ማክሰኞ 18 ማርች 2014

‹‹ቅዳሴ›› ክፍል -2-

አይነጋ የለ ነጋ ጊዜው 1130 ሰዓት ነው የሞላኋት የግድግዳ ሰዓቴ ድምፅ አሰማች እኔም ከእንቅልፌ ነቃሁ ሲረፍድብኝ እንዳላደርኩ ሳይረፍድብኝ ወደ ቅዳሴ ሄድኩ የቀን መዘውሩ ተገባዶ ሌሊቱ ለንጋት ስፍራውን መልቀቁን የተገነዘበ ሕዝበ አዳም ታጥቆ ተነስቷል ፀሐይ የንጋት ብርሃኗን ለመፈንጠቅ ሰማዩን አድርጋዋለች ነጭ ነጠላ የለበሱ ምዕመን መንገዱን ሞልቶታል አብያተ ክርስቲያናት የጥሪ ደውላቸውን (ድምፃቸውን) እያሰሙ ነው ሱቆችም የአሁኗን ንጋት በጥዋፍና ሻማ ዕጣን ሽያጭ ጀምረዋል ነዳያን ቤተክርስቲያን ጌጥ መስለው ከደጇ በረድፍ ተቀምጠዋል አስቀዳሹ እኔም አላረፈድኩም በሚል ስሜት በርጋታ እየተራመድኩ የደጃፉን በር ተሳልሜ ከግቢው ከመግባቴ ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ …›› የሚለውን የካህኑ ድምፅ በዜማ ተሰማኝ ተፈጥሮ ካስዋበው ከቤተክርስቲያኑ አጸድ ሥር ተጠንቅቄ በመቆም እጆቼን ከላይ ሆኖ ወደሚያየኝ አምላክ በማንጋጠጥ ዘረጋሁ ዙሪያው ጭር ያለው ግቢ በምዕመናን እየተጨናነቀ መጣ የቅዳሴውየተሰጥኦዜማ ሥፍራውን የመላዕክት ከተማ ኢዮር፣ ኤረር፣ ራማን አስመስሎታል የዕጣን የሽታ መአዛ ግቢውን አውዶታል ነፍሳችን እጅግ ተደስታለች ቅዳሴውን የሰማይ አዕዋፍ በድምፃቸው አብረው ሲያጅቡት የበለጠውን ውበት ሰጥተውታል የዕጣን ጢስ ወደላይ ማረግ የተመለከተ ልቡናችን አብሮ ከመንበረ ፀባኦት ደርሷል

‹‹ቅዳሴ››

ያለው ዕለት ለንጋቱ ቦታውን ለመልቀቅ መሰናዶውን ያጠናቀቀ ይመስላል በቤቴ መስኮት ቀዳዳ የሚገባው የንጋት ብርሃንነግቷል ተነስ” ሚል ሰው ያህል ከፊት ለፊት በቀዳዳው እየገባ ይጎነትለኛል የጭላንጭሉን ብርሃን ተልዕኮ የሚያጨናግፈው ድብርትአይዞህ ተኛ ገና ነው” እያለ ያዘናጋኛል፤ አሁንም በመስኮቱ የሚገባው የብርሃን ጭላንጭል ገብቶ ገብቶ ቤቱን በሰፊው ተቆጣጥሮታል፣ አካላቴ ሁሉ ሳምንቱን መንገድ ሲጓዝ እንደከረመ አንጓዎቼ በሙሉ መዛል ስሜት ይሰማባቸዋል፡፡ ከሁለቱ አንደኛዋ አይኔ ብቻ ብርታት ይሰማታል እንጂ ሁለተኛዋ ጭራሽ የለችም ማለት ይችላል፤ አንደኛው ሲተኛ እርሷ ነቅታለች እርሱን ለመቀስቀስ ባደረገችው ጥረት እርሷም ድካም ተሰምቷት ማሸለብ ጀመረች የሌላት ልብሴን ገላልጣ ለመውጣት ጡንቻዋን ያፈረጠመችው ክንዴ ብርድ ሲያኮማትራት ተመልሳ ከብርድልብሱ ሾልካ ገባች ገና ተመኝታ የተገናኘች ይመስል እንቅልፍ ጣማት በዚያቹ በቀጫጫ ክንዷ ራሷን በራሷ እቅፍ አድርጋ ጋደም እንዳለች የእንቅልፍ ማዕበል ይዟት ጥርግ አለ፡፡ በልቦናዋ በብርቱው ምሽት ያሰበችው የዕለት ሰንበት የቅዳሴ መርሃግብርና ጠዋት በብርሃኑ ጭላንጭል መካከል ትዝ ላት ልቡናዋን እንደብል በልቶ ጨርሷታል ሰውነቴ ለእንቅልፍ ተማርካ ከሞቀው መኝታዋ በመሆን ቅዳሴን ታስቀድስ ጀመር፤ ልክ ከመቅደሱ ፊት እንደቆመ አስቀዳሽ አሁን ለዛለችው ገላዬ ንፍቁ ዲቆኑጸልዩ በእንተ ያበውኡ መባእ …” የሚለውን አዚሞ ሕዝቡምተወከፍ መባኦሙ ለአኃው” የሚለውን ጨርሶ ዲያቆኑ በድጋሜስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት” ብሏል የዛለው ገላዬምቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሐከ” ብላ ሰግዳለች

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...