እሑድ 15 ጁላይ 2012

ትላንትንፈለኩት


አንዳንዴምናለ? ትላንት ተመልሶ
እንግዳ በሆነ
ህመምቁርጥማቴን መጥቶ በጠየቀኝ፣
                                                        ሆድብሶቴን አይቶ
እንባዬን ባበሰኝ፣
ያጣሁትንተስፋ መልሶ በሰጠኝ፡፡
እነግረው ነበረ ፀፀቴን ቁጭቴን፣
ሥህተቴን ውድቀቴን፣
ያንድቀን መዘዜን፣
በዚያው እንዲተወኝ ፣
                    ለዛሬ አሻግሮ በፀፀትይገድለኝ፡፡
visit us again!

ሰኞ 23 ኤፕሪል 2012

ሐሙስ 19 ኤፕሪል 2012

ውረድ


ተው ተው ሲሉህ
 ሲያፈራሩህ
አቅማቸውን አተው
ማንነትህን ዘንግተው
አቅራሩ ሸለሉ
ፎከሩ
ፍጥረት በሙሉ
አንድም ሳይቀሩ
ለአመድ ባንድነት
ለትርፍ ሳይሆን ለጉድለት/ለክስረት/
ተው ተው እያለሁ
እያስፈራሩህ
ውረድ ወይ ፍረድ
ብለው ተሳለቁብህ
ትወርዳለህ ወይስ ትፈርዳለህ?
ቅል ልመናውን ለማያውቅ ፍርዱ
አዕምሮ መስጠት ነው
በትዕግሥት ማለፍ ነው
የፈጣሪ/ የአባት ልምዱ
እላለሁ
አትውረድ
አትፍረድ
ይቅር በለኝ እንጂ
በምህረትህ እንድንዋጅ
ተው ተው ተው አለህ
በመፍጠርህ ሊያስቆጩህ
22/01/03
ደረሰ ረታ
visit us again!

ሰኞ 9 ኤፕሪል 2012

Deresse Reta's Views የደረሰ ረታ እይታዎች: ‘’Disqualify’’

Deresse Reta's Views የደረሰ ረታ እይታዎች: ‘’Disqualify’’: Disqualify   የሚለው ቃል የእንግሊዝኛ ቃል ሲሆን ‘’verb’’ ወይም ግስ ብለን የምንጠራው ሲሆን መዝገበ ቃላት ‘’to put out of a competition’’   ወይም ‘ ’to make unfit for...

ቅዳሜ 7 ኤፕሪል 2012

‹‹የዱር አራዊቶች አቤቱታ››

coming soon.

‹‹ሰባት ቢሊዮን››


ዛሬ ዛሬ ነገሮችን በሚሊዮን አይደለም በቢሊየን መቁጠር ይህንን ያህል ገረሜታን የሚፈጥር አይደለም፤ ሁሉም ነገሮች እጅግ በፍጥነት እያሻቀቡ ከመሆናቸው የተነሳ ቁጥራቸው ጨምሯል የሰው ልጅ ቁጥር እየጨመረ ለሰው ልጆች መሠረታዊ የሚባሉ ነገሮች እየቀነሱ፣ የዓለም ኢኮኖሚ እየጨመረ የነፍስ ወከፍ ገቢ እየቀነሰ፣ በዓለም ላይ ቋንቋዎች እየጨመሩ መግባባት እየቀነሰ …. መጥቷል፡፡ በአስገራሚ ሁኔታ የዓለም ህዝብ ቁጥር በፍጥነት መጨመሩን የዓለም መገናኛ ብዙኋን፣ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች፣ የዓለም መንግሥታት፣ የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸው ሁሉ (ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ የማይመለከተው ሠው የለም) የቁጥሩ መጨመር ካለን የዕድገት ደረጃ፣ ከሚጨምረው የቁጥር መጠንና በዓለም ላይ ካንዠራበበው የሙቀት መጠን መጨመር፣ የነፍስ ወከፍ ገቢያችን ሥጋት አንፃር አሉታዊ ተጽዕኖዎች እንዳሉት ያመላክታል በአንፃሩም የአምራች ኃይል በብዛት መኖር የተጠቀሱትን አስከፊ ነገሮች ሁሉ በአዎንታዊው ገጽ ሊቀይረው እንደሚችል እሙን ነው፡፡
     ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም የዓለም ህዝብ ሰባት ቢሊዮን ይሆናል ተብሎ ተገምቷል ይህ ቁጥር በእያንዳንዳችን ጆሮ ሲሰማ ምን ይመስለናል? ምንስ እናስባለን? ያኔ ከዛሬ ብዙ ዓመታት በፊት ዓለም ሲፈጠር ብቻውን የነበረው አዳም፣ ብቻውን መሆን መልካም አይደለም ተብላ የተፈጠረችው ሴት የአዳም ውድ ባለቤቱ ሔዋን ምን ይሉ ይሆን? የሃላፊያትንና የመፃኢያትን ጊዜ ጠንቅቆ የሚያውቅ እግዚአብሔር እንደ ሰው ቢሆንና ‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት›› ያለው ትዛዙን ሞልተን እንዲህ ሰባት ቢልየን ሰዎች ስንሆን ሰው ቢሆን ኖሮ ምን ይል ነበር? አዳምና ሔዋን እነዚህን ሰባት ቢሊዮን ህዝብ እንደ ወላጅ ዛሬም በህይወት ኖረው ቢያስተዳድሩን ምን ይሆኑ ነበር?
     እስኪ ወደ ቁምነገሩ እንመለስ በተለያዩ የዓለም አገራት መንግሥት የህዝብ መጨመር ሥጋት ውስጥ ስለከተታቸው ህዝባቸው እንዳይራብ መሠረታዊ ነገሮችን በማጣት እንዳይጎዳ የቤተሰባቸውን መጠን እንዲቀንሱ አልፎ አልፎም የቁጥሩን መጠን በመገደብ ህዝቡን ያስተዳድራሉ፤ ከዚህም አልፎ በጤና ተቋማት በመገናኛ ብዙኅን በተለያዩ አጋጣሚዎች የቤተሰብ ምጣኔን ያስተምራል፡፡ እኛስ የቤተሰባችንን ቁጥር መጠን በዕቅድ ነው በአጋጣሚ የምንወስነው? የዓለም መንግሥታት የዓለምን ህዝብ ቁጥ በበጎ አመለካከት ለመቀነስ ከሚያደርጉት ጎን ለጎን በአሰቃቂ ሁኔታ አስከፊ በሽታዎች የዓለምን ህዝብ እየቀጠፉት ይገኛሉ፤ ይኼ ብቻ አይደለም ጦርነቶች፣ ድርቆች፣ የምግብና የንፁህ መጠጥ እጦት፣ ድንገተኛ አደጋዎች ለምሳሌ፡- የመሬት መንሸራተት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ እሳተጎመራ፣ የህንፃዎች መናድ፣ የእሳት ቃጠሎ፣ ተላላፊ በሽታዎች ወዘተ… የዓለምን ህዝብ ቁጥር በፍጥነት እየቀነሱ ይገኛሉ መብዛት እንዳለ መቀነስ፣ መፈጠር እንዳለ መሞት፣ ባይኖር ኖሮ የዓለም ህዝብ ቁጥር ስንት ይሆን ነበር? ዛሬ ሰባት ቢልየን ሆንን የዛሬ ዓመት ስንት እንሆን ይሆን? የዛሬ አሥርና ሃያ ዓመትስ?
     ሰባት ቢሊዮን መሆናችን ብቻ አይደለም የሚገርመው ብዙ አይነት ህዝቦች እዚህ ቁጥር ውስጥ መካተታቸውም እንጂ ቅሩበ እግዚአብሔር የሆኑ ፃድቃን፣ የዓለምን በደል የሚያፀኑ ግፈኞች፣ ራሳቸውን አሸባሪ እያሉ የሰየሙ በቡድን የተደራጁ፣ ርህሩሆች፣ ጨካኞች፣ የዕለት ጉርሳቸውን የዓመት ልብሳቸውን ለማሟላት በቅንነት ደፋ ቀና የሚሉ ሚሊዮኖች፣ ሽፍቶች፣ አጭበርባሪዎች፣ ደጋግ ህዝቦች፣ አምባገነን መሪዎች፣ የሃይማኖት ሰዎችና እምነት አልባዎች ወዘተ … እነዚህ ሁሉ ይህንን ሰባት ቢልየን ቁጥር መጋረታቸው የሚደንቀው አንዱ ገፅታው ነው፡፡ እስኪ ለአንድ አፍታ ይኸ ሁሉ ህዝብ አንድ ፆታ አንድ ብሔር አንድ ቋንቋ አንድ ገጽታ አንድ አይነት ቁመትና ተክለቁመና አንድ አይነት ባህርይ አንድ መሪ ወዘተ… ቢኖረው ብላችሁ አስቡት እግረ መንገዳችሁን ይኸንን ሁሉ ያላማካሪ እንዲህ ውብ አድርጎ የፈጠራና የሚገዛ የሚመግብ እግዚአብሔርን ሥራህ ዕፁብ ድንቅ ብለን እናመሰግነው፡፡

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...