ራስን ሁልጊዜ በአሸናፊነት ዙፋን ላይ …
ይህ ዓለም የዉድድር ዓለም እንደመሆኑ መጠን ይበልጡኑ
የሰዉ ልጅ ትልቁን ዉድድር በተሳታፊነት እና በበላይነት ሚናዉን ይወጣል፡፡ ይሁን እንጂ በዉድድሩ ሁሉም በመንፈሰ ጠንካራነትም ሆነ
አልሸነፍ ባይነት መንፈስ መሸነፍን አይወድም፡፡ ሁሌም እርሱ አሸናፊ ቢሆን እና በድል ቢያጠናቅቅ ደስ ይለዋል፡፡ ይሁን እንጂ ዉድድሩ
በአንድ ሰዉ የበላይነት ( አንደኝነት ) መጠናቀቁ ግድ ይላል፡፡ ሆኖም ሁሉም
ሰዉ በአንደኝነት ሊጨርስ ይቻለዋል፤ ጨርሻለሁ ብሎ ማመንም ማሳመንም ይችላል፡፡ እንዴት?
ሁሉም ሰዉ የሥራ ድርሻ እንዳለዉ የታመነ ነዉ፤
ሁሉም ወደ ዉድድሩ የሚገባዉና የአሸናፊነት አክሊሉን ሊደፋ የሚችለዉ እየሰራ ባለዉና በሚሰራዉ መስክ ነዉ፡፡ ማንም ሰዉ አንተ እየሰራህ
ያለዉን ሥራ አንተ በምትሰራዉ መንገድ አይሠራም፣ አልሠራምም፤ ስለዚህ ይህንን ሥራ በምታጠናቅቅበት ሠዓት አሸናፊዉ አንተ ነህና፡፡
ተወዳዳሪህን ባታሸንፈዉ ሥራህን አሸንፈሃልና፡፡የሰዉ ልጅ በአሸናፊነት ዙፋን ላይ ለመቀመጥ ሁል ጊዜ ሥራዉን ማሸነፍ አለበት፡፡
በተገቢዉ ሁኔታ ተጀምሮ እስኪያልቅ ሥራዉን ካወቀ፣ ከሰራ፣ ካጠናቀቀ፣ እሱ ሰዉ ባለድል ነዉ፡፡
ሁላችንም ከፊታችን በሚመጣዉ አዲስ ዓመት ራሳችንን
ሁል ጊዜ በአሸናፊነት ዙፋን ላይ ማስቀመጥ የሚችል ልዩ ሞራል ባለቤት እንድንሆን መልካም ምኞቴን ገልፃለሁ፤ መልካም አዲስ ዓመት፡፡
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ