል ሁለት አሥርት ዓመታት አስቆጥሯል ታዲያ መፍትሔው ሃያ ዓመት ሙሉ ስአለመርባቱ ማውራትነው ወይስ የሚረባበትን መንገድ መቀየስ፣ አንዲረባ ማገዝ፣ ወይስ ምን ይሻላል ባለው አቅም መልካሙንም የሚስነቅፈውን እስከአሁን ሠራ ከአሁን በኋላስ የዘመንድ ቤት፣ የሙስና የተዘፈቀ፣ የተኩላ የመሸሺጊያ… እንዳሆነ ይቀጥል ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም እንደተመሰረተች “የሲኦል ደጆች አይችሏትም” ተብላ በኛ ዘመን የወላድ መካን ሆና ታንባ? ታልቅስ? ክፉ ነገር አውርተንባት ተጠቋቁመንባት ለጠላት አሳልፈን እንስጣት? በሌሎች የዕምነት ተቋማትም በመስኪድ የፀሎት ሥርዓቱን የሚመራው፣ ምዕመኑን የሚስተዳድረው፣ የሚያስመልከው፣ መጋቢው …..መንገድ ሲስት አርአያነት ሲጎለው እናውራ? አይረቡም እያልን እንቀመጥ? ወይስ ድራሻችንን እንወጣ ? እንዴት የተቻለ ፖሊሲ፣መተዳደሪያ ደንቦችን፣ እንቅረፅ እንሳተፍ ውጭ ከማውረት ጠጋ ብለን የሚረባ ነገር ረሀብን የሚያስታግስ ከሽሽት ከስደት የሚመልስ ለአምልኮ እግዚአብሔር የሚጋብዝ ሥራ እንስራ፡፡
ማኀበረ ቅዱሳን ማኀበሩ እንደሚለው ከ120,000 በላይ አባላት በመላው አገሪቱ እና በውጭው ክፍለ ዓለም ከሰንበት ትምህርት ቤት እስከ ግቢ ጉባኤ /በዩኒቨርስቲዎች/ ያሉት ሲሆን በቤተክርስቲያኑልማታዊና መንፈሳዊ ግልጋሎቶችን ሲሰጥ ሃያ አመቱን ደፍኗል፤ ማኀበሩም እንደሚያምን በድካም ውስጥ ጠንካራ ነገሮችን ሰርቷል “ኃይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ሁሉ እንችላለን” በማለትም አሁንም በስራ ላይ ይገኛል::ከመምሪያው ኃላፊዎች ጀምሮ ብዙዎቹ አይረባም ይሉታል ታዲያ ይገኛል ከመመሪያው ኃላፊዎች ጀምሮ ብዙዎች አይረባም ይሉታል ታዲያ ይህን የመሰለ በጎ ሥራ እየሰራ ያ ተቋም የቤተክርስቲያን ደጆች ሳይዘጉ፣ከወድቀታቸው እያንሰራሩ የአብነት ትምህርት ቤቶች ቀኑ ሳይጨልምባቸው... እንዴት ይርባ? እንዴት ወደተሻለ አኳኃን ይሻገር? ጥያቄው እዚህ ጋር ነው ጥቄቶች “ይዘጋ” ይላሉ ይህ የጠላት ወሬ ካልሆነ በቀር እንኳንስ ይህን የመሰለ ተግባር ያለው ቀርቶ ሃሳብ ይዞ የመጣ ይቋረጥ ሳይን እንዴት ይቀጥል በሚባልበት ዘመን አይመከርም፡፡ እሺ ምን ይደረግ? ሥንል የሚሻሻልበትን መንገድ እንጠቁም ይህ ነው አገርን፣ ተቋመን፣ ህብርተሰብን… የሚጠቅመው ችግሩን እንኳንስ እኛ ተቋሙም ያምናል ጠንካራ ነኝ ብሎ አይከራከርም፡፡
የኢትዮጵያ የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አይረባም፡፡ አዎ! አይረባም ታዲያ መፍትሔው ምንድን ነው? ሜዳ ገብተው ሲጫወቱ አትርቡም አንበላቸው ወይስ ከሜዳ ውጭ ሜዳ ከመግባታቸው በፊት አሰልጣኝ እንቅጠርላቸው? ዳጎስ ያለ ደሞዝ/አበረታች/ ይከፈላቸው? የሚጎድላቸውን እናሟላላቸው? በቂ የስልጠና ሥፍራ እናዘጋጅላቸው?...  ወይስ ቁጭ ብለን ስለ አለመርባታቸው እንነጋገር? የቱነው የኳስ ፍቅር ርሃባችንን የሚያስታግሰው? የቱስ የአገራችንን ስም በተሸለ ውጤት የሚያስጠራው? መነቃቀፍ ወየስ መደጋገፍ?
የቻይና ዕቃ አይረባም በኢህአዴግ ዘመነ ሥልጣን ቻይና 81 ብሔር ትሆናለች ብለው ይተነትናሉ ቀልደኞች እውነትም ከገጠር እስከ ከተማ ቻይናዊ የማይገኝበት ድንበር የለምያገባት የስራ ዘርፍ ሻይና ፓስቲመንገድ ላይ መሸጥ ብቻ እስኪመስለን ድረስ ሁሉም ተቆጣጥረውታል አብዛኛው ወደ አገር ወስጥ የሚገቡ ቃዎች የትውልድ አገራቸው ቻይና መሆኑን መርካቶን በእማኝነት መጥራት አሰገዳጅ አይደል ሁላችንም ምስክሮች ነንና፡፡ነገር ግን ይህቺ ለአሜርካን ለአውሮፓ አምርታ የምታቀርብ አገር ወደ ኢትዮጵያ የምትለካቸው ዕቃዎቿ አይረቡም ይባላ?እንደያውም ካጅማ የተባለው የመንገድ ስራ ተቋራጭ ከአዲስአበባ ደጀን ያለውን መንገድ ሲገነባ በጫማዋ ያቃጠለችን አንሶ በመንገዷ ልታቀጥለን መጣች የሚል ምሬት አዘል ቀልድ ሲቀለድ እንደነበር የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ አዎ አይረባም ነገር ግን ምን ይደረግ? የማይረባ ነገር ምርት አገር እንደልሆነች የኢኮኖሜ ዕደገቷ ምስክር ነው ችግር የመግዛት እቅማችን የፈጠረው አቅርቦት ነው፡፡ ደሃ ከመሆናችን የተነሳ የመግዛት አቅም አጠረን አዎ ቻይና የሚረባውንም የማይረባውንም እንደ መግዛት አቅማችን ትልካለች ብዙዎቻችን የመግዛት አቅማችን የወረደ ከመሆኑ የተነሳ የምትልከው አይረባም፡፡ ባለመርባቱ ቻይና ተጠያቂ ናት? የሚረባ ነገር እንድትልክ ምን ይደረግ? እንዲህ በደፈናው የቻይና እቃ አይረባም ማለት የተሟላ ወቀሳ አለመሆኑን የአሜሪካና የአውሮፓ ገበያ ምስክርነው፡፡ እነ ኢትዮ ቴሌኮም፤ እነ መብራት ኃይል፣ የውሃናፍሳሽ፤ መንገድና ትራንስፖትስ አትረቡም ሥንላቸው  እነርሱም እንደማይረቡ ያውቁት ይሆን? ልብ ይስጥልን፡፡
ለማመላከት ያህል ይህን ያህል ፀሐፊው ከተጋራ ቀሪውን ደግሞ አንባቢያን ልብ እንደምትሉት ተስፋ ያደርጋል፡፡ አዎ ሁሉም ቦታ ችግር አለ ሁሉም ቦታ የማይረባ ነገር አለ እኛስጋ ረሃብ የሚያስታግስ፤ ከስደት የሚመልስ፤ ዕምባ የሚያብሰና ጫጫታውን የሚቀንስ ምን መፍትሔ አለ? ወይንስ “ችግር አለ፤ “አይረባም” እያሉ ማውራት ብቻ ይሆን? የተፀናወተን ችግርን የሚፈታው ችግርን መጠቆም ብቻ ሳይሆን መፍትሔን ማምጣት ነውና፡፡
እነዚህ የጠቀስናቸውና ሌሎችም አይረቡም ብለን ተስማማን ግን ለዚህ ማህበረሰብ እነረሱ ካደረጉት አስተዋጽኦ የተሻለ ያደረግነው ነገር ምን አለ? ለዚህ ማህበረሰብ ከቻይና ልብስና ጫማ ውጭ እኛ ምን ሰጠነው? ምን አጫማነው /ምን አለበስነው?/
ለዚህች አገር ባለው ነባራዊ ሁኔታ ካለው “መንግሥት” ምን የተሻለ ነገር አደረግን ባለመርባት ውስጥም እያስተዳደረ እያለ የምንተችው መንግሥት ነው: ለቤተክርስቲያንስ ቢሆን ከማኃበረ ቅዱሳን በተሻለ ምን ፈየድንላት? ካለው የትምህርት ፖሊሲ የትኛው ተቋም ትምህርት ሊያደርስ ማን ቻለ? የተሻለ ፖሊስና አሠራር ያለው እኔ ነኝ ይበል ተንፍሱ ተያዩበት ተችቱ፣ አመስግኑ፣ አቅጣጫ አመልክቱ፣……(ልብ በሉልኝ ቤተመንግስትም ሆነ ቤተ ክህነት ይረባልም አይረባምም ማለት አልፈልግም መለኪያ የለኝምና፣ ራሴን ማግለሌ ከፍርሐት እንዳልመነጨ ይታወቅልኝ ተከባበሩ እንጂ አትፈራሩ እግዚአብሔርን ፍሩ ሠውን አክብሩ፡፡)
God bless Ethiopia!

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...