*. ብዙዎች ስለ ዘራቸው እምነታቸውን ዘንግተዋል፣
*. ብዙዎች ስለ ፖለቲካ ሲሉ እምነታቸው ላልቷል፣
*. ብዙዎች ስለ ጥቂት ብዙ ነገር አጥተዋል፣
*. ብዙዎች የእምነት ጥንካሬያቸውን ስለ እምነት ተቋም ይዞታቸው ገብረዋል፣
*. ብዙዎቹ በየቡድናቸው ስለ መደጋገፍ እውነትን፣ እምነትን፣ ሐቅን፣ በቁሟ ቀብረዋታል፣
*. ብዙዎች ስለ እኔን ይድላኝ፣ የኔ ይቅደም፣ የኔ ይብለጥ አገርን ወደኋላ አስቀርተዋል፣
*. ብዙዎች ስለ ምድራዊው ነገር ሰማያዊ ነገራቸውን በጥቅም አስይዘዋል፣
*. ብዙ የእምነት አባቶች የምእመኖቿ መሪ ሣይሆን የምድር ርስት ጉልት ይጨነቃሉ፣
*. ብዙዎች የሚሰባሰቡት ከአንድ ሁለት ስለሚሻል ሳይሆን ከዘርህ ዘሬ፣ ከባህልህ ባህሌ፣ ከሐይማኖትህ ሐይማኖቴ፣ ከፖለቲካህ ፖለቲካዬ፣ ከድርጅትህ ድርጅቴ ይበልጣል ብለው ነው፣
*. ብዙዎች ስለውጫዊ ልዩነታቸው ውስጣዊ አንድነታቸውን ክደዋል፣
*. ብዙዎች ብዙ በጎ ነገርህን ቀብረው በጥቂቱ ስተትህ ሐዘን ተቀምጠዋል፣
*. ብዙውች ለመከባበር ቦታ ነፍገው መቻቻል አንግሰዋል፣
*. ብዙዎች በራስ መንገድ ከማሰብ በቡድን ማሰብ ተጸናውቷቸዋል፣
*. ብዙዎች እውነትን ሳይሆን ሰወችን በመከተል ዘመናቸውን ይጨርሳሉ፣
*. ብዙዎች በጋራ መውደድ እና በጋራ በመጥላት ተጠልፈዋል፣