"ሌላ ትምክህት ከእኔ
ይራቅ" ገላትያ 6÷14
ይህን መልእክት የጻፈልን ከሐዋርያት ጋር ለሐዋርያነት
ያልተመረጠው ይልቁን ሐዋርያትን በማሳደድ የሚተባበረው ከሐዋርያት መካከል እንደ አንዱ የሚቆጠረው ቅዱስ ጳውሎስ ነው።
መልዕክቱ የተጻፈው በገላትያ ቤተክርስቲያን ለሚገኙ
ምዕመናን ነው። ገላትያ፦ ቱርክ ውስጥ የምትገኝ አንድ አውራጃ ነች።
ቱርክ ቅዱስ ጳውሎስ ለወንጌል አገልግሎት ሲሰማራ
ካገኛቸው ከተሞች አንዷ ነች።
በገላትያ የሚገኙ አብያተክርስቲያናት በቅዱስ
ጳውሎስ የተመሰረቱ ናቸው።
የገላትያ ሰዎች ቅዱስ ጳውሎስ አስተምሯቸው ከሄደ
በኋላ ካስተማራቸው ትምህርት ቢያፈገፍጉም (ስለግርዘት ተምረው ነበረ ያፈገፈጉት) በመጨረሻም ተጸጽተው ተመልሰዋል።
ይህ መልዕክት የመጀመሪያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት
እንዳልሆነ ይነገራል። መልዕክቱ ጠጠር ያለ እና ከበድ ያለ መልእክት ነው።
የመነሻ ቃላችን ሙሉው እንዲህ ይላል።