በመዲናችን
በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ የጅማ በር /መውጫ/ ለአራት አሥርት ዓመታት በደረቅ ቆሻሻ መጣያነት /ማጠራቀሚያነት/
ስንገለገልባት/ ስናቆሽሸው/ የነበረ በአሁኑ ሰዓት ከረጅም ዓመታት በኋላ የአዲስ አበባ መስተዳደር መልሶ መጠቀም ክፍል ቦታውን
ለተሻለ ለከተማዋ ልማት ሊጠቀምበት በቀን ብዙ መቶ ሺዎች ካሬ ሜትር ከመንግሥትና ከግል ተቋማት ሲጣልበት የነበረውን በማፅዳትና
በተለያዩ አቅጣጫ ተተኪ ቆሻሻ መጣያ ሥፍራዎችን አዘጋጅቷል፤ የሚገርመው ግን ቆሻሻዎቹን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋልም
/Recycle/ ሆነ በተለያየ ምክንያት ቦታ ሲያገኙ ብዙ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ፣ ሥራቸውን ጠቃሚ የሚባሉትን ነገሮች ከቆሻሻው
በመልቀምና በመሸጥ የሚተዳደሩ፣ የህልውናቸው መሠረት በቆሼ ዙሪያ የጣሉ፣ … ብዙ አሥር መቶዎች ቦታ አልተፈለገላቸውም
/አልተገኘላቸውም/ አስታዋሽ ይሻሉ ቢቻል በማህበር መደራጀት ካልተቻለ ግን ቆሻሻውን ያሰበ መንግሥትም ሆነ እግዚአብሔር
መውደቂያቸውን ከቆሻሻው ሥፍራ አልያም ለምለም መሥክ ይሻሉ፡፡ ካልሆነ Recycle መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡
አዲስ
አበባ ከተማችን ለብዙ ዓመታት ‹‹ፅዱና አረንጓዴ›› እያልን ሥንፎግራት ከከረምን በኃላ ጋሼ አበራ ሞላም ብዙ ከደከመላት
ከሰለቸውና ጥሏት ከተሰደደ በኃላ አርባ ዓመታትን እና ከዚያ በላይ አስተዋጽኦ አጥታ ከኖረች በኃላ መቶ ሃያ አምስተኛ የልደት
በዓሏን በማክበሪያዋ ሰዓት መፅዳትን ከቆሼ ጀምራለች አሁን ወቅቱ ኅዳር የዘልማድ የመጽጃ ወቅት ስለሆነ መልኩን ከቀየረ
የማቆሸሽ ዘዴ አየር ሳንበክልና ቆሻሻን ሳናቃጥል በተገቢው ሁኔታ ደረቅ ቆሻሻን ልናስወግድ የመዲናችን የመጪ ዘመን ዕጣ ፈንታ
አደራ በእጃችን ነው፡፡
ጽዳትን
ለማፅዳት በዘልማድ በዓመት አንድ ጊዜ /ህዳር ሲታጠን/ በሚል ሳይሆን ሁላችንም በዘመናዊነት ተለውጠን በየጓዳችን፣ በየግቢያችን፣
በየቢሮአችን … ያለውን ቆሻሻ ልናፀዳ ቃል እንግባ፣ እናቅድ፣ እንተግብር፣ የመጥረጊያዎቻችን Vision, mission, Goal
ማፅዳት /ፅዳት/ ይሁን ያኔ ነው ‹‹ፅዱና አረንጓዴ አዲስ አበባን›› ማግኘት የሚቻለው አለበለዚያ እኛም አዲስ አበባም
አስተሳሰባችንም ‹‹ቆሼ ቆንቦሬ›› ሆነን እንቀራለን፡፡
ከአዲስ
አበባ መስተዳደር እስከዛሬ ያለውን መዘናጋት ሳይሆን ዛሬ መንቃትን እንማር መስተዳድሩ ለከተማዋ ፅዳት ተግቶ ከሰራ እኛ ዳግም
ለግል ንፅህናችን እና ለግቢያችን ልናንስ አይገባም፡፡ የቆሼ ተሞክሮ እዚያው ሊያከትም አይገባም የመልካም ነገር ጅማሮ ሊሆን
እንጂ፤ የአዲስ አበባ መስተዳድር ይህንን ጉልህ ተግባር እንዲከናወን እና አራት አሥርት ኣመታትን ያስቆጠረ ችግር ወደ ዘላቂ
መፍትሔነት እንደተሸጋገረ መፍትሔ የሚያሻቸው እንደ ቆሼ የበከቱና የቆሸሹ የልማትን ሥራ ቦታ የያዙ ሊወገዱ እና እርምት
የሚያሻቸው ድርጊቶች በተለያዩ በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ በዕምነት ድርጅቶችና ሐይማኖቶች፣ በፖለቲካ ድርጅቶች፣
በምግባረ ሰናይት በተቋቋሙ የእርዳታ ድርጅቶች፣ በመሪዎችና በተመሪው ህብረተሰብ፣ በማኅበራት፣ … ተበራክተው ይገኛሉ ለነዚህ
የአገር ካንሰሮች ተቋማት ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ በማያዳግም ሁኔታ ሊያፀዷቸው የሚታረሙና መልካም ሥራ ላይ መሠማራት
የሚችሉ ከሆነ እሠየው ካልሆነ ግን የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ሊያስወግዳቸውና የጥፋት ቅጣት ማስተማሪያ ሊያደርጋቸው ይገባል፡፡
የፀረ-ሙስና
ተቋም ጅማሮው መልካም ቢሆንም ማሻሻል የሚገባው ጉዳይ የህዝብ ንብረት የሃገር ሃብት በጥቂት ግለሰቦች ተበልቶ /ተመዝብሮ/
ከማለቁ በፊት /እንደ ቆሼ ለረጅም ዓመታት በቆሻሻ ተወሮና በክቶ/ ‹ሳይቃጠል በቅጠል› እንደሚባለው ሁሉ በሙስና ምክንያት
ሆዳቸው ሲሞላ ደረታቸው ሲቀላ ቁጭ ብሎ ‹መረጃ› እና ‹ማስረጃ› በማለት ነገሮችን ከሚያድበሰብስ እስር ቤት ሆነው የሚቀለቡትን
እስከ ሰባት ትውልድ ሊያኖር የሚችል ሃብትና ንብረት ካካበቱ በኃላ እስር ቤት አስቀምጦ ከሚያዝናናቸው በአጭሩ ሳይመሽ በጊዜ
ቢያፀዳቸው መልካም ነው፤ አፋጣኝ እርምጃን ቢወስድ ኖሮ ዛሬ መሬት እንደ ሻማ በጨለማ ባልተቸበቸበች ነበር፤ ዘመዶቻቸውን
በየቦታው ያለምንም በቂ እውቀትና የሥራ ልምድ ባልሰገሰጓቸው ነበር፣ ‹ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋልን› እንደ ትኩስ ተረት ባላስተረቱት ነበር፣ … አሁንም
አልረፈደም፡፡ መሬትን በአግባቡ ሥልጣንን በልኩ መከፋፈል የሚሻል ይመስላል እንደ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ማዕረግ ከማብዛት ከዋና ምናምንነት
እስከ ፀሐፊነት ከማጋብስ፡፡
ፀድተዋል በየምንላቸው ተቋማት ደግሞ የ‹ቆሼ› ቆሻሻ /ሙስና፣
የዘመድ ሥራ፣ ሥልጣንን ያለአግባብ መጠቀም፣ … /እንደገና እንዳይጣል /እንዳያንሰራራ/ አድርጎ እርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ የዕምነት
ተቋማት ክህነት አሰጣጥ፣ የሥራ ኃላፊ አሻEሻEም
ከዝምድና ሥራ ሲፀዳ፤ ሲኖዶሱ እንደዛሬዉ የቤተዘመድ ቤት ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ፣ ጉባኤው በሠው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱሰ
የሚመራ፣ በጭቅጭቅና በኃሜት ባለመግባባት የሚጀምር ሳይሆን በፀሎትና በሱባኤ የሚጀመርና የሚጠናቀቅ ምዕመኑም በሰላም እንደገቡ በሰላም
እንዲወጡ መንፈስ ቅዱስ የምንፈልገውን ሳይሆን የሚበጀንና የሚያስፈልገንን እንዲያስወስን ልንፀልይና ሱባኤ በመግባት ልንጠባበቅ እንጂ
ዛሬ ደግሞ ምን ተባለ በማለት ወሬ በማነፍነፍ ጊዜያችንን የምናባክንበት ዘመን ሊብቃ ይገባል፡፡
በየመሥሪያ ቤታችን (በግልም በመንግሥትም በዓለም አቀፍ ድርጅቶችም
በእርዳታ ሠጪ ድርጅቶችም) የምንሠራም የየክፍላችንን ቆሼ (ቆሻሻ)፣ የተከመሩ ችግሮች ልንቀርፍ፣ የዘመናት ችግሮቻችንን ማስወገጃ
ጊዜያችን አሁን ነው፡፡ ቆሻሻ ነገርን /ሙስናን/ እርም ልንል ጊዜው ዛሬ ነው በየእምነት ተቋማት ለምዕመኑ ከሚያስተምሩት የሃይማኖት
ትምህርት ጎን ለጎን እንደ መምህራቸው እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ /ነቢዩ መሐመድ/ እንደ ሆሳዕናው ዕለት ቤቱን ማፅዳት ‹‹ቤቴ የፀሎት
ቤት እንጂ የገበያ ቦታ አይደለም›› እንዳለ ሥራቸውን ለመጀመር ሰባኪያን፣ መጋቢያን አስመላኪዎች፣ … ግዴታ አለባቸው፡፡ እንዲሁ
ሚኒስተር መሥሪያ ቤቶች በሥራቸው ለሚገኙት ክፍሎች ሁሉ እንዲሁ ሊያደርጉ ፅዳትን ከራስ ሊጀምሩ ይገባል፡፡ ምደባን፣ እድገትን፣
አዲስ ቅጥርን፣ ዝውውርን፣ ሹመትን፣ … ከዝምድና፣ ከእጅ መንሻ፣ በሃይማኖት፣ በቋንቋ /በብሔር/፣ በአገር ልጅነት … መደረጉን
በቃ ልንል የረጅም አመት ጥፋታችን በአንድ ጀንበር ባይፈፀም ሂደቱን ዛሬ እንጀምር ማፅዳቱን ዛሬ እንጀምር፡፡