ሐሙስ 5 ኤፕሪል 2012

“የምሥራቁ ፀሐይ”


ተዋህ በምሥራቅ እንድታበራ ያደረጋት መድኀነ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ልብ ይለዋል፡፡  ‘’በእኔ ያመነ…….’’ ያለው የፅድቅ ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ዓለም ጥለው እርሱን ተከትለው ‘’ዓለም እና በዓለም ያለ ምን ይረባናል’’ ያሉ ጥቂቶች አይደሉም እርሱ በዚህ ዓለም በቁመተ ሥጋ ሲመላለስ 120 ቤተሰቦች እርሱን አሉ፡፡  12 ሐዋርያት ለዓለም ብርሃን በመሆን የዓለምን ጨለማ እንዲያስወግዱ፣ ‘’ወልድ ዋህድ’’ ብለው እንዲያሳምኑ፣ተመረጡ ይሁዳን የመሰሉ ትጥቃቸውን ፈተው ለዓለም ተማረኩ እንደ ዴማስ ያሉቱ ደግሞ ዓለም ማረከቻቸው ዛሬም ዓለምንና ዓለማዊያን እኛን ሊያፀኑና ሊያፅናኑን አባቶች ሁሉን ትተው ‘’በጎችን የመጠበቅ አደራ’’ ተቀብለው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ ይልቁንም ደግሞ በስተምሥራቅ አፍሪካ በአፍራካ ቀንድ ኢትዮጵያዊ አቡነ ጎርጎርዮስ እና ግብፃዊ አቡነሲኖዳ የሚጠቀሱ ነበሩ ታዲያ ምን ያድርጋል የዚህችን ዓለም ምሬት በማጣፈጫቸውና የዚህን ዓለም ሐዘንተኛ /እኛን /በማፅናኛቸውና ቀኖና በመስጫቸው ጊዜ ታግሰው የማያሽንፋት ሞተ ሥጋ ቀደማቸው፡፡
    ኢየሱስ ክርስቶስ ተልዕኮውን ባጠናቀቀ ጊዜ በመስቀል ላይ ሳለ ብዙዎች በሞቱ አዝነው ያለቅሱ ነበርና እንዲህ አላቸው ‘’ለራሳችሁ አልቅሱ’’ ዛሬም በምሥራቅ አፍራካውያን ግብፅ ብቻ አይደለችም ዛሬ  ነው ለራሳችን ማልቀስ ያለብን  በሞት ስለተለዩት የምሥራቁ ፀሐይ ለአቡነ ሲኖዳ ሳይሆን ምነው ቢሉ እነዚያ እኛን የሚባርኩት እጆቻቸው ዛሬ የሉምና፣ እነዚያ ብዕሮቻቸው ዛሬ ነጥፈዋልና፡፡ (መፃፍ አቁመዋልና) እኛ ቀድሰው ፈተትው ያቆርቡ የነበሩ   አባት ዛሬ የሉምና፣ የወንጌልን ወተት ሲመግቡን አባት  መድረክ ላይ የሉምና፣ ባዶነትና በምክር በተግሳፅ በፀሎት የሚሞሉት አባት ዛሬ ከበዓታቸው አጥተናቸዋልና፡፡
    ግብፅ በአህዛብ በግፍ በምትታመስበት በዚህ ሰዓት በጎች በግፍ በሚሰቃዩበት በዚህ ሰዓት መሪር ዕንባን በሚያነቡበት በዚህ ሰዓት….. ሐዘናቸው ከፈት ይልቅ ዛሬ ሐዘናቸው በረታ ታገሱ እግዚአብሔር ሁሉን የሚያደርገው ለበጎ ነው እያሉ  የሚያፅናናቸው አባት፣ ስቃያችሁ የመንግሥት ሰማያትን ፍሬ እንድትመገቡ ያደርጋችኃል እያለ የሚያበረታ ታላቅ  አባት፣ በኃዘን በለቅሶ የሚዘሩ በደስታ ያጭዳሉ እያለ የሚመክር ፅኑ አባት፣…. ዛሬ ዓይኑ እንዳያይ ጆሮው እንዳይሰማ፣እጁ እንደይባርክ፣ አንደበቱ ርቱዕ አንደበት እንዳያስተምር እንዳይፅናና፣ እነዚያ እይተዟዟሩ የሚባርኩ ከባዕት ባዕት የሚጓጓዙ እግሮቹ በፅኑ ህማም /በሞት/ ተይዘዋልና፡፡ ግብፅ ታልቅስ፣ ኢትዮጵያ ታልቅስ፣ የዓለም አብያተ ክርስትያናት ያልቅሱ 40 ዘመን በፅናት  በትጋት ቤተክርስትያንን ሲያገለግሉ ምዕምናንን እንደመልካም እረኝነታቸው ሲያግዱ /ሲጠብቁ/ በመከራም ያለመከራም ሲፀኑና ሲያፅናኑ የነበሩ አባት ይህን ዓለም ጥለው ተሰደዋልና፡፡.
       አቡነ ሲኖዳ ፓትሪያርክ ከግብፅ በረሃ በማርቆስ መንበር በሥልጣነ ክህነት ማገልገል ከጀመሩበት ሰዓት አንስቶ እስከ 88 ዓመታቸው ከመቶ በላይ መፃህፍት ብዛት ያላቸውን ኦዲዮና ቪድዮ ስብከቶችን ለዓለም የክርስትና ሃይማኖት ተከታዩች አበርከተዋል፡፡ ብዙዎችም መፅሐፎቻቸው ወደተለያየ ቋንቋ ተርጉመዋል፡፡ ለመንፈሳዊ ኮሌጆች  መማሪያነት፣ ለጥናትና ምርምር ማስረጃነት አገልግለዋል መጽሐፎቻቸው ሲኖዳ ፓትሪያሪክ ዓለምን ዞረው ባርከዋል፣ ወንጌልን ሰብከዋል፣ በሰውልጅ ልቡና ሥፍራን ይዘዋል፣ የሰው ልጅ በህይወታቸው፣ በትምህርታቸው፣ በአባትነታቸው መግዛት የሚችሉ ቅዱስ አባት ነበሩ፡፡
     ሲኖዳ ሳልሳዊ ለብዙ ዓመታት በበሸታ ቢመቱም የሥጋቸውን ሥቃይ ሲያፀና የነበረውን የኩላሊትን በሸታ በተለያዩ የአሜሪካና የአውሮፓ አገሮች በመዟዟር ታክመዋል የኩላሊትን ሥራ በቴክኖሎጂ በታገዘ መሣሪያ የማሠራት ሥራቸውን (አገልግሎታቸውን) ሲያከናውኑ ቆይተው በአደረባቸው ፅኑ ህመም ከሞት ጋር ግብ ግብ ገጠሙ ለፃድቅ ይታወቀዋልና  ከበዓታቸው ወደርሳቸው የተላከው መልዐከ ሞት ጠበቁት ‘’ተነስ’’ የሚል ድምፅ በሰሙ ጊዜ ተንስተው ተከቱሉት፡፡ በዚህ ዋሉ በዚህ እደሩ አላሉም በጎቻቸውን ምዕመናንን፣ ‘’ክቡር ሞቱ ለፃድቅ’’ ይላል ይሄ ነው፡፡
        የግብፅ ምድር በሃዘን በለቅሶ በሰቆቃ አርጩሜ ተገረፈች ልትፅናናበት በማትችለው ሐዘን ተመታች፣ በሞት ተቀደመች ግብፅ ሆይ በርቺ፣ ኢትዮጵያ ሆይ ንቂ፡፡

1 አስተያየት:

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...