ሐሙስ 29 ማርች 2012

‘’Disqualify’’


Disqualify  የሚለው ቃል የእንግሊዝኛ ቃል ሲሆን ‘’verb’’ ወይም ግስ ብለን የምንጠራው ሲሆን መዝገበ ቃላት ‘’to put out of a competition’’  ወይም ‘’to make unfit for some purpose’’ብሎ ይፈታዋል በመጠኑ ወደ አማርኛ ሳንመልሰው ‘’የማይመጥን፣ከጨዋታ ውጭ ማድረግ፣…… ወዘተ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡
    ይህንን  ነገር ጫር ጫር  ለማድረግ አንድ ነገር አጋጠመኝ ገጠመኙ እንዲህ ነው ‘’ታቦት ከመንበሩ ሰው ከሃገሩ የሚወጣው ችግር ሲኖር ነው’’ ይላሉ የአክሱም ሰዎች እናም አንዲት እህቴ  ኑሮ ሲከብዳት ሥራ ካለዘመድ፣ ካለ እጅ መንሻ፣ ሴትነትን ካልገበሩ በቀር፣ (እንዲያውም በአንድ በአገራችን ባለ ትልቅ ተቋም B.P.R ወይም Transformation የሚባለው ነገር ሲሰራ ለምደባ እና ለሹመት እንደ መወጣጫ አገልግሎ ነበር አሉ) ብቻ ምን አለፋችሁ ለብዙ ዓመታት ለረጅም ወራት ብዙዎች ሥር አጥተው እቤት አንደሚቀመጡት ሥራ አጣች፣እቤት ተቀመጠች፡፡’’ በእንቅርት ላይ…. ‘’ እንደሚባለው ሥራ በማጣት ላይ ይህችን አገር ጠላች፡፡  መጥላት በአገራችን በሰፈነው ዲሞክራሲያዊ መብት የተለገሳት ነውና፡፡  እንኳን እርሷ ሥንቶች ሄደው የለ? እንኳን እርሷ አንድ ግለሰብ ይቅርና ቱባ ቱባ የአገሪቱን ሥልጣን ተሸክመው አገርና ህዝብ ሲመሩ የነበሩትስ ጠልተው ወይ ተጣልተው  ሄደው የለ? ታዲያ ይመሯትና ያስተዳድሯት የነበሩትን ታማኝ የአገሯን ባለሥልጣናት ተከትላ ብትሄድ ምኑ ነው ክፋቱ? ወንጀል ሰርታ ለመሰወር፣ የአገሪቱን ሃብት ንብረት መዝብራ ለመደበቅ አስካልሄደች ድረስ፡፡
     ሊቁ ወደ  ጥንተ ነገራችን እንመለስ እንዳለው ወደ ጥንተ ነገራችን እንመለስና  በቃ ሥራ አጣች አገር ጠላች ሥደት አማራት ይቅርታ ከአገር ወጥታ ሌላ አገር ሄዳ ሥራ ለመፈለግ  ተመኘች ሰው አገር ሄደች ከመሄዷ በፊት ግን እንዲህ ሆነ እርሷ ለመሄድ ተመኘች ፣ ቤተሰብ መክራ ወዳጅ ዘመድ ወንድም እህት ገንዘብ አሰባስባ፣ደላላ ተፈለገ፣ /ተገኘ/ ኤምባሲ ተሄደ፣ ቪዛ ተመታ፣ደላላ ብሬን ክፈሉኝ አለ ከአገር የምትወጣበት ቪዛ ማግኛ ሳይሆን ከአገር  ለመውጣት የምታቆራርጥበት የመኪና መግዣ የሚያክል  ዋጋ ጠየቀ፣ አለመግባባት ተፈጠረ፣ ፓስፓርቷን ነጥቋት ሄደ፣ ሽምግልና ተጀመረ እንዲህ አለ፡፡……’’የምላትን ገንዘብ አስካልከፈለችኝ ድረስ የትም አትሄድም ፓስፓርቷን  አቃጥለዋለው ከዚህ በኃላ  ወደውጭ አገር የመሄድ ሙከራ እንዳታደርግ  የእርሷን ጉዳይ Disqualify አደርገዋለሁ አለ፡፡’’ እጅግ በጣም በማን አለብኝነት፣ በትቢዕት፣ ከ’ኔ ወዲያ አድራጊ ፈጣሪ የለም በሚል ሥሜት፣….. ምን አለፋችሁ  ብዙ ብዙ  ነገር ሆነ………..ግን ሄደች የልቧ ደረሰ እንባ እራጭታን ተሸኘች፡፡
     ነገሩ ወዲህ ነው አስኪ በህይወታችን ውሰጥ ሰዎች በሥልጣናቸው፣ ሰው በማወቃቸው፣ ገንዘብ ሥላላቸው፣ አካሄዱን ሥለሚያውቁበት፣ ብቻ ምናለፋችሁ በሆነ በሆነ መንገድ አድርገው ይገባሉ ገብተዋል ለመግባት አድብተዋል፡፡  ግን! ግን ይህን ለማድረግ እነርሱ ማን ናቸው? እነርሱ በኛ ህይውት ላይ ይህንን ሲያደርጉ መብት ካላቸው በእኛ ላይ እንዳይደረግ ፍትህ የለም እንዴ? ምን ይደረግ ‘’ገንዘብ ሲናገር ፍትህ ዳጥ’’ ይላል ተብሎ የለ፡፡
    አንድ ነገር ልበላችሁ ሰዎች ብዙ ነገር ሆነው ይሆናል ለመከላከል ብዙ ደክመው ድካማቸው ከንቱ ሆኖ ይሆናል እናንተ ግን አትሸነፋ ብዙዎች ታላላቅ ብለን ታሪካቸውን  የምንዘክርላቸው ታዋቂ  ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ቅዱሳን፣……. ከብዙ መውደቅ መነሳት በኃላ፣ ከብዙ ሽንፈት  በኃላ፣ ከብዙ መንገላታት  በኃላ ነውና ለዚህ የበቁት ለውድቀታችን መንስኤ የሚሆነው  መጀመሪያ የራሳችን መውደቅ ስለሆነ ጥንቃቄ እናድርግ ራሳችንን ሥንጥል ነውና ሰዎች እኛን ለመጣል የሚበረቱት፣ በደካማ ጐኖቻችን ሥለሆነ እየገቡ የሚጥሉን እጅግም ራሳችንን ለጠላቶቻችን ክፍት እናድርገው ማንነታችንን ይጫወቱበታልና እንቁዎቻችሁን በእርያዎች /ዓሣማዎች/ ፊት አታስቀምጡት እንዳይስብሩባችሁ’’ እንዲል እንቁ ማንነታችንን እንጠብቅ ብዙዎች በዚህ የተነሳ  ከሥራ ገበታቸው፣ ከሚያምር ትዳራቸው፣ ተምረው ይመጥናሉ  ተብለው ካገኙት ሥልጣን /የሥራ ደረጃ/ ከክብራቸው (ከድንግልናቸው)፣ በሰው ዘንድ ተዓማኒ ከመሆናቸው፣…… ወዘተ Disqualify ተደርገዋል ሊደረጉ ተዝቶባቸዋል፣ እየተደባባቸው ይገኛል፡፡ ግን ለምን?
    ወደኃላ ተመልሰን ታሪኩን ሥንዳስስ ያ ሰው ፓስፓርቷን ቪዛዋን…… እንዲያውም ይባስ ብላ የትም አገር እንዳትሄድ ጭምር ብሎ ሲዝት በየቦታው በየስራ ክፍሉ ለእውነት የቆመ የለም?  ፍትህስ የለም?  እውነትስ ወደየት ሄደች?  ልብ አርጉ ይህ ሰው አንድ ብቻውን ነው ብዙ ኤምባሲዎችን የመንግሥት ተቋማትን /ኤሜግሪሽንን/ ጨምሮ ማለት ነው የሚያምሰው እርሱን የመሰሉ ህብረተሰቡን የሚያውኩ ተቋማትን ለመጣልና አላማቸውን ለማሳት ባለሥልጣናትን ለማሰናከል ላይ ታች የሚሉትን ቤት ይቁጠራቸው፡፡

    ዛሬ በየማረሚያ ቤቶች /እስር ቤቶች/ ሥንት ባለስልጣናት የኃላፊነት ቦታ ላይ ሲሰሩ የነበሩ በንፅህና ህዝቡንና መንግሥትን ሲያገለግሉ ከነበሩበት እነዚህ ሰዎች እየገቡ ክፋ ዘር ዘርተውባቸው ጉድ የሰሯቸው ገሚሶችም እንሰሳትን ጨው በማላስ ወደ መታረጃው እንዲወስዷቸው እንዲሁ ጨው የተባለ ጥቅምን /ገንዘብ/፣ ውዳሴን፣ዝናን ወዘተ በማቅመስ ወደ እስር ቤት ያስወረወሯቸው ዘመድ፣ የቅርብ ወዳጅ በመምሰል የሃሰት ፈገግታቸውን በማሳየት እየሳቁ የገደሏቸው ቤተሰባቸውን የበተኑባቸው፡፡
     አንድ ነገር አጥብቄ መናገር እፈልጋለሁ የትም ይሁን የት በቀበሌ ከጥበቃ  እስከ  ቀበሌው ሊቀመንበር መታወቂያ አንሰጥም፣ የቀበሌ ቤት አንሰጣችሁም ጉዳያችሁን አንፈፅምላችሁም ብሎ ጉዳያችንን Disqualify የሚያደርጉብንን፣ በየመሥሪያ ቤታችን  የዓመት ፈቃድ (ዕረፍት) ከመስጠት እስከ ዕድገትና ዝውውራችን ላይ የሚቀልዱትን፣ሆስፒታል ሄደን ከካርድ ክፍል እስከ ሐኪሙና የመድኃኒት ወይም ላብራቶሪ ክፍል ድረስ፣ በትምህርት ቤት ከዩኒት ሊደር፣መምህር ዳይሬክተር ድረስ ፣በዕድር፣በዕቁብ፣ በትዳር ውሰጥ የእኛን ጉዳይ Disqualify በማድረግ ሽባ  ሊያደርጉ  አሰፍሥፈው የሚጠብቁትን በቃ ልንላቸው ይገባናል፡፡ ይህንን ለማስከበር  ከተቋቋሙ የፀጥታ ኃይሎች፣ የሰብዓዊ መብት፣ ዕንባ ጠባቂ ፣ ፀረ-ሙስና ኮምሽን፣በአጠቃላይ ከመንግሥት ጐን ልንቆም ይገባናል፡፡ ለመብታችን ዘብ እንቁም  እንዚህን ሰዎች እናጋልጥ ችግሩን ከምንጩ እናድርቅ ተዋናዬችም ካለን እንታቀብ፡፡

ረቡዕ 28 ማርች 2012

ውረድ?


ተውተውሲሉህ
ሲያፈራሩህ
አቅማቸውንአተው
ማንነትህንዘንግተው
አቅራሩሸለሉ
ፎከሩ
ፍጥረትበሙሉ
አንድምሳይቀሩ
ለአመድባንድነት
ለትርፍሳይሆንለጉድለት/ለክስረት/
ተውተውእያለሁ
እያስፈራሩህ
ውረድወይፍረድ
ብለውተሳለቁብህ
ትወርዳለህወይስትፈርዳለህ?
ቅልልመናውንለማያውቅፍርዱ
አዕምሮመስጠትነው
በትዕግሥትማለፍነው
የፈጣሪ/የአባትልምዱ
እላለሁ
አትውረድ
አትፍረድ
ይቅርበለኝእንጂ
በምህረትህእንድንዋጅ
ተውተውተውአለህ
በመፍጠርህሊያስቆጩህ
22/01/03
ደረሰረታ




v ጥላቻ የፈሪ በቀል ነው ፡፡
v ፍቅር ጣፍጭ ነው ክህደት ግን ከመራርነቱ አልፎ ሲኦልነው፡፡

“አንቀጽ 39 እና ደቡብ ሱዳን”


 “አንቀጽ 39 እና ደቡብ ሱዳን”
ደቡብ ሱዳን የአፍሪካን እና የዓለምን ቁጥር በአንድ እንደጨመረች የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ እንዲሁ በቅርቡ ደግሞ በፌዴራሊዝም ከሚመሩ በዓለም ላይ ካሉ ከ193 አገሮች 28ቱን ተቀላቅላ 29ኛ እንደምትሆን ተስፋ ይጣልባታል፡፡

መቸስ ነገርን ነገር ያመጣዋልና በቅርቡ ፌዴራሊዝም ቃሉ የመጣው ፌዴራል ከሚለው እንደወጣ ፌዴራል የሚለውም ለጊዜው ቃሉ የየት አገር እንደሆነ ከዘነጋሁት አገር ፌዴክስ እንደተወረሰ ሰማሁ ፌዴክስ ማለትም ‹ቃልኪዳን› ‹‹ስምምነት›› ማለት እንደሆነ ነግረውኛል፡፡

ወደ ሱዳን ጎረቤት አገራችን እንመለስና ከአንድ ሁለት ይሻላል በማለት ተስማሙና ጥንታዊቷ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን በሚል ኬክ ጋግረው ሰው ጠርተው ሥም ተከፋፈሉ እንዲያውም የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትራችንም ተጋብዘው በመገኘት የስምምነት ፊርማቸውን አድምቀዋል የደቡብ ሱዳንን መወለድ የደስታ መግለጫ እኛንና መንግሥታቸውን በመወከል እንዳደረሱ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡

ህፃን ልጅ ዓይን እንደሚያጠቃው በእኛ አገር በእነርሱ አገር ደግሞ ህፃን አገር ዓይን ያጠቃዋል መሰል በሁለቱ አገር አዋሳኝ ላይ ተጣሉ፡፡ ምነው ምን ሆናችሁ ባለፈው ደስ ብሎን ኬክ ቆርሰን በልተን ሻምፓኝ ተራጭተን ጠጥተን በአገራችሁ በአገራችን ቋንቋ ዘፈን ጨፍረን እስክስታ ወርደን ዓለም በሙሉ ጉድ ብሎ እኛ ስንት ኃያልን አገራት በህገ መንግሥታቸው አንቀጽ 39 የ ‹‹… እስከ መገንጠል ድረስ›› መብትን አርአያ ይሆኑናል ብለን ስንጠብቅ አንዲት አፍሪካዊት አገር ቀደመች ብለን በቅናት አረን ተቃጥለን ሳናበቃ ምነው ምን ነካችሁ ብለው ውስጣቸው ደስ እያለው የዓለም መንግሥታት የሃዘን መግለጫቸው ላኩላት እናት ዓለም ኢትዮጵያ ደግሞ መቸስ የእናትን ነገር እናቶች ያውቋታል ሥፍሥፍ ብላ አጥንታቸውን ሲከሰክሱ ደማቸውን ሊያፈሱ ቃል የገቡ ጀግኖች ልጆች አሏትና እዚች ሱዳን ሰላም ጠፍቷልና ትንሽ የተቀያየሙ ስለመሰለኝ ሠላም አስከብሩ ብላ ልጆቿን በነዳጅ እየተቀጣጠለ ወዳለ የከሰለ እሳት ለብቻቸው ጥቂቶች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ተሰው ይህቺ ሱዳን ባመጣችው ጣጣ፡፡

ሱዳን በሰሜን ከግብፅ በሰሜን ምሥራቅ ከቀይ ባህር በምሥራቅ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ቻድ በምዕራብ በደቡብ ከደቡብ ሱዳን ትዋሰናለች፡፡ ሱዳን ከአረብ ባህል ጋር ተዋህዳ ያለችና የምትጠቀምባቸውም ቋንቋ በአብዛኛው አረብኛና እንግሊዘኛ ነው የምትመራው በፕሬዝዳንቷ አማረ ኢል-በሽር እና በምክትሉ አሊ ኦስማን ጠሃ ነው ጠቅላላ የመሬት ስፋቷ 1,886,068 ኪ.ሜትር ስኮር እንዲሁም ጠቅላላ የህዝብ ብዛቷ በ2008 30,894,000 እንደሆነ ይገመታል፡፡

ይህንን የመሰለ ይዘት ቢኖራትም ሊከፋፈሉና ሁለት መንግሥት ሁለት አገር ከመሆን ያገዳቸው አልነበረም በ2011 በምርጫ አብላጫውን ድምፅ መገንጠል እንፈልጋለን በማለት ተስማምተው ተገነጠሉ የሚገርመው ነገር በዓለም ላይ በአፍሪካ አይደለም አንድም፡- አንድም አገር በህገ መንግሥቱ መገንጠልን አስመልክቶ ያካተተ አገር ከኢትዮጵያ በቀር ያፀደቀ አገር የለም ነገር ግን የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የሠላም ወዘተ… ጥያቄ ካስነሳ እኩልነት ከጠፋ እና መገንጠል ከፈለጉ ማንንም ሊያግድ እንደማይችል ሱዳኖች አሳይተዋል፡፡ ከዚያም ቀደም ብላ የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት የመገንጠልን አቋም በአንቀፅ 39 ከማካተቱ በፊት ኤርትራ ተገንጥላለች፡፡ ከነዚህ ሁሉ በመቅዳት ካናዳ ውስጥም የመገንጠል ሃሳብ ተነስቶ ንቅናቄው የተጀመፈ ቢሆንም የህዝብ ድምፅ እየተሰበሰበ ባለበት ሰዓት አንገነጠልም በአንድነት መቀጠል እንፈልጋለን ባዩ በመብዛቱ ወይም አብላጫውን ድምፅ በመያዙ ሊቀር ችሏል፡፡ ይህንን ንቅናቄ የገታው የአንቀጽ 39 የመገንጠል መብት በህገ መንግሥታቸው የመካተትና ያለመካተት ጉዳይ አልነበረም ያስቀረው ወደ አገራችን ጉዳይ ስንመለስ ብዙዎችን ያነጋገረና ያስቀየመ የፖለቲካ ፓርቲዎችንም ለምርጫ ቅስቀሳ ዓብይ ርዕሰ ጉዳይ ያደረገ አንቀፅ ቢኖር አንቀጽ 39 ነው፡፡ በነገራችን ላይ የአንቀጽ 39 ጉዳይ የመፈለግ ያለመፈለግ፣ የመውደድ እና የመጥላት ጉዳይ፣ የማውጣትና ያለማውጣት ጉዳይ ወዘተ… እንደፈለገው የሚያደርገው አይደለም ዛሬ መንግሥትም ህዝብም መኖሩን ጠልቶ እናውጣው ቢል የዘጠኙም ብሄር ብሄረሰቦች ተወካዮች ሊስማሙ ግድ ይላል አንቀፁን ለማውጣት ይሁንታቸው ወሳኝነት አለው፡፡ ነገር ግን ቢቀመጥስ ምን አጎደለ? ባለፈው ዓመታት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ምን አጠፉ? አንቀጹ ከመደንገጉ በኃላ ማን ተገነጠለ ይልቅስ ለመንግሥትም ለህዝብም እንደ ማስጠንቀቂያ /ማስፈራሪያነት/ ከማገልገል ውጪ እስኪ ይህ አንቀጽ ወጣ እንበል የመረረው እኩልነት የተነፈገ ነፃነት የጠማው ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካው ችግር ያጋጠመው ለመገንጠል ቢፈልግ አንቀጹ ላይ የለም ብሎ የሚከለከለው አለን? መኖሩስ እንዲገነጠል ያበረታታው አለን? (አደራችሁን ከፖለቲካው መንፈስ ነፃ በመሆን ተመልከቱት) ባለትዳሮች ትዳር ሲበቃቸው በቂ ምክንያት ኖራቸውም አልኖራቸውም የሚፈቱት ‹‹ፍቺ›› በህገ መንግሥቱ ስለተደነገገ አይደለም እነርሱ ስለፈለጉ እንጂ፣ ካናዳውያን መገንጠል ፈልገው ያልተገነጠሉት ህገ መንግሥቱ ስላልፈቀደላቸው አይደለም ህዝቡ ድምፅን በድምፅ ስለሻረ እንጂ፣ ደቡብ ሱዳን ከዋናው ሱዳን የተገነጠለችው አንቀጽ 39 በህገ መንግሥታቸው ስለ ነበረ አይደለም መገንጠል ስለፈለጉ ድምፅን በድምፅ ስለረቱ አብላጫውን ድምፅ ስላገኙ ህዝቡ በመገንጠል አቋም ላይ አንድ ስለሆነ እንጂ፡፡ የኢትዮጵያም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም አብሮ ለመኖርም ለመገንጠልም የጋራ አቋማቸውና አንድነታቸው ይወስነዋል፡፡ ለዚህችም አገር ከድህነት ጋር ለምታደርገው ትግል ትንሳኤም ይሁን ውድቀት የህዝቧ አንድነት በድህነት ላይ ሆ! ብሎ መነሳት ወሳኝ ነው ሆ! ብለን ከምንወድቅ ሆ! ብለን እንነሳ ሆ! ብለን ከመገንጠል ሆ! ብለን አንድ እንሁን አንድ ያድርገን፡፡

በአንድ አገር ሁለት አገር ሁለት መንግሥት ሁለት ህዝብ ለመፍጠር እንደተገደዱ በአንድ ቤት ጥላ ስር አንድ ከመሆን ለመቆራረስ እንደተገደዱ የመቆራረስ የመገነጣጠል ዕጣ ፈንታ ሊደርሳቸው የተቃራቡ ትዳሮችና ጎጆዎች ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ምሬት፣ ፍቅር ማጣት፣ የእኩልነት መጥፋት፣ የመለያየት መብዛት፣ ያልተንሰራፋበት በሩን ያላንኳኳበት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አለበለዚያም ራሳቸውን የሚሸነግሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለልጆቻቸው ሲሉ የሚኖሩ፣ ለሥማቸው /ሰው ምን ይለኛል/ በማለት ላም እሳት ወልዳ እንዳትልሰው … ሆነባት እንደሚባለው የሆነባቸው ቤታቸው አንቀጽ 39 እና ደቡብ ሱዳን የሆነባቸው ነፃነት እየጣማቸው የሚኖሩ የነፃነት ያለህ የሚሉ፣ ነፃነትን በልጅ፣ ነፃነትን በሥም፣ ነፃነትን በሠው ወሬ፣ የቀየሩ የትዳር አንገታቸውን የደፉ፣ የትዳር አንገታቸው /ፊታቸው/ ፅልመት የለበሰ፣ ልቡናቸው የተሰበረ፣ ጨጓራቸው የተመለጠ … ጥቂት የማይባሉ ናቸው፡፡

በሃይማኖት ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት ያጡ፣ በፖለቲካ ውስጥ የፖለቲካ ነፃነት ያጡ (የመናገርና የመደመጥ መብት ያጡ መናገራቸው በሠዓት የተገደበባቸው ቢናገሩ አሸባሪ የተባሉ …)፣ አገር እያላቸው በአገራቸው ላይ በነፃነት የመንቀሳቀስ ነፃነት ያጡ (ሁሌ ጥላቸው የደኅነት /የፖሊሲ/ አሻራ ያጠላበት፣ ቃላቶቻቸው ሁሉ በፍተሻ በቃላት መሠንጠቂያ የግድ ማለፍ ያለበት) አንቀጽ 39 የሚያምራቸው የደቡብ ሱዳን እጣ ፈንታ የሚናፍቃቸው እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ነገር ግን በአደባባይ እንዳይናገሩ እፍራት የተሰማቸው ሠው ምን ይለናል ብለው የሚጨናነቁ እንገለላለን፣ አሸባሪ እንባላለን፣ … ብለው ዝም ያሉ …

አንዳንድ የአገራችን የፖለቲካ ተንታኝ የአንቀጽ 39 መኖር አንዳችም አሉታዊ ተፅዕኖ የለውም ይልቁንም 80 ያህል የሆኑትን ብሔር ብሔረሰቦች ተከባብሮና ተፋቅሮ እንዲሁም ተቻችሎ እንዲኖር አድርጎታል በማለት ይናገራሉ ነፃነትን ከመፈቃቀርና በልማት ከመተባበር ጋር አንድነትን ያላበሰ ነው በማለትም ያክላሉ የመገንጠል ሙሉ ነፃነት እንዲሁ ደግሞ በአንድነት በፍቅር መኖርን ያላበሰ ነው ይላሉና ያጠናክሩታል፡፡ ፖለቲካ እንዲህ ከሆነ ሃይማኖት፣ ትደር፣ ጓደኝነት፣ ቤተሰብ፣ … እንዲህ ዓይነት ነፃነትና ሠላም የሚያገኘው መቼ ነው? መቼ ነው የሃይማኖት መሪዎቻችን ነፃነትን ከሠላም ጋር ከእኩልነትና ከግልፅነት ጋር የሚያጎናፅፈን መቼ ነው? የትዳር፣ የጓደኝነት፣ … አገሮቻችን ሠላምና ነፃነትን የሚሠጡን?

አከራዮቻችን ከፍለን ለምንኖርባት ጎጆአችን ነፃነት የሚሰጧት መቼ ነው? በር ለምንድን ነው በደንብ የተከፈተው? መብራት ለምን በጊዜ በራ? ውሃ ለማን ተደፋ? እንግዳ ለምን በዛ? ከመጠን በላይ ለምን ሣቃችሁ? … እየተባልን መነዝነዙ መቼ ነው የሚያበቃው? መቼ ነው ለተከራየንበት ክፍል እንደ ደቡብ ሱዳን ነፃነታችንን አውጀን በየዕለቱ አንዳንድ ነገር ሳንገብር በወር ኪራይ ብቻ የምንኖረው? መብራት ቆጠረ የቤት ኪራይ ጨምሩ፣ ውኃ ቆጠረ የቤት ኪራይ ጨምሩ መባል ስጋት መች ይሆን የሚያበቃው???

ስናጠቃልለው ደቡብ ሱዳን እና አንቀጽ 39 የመዳፍ ያለመዳፍ የመፈቀድ ያለመፈቀድ ጉዳይ አይደለም የሞደርናይዜሽን /የዘመናዊነት/ ምልክት እንጂ ዘመናዊነታችንን በዘመናዊነት (በመከባበር፣ ነፃነት አንዳችን አንዳችንን በማጎናፀፍ) እንግለፅ! ቸር ይግጠመን፡፡  

ሐሙስ 22 ማርች 2012

“እረኞቹ ከፊት በጎች ከኃላ ይከተላሉ”


     መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ብሎ ሲናገር ስለበግ እና እረኛ ተጨንቆ እንዳልሆነ እሙን ነው በጎች ያለው ምዕምናንን እረኞች ያላቸው ካህናትን፣ ጳጳሳትን ፣ (ፓትሪያሪክን)፣ መምህራነ ወንጌልን እንደሆነ የቤተክርስቲያን አስትምህሮ ያመሰጥረዋል፡፡
  ምነው ታዲያ ዕረኛን አስቀድሞ በጎችን አስከተለ ወይንስ መጽሐፍ ፀሐፊዎች ተሳስተው ነው? /Typing Error/ ይሆን? ቢሉ መጽሐፍ አልተሳሳተም የታይኘ ሥህተትም አይደለም፡፡  እናስ ምንድን ነው ቢሉ የባህል ልዩነት ነው ፡፡ እስራኤላውያን በጎችን ከለምለም መስክ  ሲያሰማሩ እንዲሁም ከነጣቂ ተኩላ ሲጠብቁ ከበጎች ፊት ለፊት በመሄድ እንደሆነና በጎችም ጠባቂያቸውን (እረኛቸውን) እንደሚከተሉ መጽሐፍ ቅዱስ ያስረዳል፡፡  በኢትዮጵያ  አገራችን ነባራዊ ሁኔታ ሲታይ ደግሞ ይህ የተገላቢጦሽ ነው፡፡  በጎች ከፊት እረኞች ከኃላ ይከተላሉና፡፡የእስራኤላዊያን በጎች እረኛውም በጎቹን ጠንቅቆ ያውቃቸዋል፡፡ በሥም በሥማቸው ይጠራቸዋል በጎቹም ድምፁን ያውቃሉ እረኛቸውን ያውቁታል እርሱ ካሰማራቸው ሥፍራ ወደየትም ሥፍራ አይሄዱም ወደ ሌላ ክልል በመግባት እረኛቸውን አምቧጓሮ ውስጥ አይከቱትም እረኛቸውም ከለምለም መሥክ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ስለሚያውላቸው አይራቡም አይጠሙም ኢትዮጵያውያን በጎችና እረኞች ግን ከዚህ ሁኔታ እጅግ የፀዱ ናቸው በጎችም በግ አይደሉም እረኛውም እረኛ አይደለም እንኳንስ በጎቹ እረኛውም በጎችም በግ አይደሉም እረኛውም  በጎቹን በሥማቸው ሊጠራቸውና ሊለያቸው ይቅርና ጭራሹን በጎቹም እረኛቸውን አይከተሉም እረኛም የሌላቸው ይመስል ያጠራጥራሉ መዋያ ለምለም መሥክም የላቸውም፡፡  የበግም ጠባይ የላቸውም እንደ ፍየል ይቅበዘባዛሉ እንጂ፡፡
እስራኤላዊ እረኛ በጎቹን ሲመራ መንገድ ሲያመላክት ከለምለም መስክ ከንፁህ መጠጥ ሥፍራ ሲያደርስ ኢትዮጵያዊ በግ በተራው የተገላቢጦሽ እረኛውን ይመራል በጉ እረኛውን የሚያደርስበት ግብ (Goal)ሥለሌለው እርሱ ሳሩን ሲግጥ እንደ ፍየል ቅጠል ሲቀነጥስ እረኛው ከመንገድ ይቀራል በጎችም ጫካ ይገባሉ እረኛ የላቸውምና መሪያቸው መንገድ ሥቶ ቀርቷልና ተኩላና ቀበሮ አንድ እያሉ በልተው ይጨርሷቸዋል፡፡
    መጽሐፍ የምድሩ ለሰማዩ ምሳሌ ነው እንዲል የኢትዮጵያውን በጎች ህይወት ለኢትዮጵያውን ምዕመናን ኑሮ ምሳሌ የሆነ የሚመስልበት ጊዜ እሩቅ አይደለም፡፡ የቀደሙ የንፁሐን አባቶቻችን አምላክ ትጉሕ የማያንቀላፋ መልካም እረኛችን ልዑል ባህርይ እግዚአብሔር ካልታደገን በስተቀር አሥራት አድርጐ ለእናቱ የሰጣትን ይህቺን አገር እግዚአብሔር ያለ መሪ፣ ያለእረኛ፣ ያለጠባቂ አያስቀራት፡፡ የስላሌው ሀገረ ስብከት  የስብከት ወንጌል ኃላፊ እና ሰባኬ ወንጌል የነበሩት ነፍሳቸውን እግዚአብሔር በገነት ያኑርልንና መጋቢ ምሥጢረ አባ ወርቅነህ ውቤ እንዲህ ይሉ ነበር ‘’ድሮ ፈረሱ ጋሪውን ይጐትት ነበር ዛሬ፣ ዛሬ ግን ጋሪው ፈረሱን መጐተት ጀምሮአል’’ እንዲህ ከመሆን ይጠብቀን፡፡ አባት፣ መምህር፣ ካህን፣ጳጳስ፣ ሊቀጳጳስ፣ፓትሪያሪክ፣አያሳጣን፡፡  ወደነው አብረን ኖረን ሲለየን የሚያሳዝነን እንጂ የምናዝንበት፡ እሰይ ተገላገልን፣ ነቀለልን፣……. እያልን የምንለው ይነሳልን ብለን ሰላማዊ ሰለፍ የምንወጣበት ሳይሆን ሲመጣ መጣልን ብለን የምንቀበለው ሲሄድ ሄደብን ብለን በጸሎት በምሥጋና የምንሸኘው አባት ይስጠን፡፡  በለመለመ መሥክ ሰብስቦ የቃሉን ወተት እየመገበ የማያሰድገንን ለንስሐና ለሥጋ-ወደሙ የሚያበቃንን አባት አያሳጣን የተሰበሰበን ከሚበትን፣ ለተኩላ አሳልፎ ከሚሰጥ፣የተኩላ ካባ ደርቦ ከበጎች መሐል ከሚገባ ነጣቂ ተኩላ ይሠውረን፣ ከማስታረቅ ይልቅ ፀብ አጫሪ፣ ፀብ ያለሽ በደቦ ከሆነ ይጠብቀን፡፡
ሃብተወልድና  ሥመ-ክርስትናን ካገኘንባት፣ በክርስቶስ ደም ከተመሰረተች ከቅድስት ቤተክርስቲያን ፀንተን እንድንቆይ የሚያደርጉ እረኞች አስተደዳሪዎችን ካህናትና ሰባኪዎችን…….. እግዚአብሔር ያድለን፡፡
     ምነው እነዲህ ለማለት በቃህ ትሉ ይሆናሉ አዎ ነገርን ነገር ያመጣዋልና በባለፈው የምሥራቁ ፀሐይ በሚል የግብፁን 117ኛፓትሪያሪክ ሲኖዳ 3ኛ እረፍተ ሥጋ አሥመልክቶ በፃፍኩት በመነሳት የተቀጣጠለው መንፈሳዊ እሳት ወላፈን ገረፈኝ ለዚያ ነው እንዲህ ለማለት የናፈኩት፡፡    እኚህ ሰው ኢትዮጵያዊ አይደሉም ወይ እንደ ጥነቱ ግብፅ ጳጳስ አትልክልን ወይንም እስከዚህ ወደ ኢትዮጵያ በየጊዜው እየተመላለሱ አልባረኩን አላስተማሩን ታዲያ ምነው በኢትዮጵያውያን ልብ እንዲህ ሠረፁ ሞታቸው እንዲህ አንገታችንን አስደፋን ሐዘናችንስ እንዲህ በረታ አነጋጋሪስ ጉዳይ ለምን ሆነ፣ እንደሆነ ሰው ሟች ነው አልኩና ራሴን መረመርኩት አንድ ነገር ልቤን ነካኝ ሌላ ምንም አይደለም  እውነተኛ የበጎች እረኛ ሥለነበሩ፣ በጎቻቸውን ምዕመናንን በአግባቡ ሥለሚመሩ፣ስለበጎቻቸው ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ እውነተኛ አባት ስለነበሩ በጎቻቸውን ከለምለም መስክ ከንፁህ የመጠጥ ውሃ ሥፍራ ሥለሚያውሏቸው ብዙ መፃህፍትን ፅፈው ለዓለም ያተረፋ ቃለ እግዚአብሔርን ያስተማሩ የተጣላ ያስታረቁ በፆምና  በፀሎት የጉ ያለ ሐሜትና ያለ ውዳሴ ክብር የእግዚአብሔር አገልጋይ በመሆናቸው በእውነት ያለ ሐሰት አምላካቸውን ያገለገሉ በመሆናቸው ነው በዚያ አረማዊ በበዛበት ፈተናው በጠነከረበትና መውጫ መግቢያቸው በጠበባት አገር በማፅናናትና በመንፈሳዊ ህይወት በማትጋት ለ88 ዓመታት በመትጋታቸው ነው፣…… ሌላ ምንም አይደለም  አለኝ ውስጤ ራሴን ጥያቄዬን ሲመልስልኝ ለዚህም ነው ያለቀሰ ነው ያዘነው መንፈሳዊ ቅናት አንገብግቦኝ ታዲያ ኢትዮጵያዊው ምዕመን ምነው እረኛ አልባ ሆነ የቅዱስ ጴጥሮስ ምትክ በጎቹን የሚያስማራ ጠቦቶቹን የሚጠብቅ ኢትዮጵያ ምነሙ አጣች ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዝረጋለች የተባለው ለከንቱ ነውን አይደለም እናንተ እሰራኤልያውያን እንደ ኢትዮጵያውን ከቶ አትሆኑልኝም ያለን እግዚአብሔር ያለ እረኛ፣ ያለመሪ፣ያለአስተዳዳሪ፣ ሊያስቀረን ይሆን አይደለም፡፡  አምላካችን በቃለ የታመነ አምላክ ነውና፡፡
     ታዲያ ይኼ ለራሱ ላልሆነ ወገን እንባውን የሚራጭ፣ ደረቱን የሚደቃ አንገቱን በሐዘን የሚደፋ ምዕመን ምነው እውነተኛ እረኛ አጣ ከፊት ለፈት እየሄደ መንገድ የሚመራው መሥዋዕትንትን እየተቀበለ ለመሥዋዕትነት የሚያተጋው ፀንቶ የሚያፀናው ታምኖ እንዲታመን የሚያደርግው ቤተክርስቲያንን ጠብቆ ለተተኪ የሚያስረክብ፣ ከውስጥ እና ከውጭ ጠላት የሚጠብቃት እረኛ ምነው ቤተክርስቲያን  አጣች ልጆቿስ ሥለምን በዱር እንዲባዝኑና እንደቅበዘበዙ ሆኑ ቤት እንደሌላቸውስ ሆነው ከደጅ ሲቀሩ እገዲአብሔር ተመልክቶ ዝር አለ
1.   ምዕመኑ በራሱ በዚህ ዓለም ሲኖር እነደ አርግብ የዋህ እንደ ዕባብ ብልህ  መሆን ስላቃተውና ጅልና ተንኮለኛ ስለሆነ እግዚአብሔር ከጥፋቱ ሊመልሰው
2.  ምዕመኑ ራሱ በግ የመሆኑን ጠባይ ትተ ለእረኛው አስቸጋሪ ፍየል ሥለሆነ እግዚአብሔር ሲቆጣ በትር አያነሳምና  ወደ ራሳችን ልቡና እስክንመለስና ንስሐ እስክንገባ እረኞቹ ከፊታችን ገለል በማድረግ የሌሉ አስመሰላቸው እንጂ እግዚአብሄር ልጆቹን እነዲሁ አይጥልም የሚታይ እረኛ ባይኖር በሥውር ይጠብቃቸዋልና፡፡
3.  እረኛው በጎቹን ለተኩላና ለቀበሮ ትቶ ሲሄድ አስደንግጦ ከሚመልሰው በጎቹን ራሱ እየታደጋቸው እረኞቹን እስኪመለሱ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በመንገድ ይከተላቸዋል፣ መልሶም በጎቹን ከመንጋው እረኛውንም ከሙያው ይመልሰዋል ትዕግሥቱ ብዙ ነውና፡፡
4.  ይሁዳን ከ12ቱ ሐዋሪያት ዕድል ፈንታ ፅዋ ተርታ ቢያስገባው ፈጣሪውን በ 30 ብር ሽጦ እንደተለየ በርሱ እግርም ማትያስን እንደተከ እንዲሁ በነዚህ እረኞች ፈንታ እተካለሁ ሲል አንድም የእናንተ ዋጋችሁ በከንቱ አይቀርም ሲል ነው
5.  በጎችን ቢሰትኑና ሲበጠብጡ ዝምታው የትዕግሥቱን ብዙት ምህረት ቸርነቱ እስከምን ድረስ እንደሆነ ለንስሐም ምን ያህል ጊዜ እንደጠበቀን ለማሳወቅ ወዘተ ሲሆን ታዲያ የኛ አባቶች ፣ የኛ መምህራን ፣የኛ የቤተክርስቲያን እና የቤተክህነት አሥተዳዳሪዎች ከእግዚአብሔር መንግሥት ይልቅ የዚህ ዓለም ነገር ለምን ታያቸው ለምንስ እንደ ዴማስ በዚህች ዓለም ማብረቅረቅ ተታለሉ ያለዋጋ በከንቲ የማይተው አምላክ እያላቸው በ12ቱ የፍርድ ወንበር ላይ የማስቀመጥ ሥልጣን የሚሰጥ ኃይል ጌታ እያላቸው ለዚህች ዓለም ሀብት ንብረት ፣ሥልጣን ሹመት ሽልማት ምነው ተማረኩ በፍቅር የሚወደን ይህን ህዝብ ሥለምን ያለጠባቂ አስቀሩት ለምንስ ተነሱልን፣ሂዱልን፣ አትምጡብኝ እያለ ምሬቱንና ሐዙኑን በአደባባይ እሰኪገልጥ አስመረሩት ነጣቂ ተኩላዎች ከመንጋው መሐል ገብትው ሲያምሱ እነዴት በሩን ከፍተው ዝም አሉ እንዴትስ ሲያተራምሱ ዝም ለማለት ታገሱ በርባን ይፈታ ኢየሱስ ይሰቀል ዓይነት ፍርድ ሲጓደለ ንፁሐን ሲታሰሩ ተኩላዎች እንደበግ ሲቆጠሩና የተኩላዎች ካባ ሳይገለጥ የበጎች ቆዳ ሲገፈፍ እንዴት አስቻላቸው
ሐሰተኞች እንዴት በጥቂት ድምፅ አሸነፋ የእውነት ድምፅ ወዴት ገባ የሐሰተኞች መስካሪዎች ኃይላቸው እንደምን በረታ ምንውስ ፍርድ ተዛባ አባቶቻችን ክብራቸው በነውራቸው ምነው ሆነብን ሃሳባቸውስ ሥለምን ምድራዋና አላማዊ ሃብት ንብረት ሥልጣን ዝና ጥቅም ክብር ሆነ የኛ ግፍ ነው ወይስ የነርሱ በደል
ጌታ ሆይ እኛን በጎች አድርገን እውነተኛ የበግ ጠባቂም ስጠን አሜን፡፡  እረኞቻችን ከግብፁ አቡነ ሲኖዳ ሳልሳዊ ምን ይማሩ ይሆን ምንስ መማር አለባቸው እኛ በጎችስ ከግብፃዊያነ ምዕመናን  ምን መማር ይጠበቅብን ይሆን እረኞቻችን አኛን በየትኛው መስክ ሊያሰማሩን ይገባል መን ከፊት ይምራ ማንስ ከኃላ መከተል አለብት እግዚአብሔር  በጎቹን ያለ እረኛ ለምን ተዋቸው  እነዚህንና ሌሎችንም ጉዳዮች በማንሳት እንወያይበት አሥተያየቶቻችሁን ፃፋልኝ፡፡
አሁንም ደግሜ እላለሁ የበጎች መልካም እረኛ የነበሩትን የግብፁን ፓትሪያሪክ አቡነ ሲኖዳን እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን በእቅፍ ያኑርልን ለግብፃውያንም መፅናናትን ያድልልን መልካም እረኛም ይሥጥልን አሜን:: ይቆየን፡፡

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...