ነገሩ እንዲህ ነዉ ወደ ስራ ገበታችን ለመሄድ ለገሃር ባቡር ጣቢያ የከተማ አዉቶቡስ እየጠበቅን እንገኛለን፤ 36 ቁጥር
ያለወትሮዋ በጣም ከማርፈድዋ የተነሳ መሰላቸትም ድካምም ይታይብናል አንድ ልጅ'ግር ከሰልፉ መካከል ደክሞኛልና
አረፍ ልበል በማለት ከፊቱና ከኋላዉ ላሉት ወረፋ ጠባቂዎች አሳዉቆ እዛዉ አከባቢ ድንጋይ ላይ አረፍ አለ፡፡ ሰልፉ እጅግ እየረዘመ
ከመሄዱ የተነሳ አንድ አዉቶቡስ ብቻ የሚችለዉ አይመስልም ነበር፡፡
ቀርታ አልቀረችም ተስፋ ቆርጠን ሳናበቃ መጣች፤ ሁሉም ኪሱን ፣ ቦርሳዉን ፣ …. መፈታተሸ ጀመረ ተልመጥምጦ የነበረዉ
ሰልፍ ቀጥ አለ፤ ፀጥታ ነግሶበት የነበረዉ ስፍራ አዉራዉ እንደተነካ የንብ መንጋ ታወከ፡፡ ቲኬት ቆራጩ ጎልማሳ እስክርቢቶዉን ከደረት
ኪሱ አዉጥቶ ጆሮግንዱ ላይ ሻጥ አድርጎ ሰልፉን እኩል ገምሶ ጀብነን ብሎ ቆመ፡፡ ሰዉ ከቅድሙ ይልቅ ደሙፈላ፣ በዉስጣቸዉ ማጉረምረም
የጀመሩትን ሳንቲም አምጡ አታምጡ ላይ ንትርኩ ጨመረ፡፡ በዚህ መካከል ያ ወጣት ወደሰልፉ ተመለሰ ከኋላ ከረጅም ርቀት ላይ ከሰልፉ
ሌላኛዉ ጠርዝ ላይ "ተመለስ" የሚል ጩኸት ሰልፉን ድንጋጤ ፈጠረበት፤
ሁልም ሰዉ ድምፁ ወደ ተፈጠረበት አቅጣጫ አይኑን ላከ ሰዉየዉ እየተንደረደሩ
ሲመጡ ጤነኛ አይመስሉም ነበር፡፡"ዉጣ ብዬሃለዉ ዉጣ!"
ጩኸቱ በረታ፣
እስከዚህ ሰዓት የጉዳዩ ባለቤት ጉዳዩን ልብ አላለዉም እጁን ሳንቲም ካስቀመጠበት ኪሱ ከቶ እያለ ክንዱን አፈፍ አርገዉ ያዙት ….
በድንጋጤ እጁን እንኳን ሳያወጣ ደርቆ ቀረ፡፡ "ዉጣ! ባለጌ! እኛ እዚህ ቆመን
የማነህ ፈጣጣ ከየትም መጥተህ ዘዉ የምትለዉ?"
እኔ ነዉ?
"ከአንተ ጋር እያወራሁ እኔ ነዉ ትላለህ ? ደፋር! "
ምን አደረኩ?
" ዉጣ ሰልፉን አትረብሽ"
ለምን?
" ሰዉዬ ነግሬሃለዉ በሰላም እንሂድበት ሰልፉን አትረብሽብን"
ሰዉየዉ እጅግ ትልቅ ከመሆናቸዉም የተነሳ አብዝቶ መናገርም "ባህላችን "
ስላልሆነ ለረጅም
ሰከንዶች ዝምታን መረጠ ሰልፉ ግን ስራዉን አላቆመም ልጁም ወደፊት ሰዉየዉም ሰልፉን እየታከኩ ፣ልጁን እየተሳደቡ እና እያመናጨቁ
ወደፊት እያመሩ ነዉ፤
ከሰልፉ ኋለኛዉ ክፍል እንደገና በዕድሜ የሚቀርቧቸዉ ሰዉ " እስካሁን ሰማኖት ልጁወረፋዉ ነዉ
እርሶ ወደ ቦታዎ ይመለሱ"
"ይቺ ደሞ ምን ትላለች? አንቺ ደሞ ምንሽ ተነካ?"
"ምንም አልሆንኩ! ልጅ ከሁላችን በፊት እዚህ ቆሞ ነበር ደከመዉ ከፊትለፊቱና
ከኋላዉ ላሉት አሳዉቆ አረፍ አለ፤ ተራዉ ሲደርስ መጣ አንተ ምን ቤት ነህ ከኋላዉ መተህ ቡራከረዩ የምትለዉ? ዉጣ!"ልጁ ልቡ ተረጋጋ ስድቡና አላስፈላጊዉ
ትችት ከርሱ ላይ ዘወር አለለት፡፡
ሰዉየዉ ግን አሁንም ሊበርዱ አልቻሉም ፤ ልጅየዉ ጎረቤቱ የሆነች ልጅ ታማ ሆስፒታል አድሮ ነዉ የመጣዉ ምንም እንኳን
እንቅልፉም ድካሙም ቢኖርበት ስራ ስለነበረዉ ላለመቅረት ነበር ወደ ስራዉ ለመሄድ አዉቶቡስ እየጠበቀ የነበረዉ እና ሰልፍ ላይ ይህ
ችግር የተፈጠረዉ፡፡
አባባ አላቸዉ፤ እኔኮ እያጭበረበርኩ አይደለም ተሰልፌ ነበር ሲደክመኝ አረፍ ለማለት አስፈቅጄ ነዉ የሄድኩት እባክዎ በኔ የተነሳ አይጣሉ፡፡
"ዝም በል! አይናዉጣ!"
በቃ! እንዲያዉም ይሄ ሁሉ ፀብ እንዲህ ደክሞኝ እና እንቅልፍ ይዞኝ እያለ ስራዬን አክብሬ ወደ ስራ ገበታዬ ባልኩኝ
ነዉ አይደል? ጥሩ ምክንያት ሆኑኝ በቃ አልሄድም!
አያዉቁኝም አይደል?እኔም ከዛሬ በፊት አይቼዎት አላዉቅም፣ በዕድሜም ሆነ በሰፈር አንገናኝም፣ ጎረቤት ሆነን
ቢሆን ኖሮ ጉድ በፈላ ነበር፤ ነገር ግን ከዛሬ ወዲህ አንገናኝም፡፡ ብዙ ፀቦች አይቼ አዉቃለሁ የእኔ እና የእርስዎ ፀብ ግን ይለያል
ፀብ በደላላ የሚፈልጉ ነዉ የሚመስሉት ለነገሩ ከማይረባ ፍቅር የረባ ጥል ይሻላል፤ሰዉ እንደ እኔ እርሶ የረባ ፀብ ከተጣላ በሰፈር
ሰዉ በሽማግሌ ይታረቃል አስመሳይ ፍቅር ግን ከሆነ እዉነተኛ ፍቅር ሳይፋቀሩ እንዲሁ ያልፋሉ ብሏቸዉ አመስግኖ ጥሏቸዉ ሄደ፡፡
ከማይረባ ፍቅር የረባ ጥል ይሻላል! አለቀ፡፡