መፅሐፍ ስለምርኮ በሚናገረዉ በዘመኑ ስለተደረጉት
ዋና ዋና ድርጊቶች ሲተርክ በባቢሎን በስደት መኖርን ሲያነሳ ታላላቅ ሰዎች ብሎ ካነሳቸዉ መካከል ሕዝቅኤልና ዳንኤል ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡
ብልጣሶር፡- ትርጉሙ ቤል (የባቢሎን ጣኦት) ንጉሥን ይጠብቀዉ ማለት ነዉ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ
46÷1
1)
የናቡከደነፆር የልጅ ልጅ
የናቡናዲስ ልጅ፡፡ የአዲሲቱ ባቢሎን መንግሥት የመጨረሻ ንጉሥ፡፡
በመጠጥ ግብዣ ጊዜ በቤቱ ግንብ ላይ ፅሕፈት
የምትፅፍ እጅ ታያቸዉ ፅሕፈቱም ፡- ̎ማኔ ቴቄል ፋሬስ̎ የሚልነበረ፡፡
ንጉሡም ደንግጦ ትርጉሙን ሲፈልግ ዳንኤል እንዲህ
ብሎ ተረጎመለት፡፡
̎ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቆጠረዉ፣ ፈፀመዉ፣
በሚዛን ተመዝነህ ቀለህ ተገኘህ፤ መንግሥትህም ተከፈለ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ፡፡̎ ዳንኤል 5÷25-28
በዚያ ሌሊት የባቢሎን መንግሥት በፋርስ እጅ
ወደቀ፡፡ ይህም የሆነዉ በ539 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነዉ፡፡ ዳንኤል 5÷1-30፣ 8÷1
2)
ለዳንኤልም የተሰጠ ሥም ነዉ፡፡
ዳንኤል 1÷7 በሥም እኩል በግብር ሥንኩል ማለት እንዲህ ነዉ፡፡
ዳንኤል ማን ነዉ?
የስሙ ትርጓሜ ፡- ̎ እግዚአብሔር ፈራጅ ነዉ̎ ማለት ሲሆን
ትዉልዱ፡-
መጻሕፍት እንደሚሉት የተወለደዉ በ618
ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ትዉልዱም ከይሁዳ ነገድ ስለሆነ ከንጉሳዊ/ከመሳፍንት
ቤተሰብ እንደሆነ ይገመታል፤ የዮናኪር የልጅ ልጅ ነዉና፡፡ ምነዉ ቢሉ ዮናኪር የንጉሡ የኢዮአቄም (የእስራኤል ንጉሥ) ልጅ ስለሆነ፡፡
የኢዮአቄም ዘመነ ንግሥናዉም ከ609 እስከ 598 ከክርስቶስ ልደት በፊት ማለት ሲሆን የነገሠዉም በ18 አመቱ እንደሆነ ይነገራል፡፡
አንዳንዶችም በ25 አመቱ እንደነገሠ ይናገራሉ፡፡ ዳንኤል ግን መሾሙን መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ዳንኤል 1÷6