ሐሙስ 15 ኖቬምበር 2012

“የአንበሳውን ድርሻ ማን ይውሰድ?”



ለሰው ልጆች በዚህ ምድር ላይ የምንኖበት ሰዓት መስራታዊና አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በታችኞቹ የትምህርት  ቤት ክፍሎች በደንብ ስምተናል፤ ዛሬ ዛሬ ግን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይልቁንም ለተማሪዎችና ለመንግሥትም ሆነ ለግል ድርጅት ተቀጣሪ ሠራተኞች መሠራታዊ እየሆኑ ካ ነገሮች መካከል ትራንስፖርት ቅድሚያውን ሥፍራ ከያዘ ሠነባበቱ ነገር ግን “አባከና” የሚለውም ካጣ በመስነባበቱ ምክንት ችግሩ ከጊዜ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል “መፍትሔ” እየተባሉ የሚወሰዱትም ተጠቃሚ ህብረተሰብን ያላማከለ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ከዚህም ጎን ለጎን በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ የተሰማሩት እንዲሁ ተበደልን ከገበያው ልንወጣ ነው በማት ሮሮዋቸውን የነዳጁን በየጊጊዌውመጨመር፤ የመለዋወጫ ዕቃ መናገር፤ እንዲሁ ከአሥር ዓመት በፊት ለሙሉ ጥገና የምናወጣው ወጪ ከእጥፍ በላይ መጨ መርን….ቀዘተ ዋቢ በማድረግ ያቀርባ፡፡ ይኽ ሁሉ እውነታ ካለ ታዲያ መፍትሔው ምን ይሁን? ባለድርሻ አካላት፤ ባለሃበት፤ መንግሥት፤ ህብረተሰብ፤ ወዘተ ማት የሚገባውን ከተግባ ጋር እንደያደርጉት አደራዬን አሠማለሁ በበኩሌ ግን አንድ ነገር ጠይቄ በዚየው ማት ያብኝን ማት አውዳለሁ፡፡


ጎልቶ በሚታየው የትራንስፖርት ችግር ላይ መፍትሔ ለመሥጠት እብጠቱን ለማስተንፈስ ከችግር ይልቅ ወደመፍትሄነት ለማሸጋገር የአንበሳው ደርሻ ምን ይወስድ?

ተጨማሪ ለማንበብ ይህን ይጫኑ

እሑድ 11 ኖቬምበር 2012

‹‹የዱር አራዊቶች አቤቱታ››


ሰሞኑን በዚች በምድራችን ‹‹ጫካው ለዛፎች ብቻ›› በሚል ዛፎች ተሰባስበው በዱር አራዊቶች እና አዕዋፎች ላይ የአቋም መግለጫ አወጡ አሉ፤ ከመግለጫው ሥር እንደ አብይ ርዕሰ ጉዳይ ያደረጉት ጫካው ለእኛ ለዛፎች ብቻ ይሁን በማለት ተስማሙ አራዊቶችም አዕዋፍም ወደ ጫካው ዝር እንዳይሉ ተደረገ፡፡
     ምንም እንኳን ዛፎች ይኸንን የመሰለ የመገንጠል የራስን ክልል በራስ የማዘዝና የመግዛት /የማስተዳደር/ አቋማቸውን ቢያሰሙም ዛፎች ቅሬታቸውን በማሰማታቸው የተነሳ

ሐሙስ 8 ኖቬምበር 2012

“ላላ”


ላላ
እኔም እንዳሻኝ  እናንተም እንደሻችሁ ከፈለኩ አጥብቄ ሲያሻኝ አላልቼ አነበዋለሁ! ላላ! (ላላን አላልተዉ ያንብብቡት) አለች ፋጤ፤ የሰፈራችን ሰዎች ሞያ ብለው ተያይዘውታል ልጆቻቸውን ወደ “ቻቻ”(ቻቻ የሚለዉ ቋንቋ ከሚላዉ የአማርኛ ኮሜዲ የተወሰደ ነዉ)ልጅ አገር ልጆቻቸዉን መላክ አንዷም የእማማ አፀዱ ልጅ ከች(መጥታለች ማለት በአራዳ ቋንቋ) ብላለች ከወደዚያው፣ እናላችሁ እንኳን የኛ ሰፈር ሠው የአገራችን ሠው ETV እንደሚለዉ “አንዳንዶች’’ ካልሆኑ በቀር 80 ሚሊዮኑም የዋህ ነው፡፡  ‘’እንኳን ደስ ያሎት’’ ለማለት ቤቱን ብቻ ሳይሆን ልጃቸው ገንዘብ ልካ ያስገጠመችው“French door’’  ሣይቀር Busy  ሆኗል: ተበርግዶ:: አንዳንዶችም መቸስ ለወሬ  የሚሄዱ  አይጠፉም የሰፈራችንን እማማ አፀዱንእንኳን ደስ ሎት  ብሎ ሙዝ፣ ቡርትኳን፣ የአበሻ አረቄ፣…. ይዞ ከሚመጣው ከፊሉ “ምን ይዛልዎት መጣች?” ብሎ እንደወንጀል መርማሪ የሚያደርቃቸው አልጠፋም በጥፊና በእርግጫ አላጣቸውም እንጂ፡፡ እማማ አፀዱም ያለመሰላቸትና መታከት መልስ በመስጠት ተጠምደዋል፡፡  እኔም ከመጣሁ አይቀር እንዴት ነው ሰላም መጣች? ድካሙ እንዴት ነው በረታች መቸስ ረጅም መንገድ መሄድ ያደክማል፣ አየሩን  ምግብና መጠጡንስ  ለመደችሎት ... ካልኩ በኃላ እኔም ምን አፌላይ እንደጣለው የማላውቀው እንዴት ነው ምን ይዛ መጣች ብዬ እርፍ አይገርምም መቸስ የኔ ሲሆን አይገርምም እንደማትሉኝ ተስፋ አደርጋለሁ እኔ ግን ገርሞኛል፡፡  እማማ አፀዱም በመገረም በረጅሙ ከተነፈሱ በኃላ ወደጆሮዬ ጠጋ ብለው “ያገር ላላ” ይዛ መታለች አሉኝ፤ ልቤ በደስታ ተሞላ ለርሳቸው አለፈላቸው ለእኛም  ያው … አንዳንድ ይደርስናለ ብዬ ልቤ ፈነደቀ፡፡ ቶሎ ብዬ በብር ማሰሪያ ላስቲክ ጠፍሬ ያሰርኳትን የቻይና ሞባይል ተመለከትኩ ምናልባት ላላ የሚባል የሞባይል ቀፎ ሊሆን ይችላል በማለት፤ ተጫወት የኔ ልጅ ማነሽ? ትዴ ነይና አጫውችው እንጂ የምን ስልክ ሲያወሩ መዋል ነው አንዳንዴም ሥልኩን አቋርጠሽ እንግዳ አጫውቺ በማለት የመመሪያ ዓይነት ትዕዛዝ አዘል መልዕክት አስተላለፉ፡፡ አቤት ቁልምጫ ትደነቂያለሽ  ሲቆላመጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ሠማሁ  ማሚ መጣሁ አንዴ ሥልክ ይዤ ነው፤ እያወራች ወደኔ ቀረብ ብላ በማላውቀው  ቋንቋ የሆነ ነገር ብላ ሥልኩን አቋርጣ ጉንጮቼን ግራናቀኝ በጉንጯ እያስነካች ጡዋ ጡዋ ጡዋ የሚሉ ድምፆች በጆሮግንዴ በሽቶ ያበዱ መዓዛዎቿን በአፍንጫዬ አስረጫጨቻቸው፡፡ ደስ አለኝ! ወደያው ወደአቋረጠችው ስልክ ተመለሰች ጆሮዬ በተደጋጋሚ አንድ ነገር መስማት ጀመረ ላላ የሚሉ ቃላት ከትደነቂየለሽ አንደበት ውስጤ  አንድ ነገር ጠረጠረ እማማ አፀዱ ያሉኝ የአገር ላላ ይዛ መጥታለች  የሚለው አባባል ውስጠ ወይራ እንደሆነ፡፡
     እማማ አፀዱ በሉ ደህና ዋሉ ልሂድ እንግዲህ፣
v  በል እግዚአብሔር ያክብርልኝ፣….እነርሱ እንደዚህ ናቸው ልባቸው ወደ አገራቸው እስኪመለስ በሥልክ እንጂ በአካል እንዲህ እንኳን ደህና መጣችሁ የሚላቸውን ቁጭ  ብለው አያወሩም  ከዚህ በፊትም ብዙ ልጆች  ሠፈራችን ሲመጡ ጐረቤት ሲማረርባቸው እሰማለሁና ደግፍኳቸው፤እሳቸውም በር ድረስ  ሊሽኙኝ  ወጡ እኔም እየፈራሁ ላላ ምንድን ነው?አልኳቸው፡፡ 
v  እስካሁን ሥታወራ አሥሬ ላላ ሥትል አልሠማሃትም እንግዲህ ምኑን አውቄ ዝምብዬ በደንቆሮ አዕምሮዬ ስጠረጥር “አይሆንም/አይደለም” ማለት ይመስለኛል፡፡
ታዲያ ቅድም ምንድን ነው አመጣችልኝ ያሉት?
v  ይኸንኑ ነዋ ላላ ሲሉ መዋል እኔ ያየሁት ነገር የለም፤ ይኸው ስንት ቀኗ ይመሻል ይነጋል ተነስታ ይዤ የመጣሁት የሠው ዕቃ አለ እያለች መሔድ ነው በነጋ በጠባ ቁጥር፡፡ የማልምልበት ነገር አንድ ሽቶ እና አንድ ሞባይል አይቻለሁ እንግዲህ አሁን እነዚህ ነገሮች ለኔ ምኔ ናቸው? ከኩሽናዬ ጭስ ወዲያ ሽቶ፤ ከሰፈራችን ወሬኞች ወዲያ ሞባይል፤ ምን ሊሰራልኝ …በሉ ደና ዋሉ ብዬ ጥያቸው እግር አውጪኝ አልኩ የሞባይሌን ላስቲክ ጠበቅ እያደረኩ፣
     ጐበዝ ነቄ በሉና ሽል በሏቸው ላላ እያሉ የሚያደነቁሯችሁን የአረብ አገር አራዶችን እንደነገርኳችሁ አኛ ሰፈር ዕድሜያችን ለአቅመ ፓስፓርት ሲደርስ ወደ ኤሚግሬሽን መጓዝ ነው፤ ከዚያ ሴቱ  ለግርድና ወንዱ ለሹፍርና ወይም ለማጣበስ/ለማቀላጠፍ/ እንሰደዳለን አሁን ሠፈሩን የሞላነው እኔና ፓስፓርታቸው disqualify የሆነባቸው /የተሰረዘባቸው/ ነን፡፡  የኔ ሥራ በቋሚነት የሚሄዱትን ቦሌ አየር ማረፍያ ድረስ ሄዶ መሸኘት የሚመጡትን የሰፈራችን ድንጋይ ላይ ቁጭ ብዬ መቀበል ነው፡፡
አንድ ጊዜ ምን ሆነ መሰላችሁ መቸሰ ከተማ ለዚያውም እኛ ሠፈር ተወልዶ ማደግ ችግር  ነዉ፤ ከባላገር የሚፈልሱ ሴቶች  እርጥብ ወደብ መሆን ነው፡፡ አንዴ በሌሊት ወረፋ ለመያዝኢሜግሬሽን፣ አንዴ ደላላ ቤት አንዴ ለምርመራ ሐኪም ቤት፡ ፎቶ ቤት፣ ፎቶኮፒ ቤት፣ብቻ ምናለፋችሁ  ሲዞሩ  መክረም ነው፤  እናላችሁ አንዴ የሆነች የዘመድ ልጅ ከገጠር መጣችና እንደልማዴ ከደላላ ቤት ደላላቤት ይዣት ስዞር አንዱ ደላላ ገና ሲያያት ለጉዲፈቻ ነው ወይሥ ለግርድና ነው ብሎ አያላግጥብኝም!! በሠው እንጀራ መግባት ይሆናል  ብዬ እንጂ በኛ ሠፈር እስታየል ሙልጭ አድርጌ ብሰድበው ደስ ባለኝ ነበር፡፡ እየተዘባነነ ቁጭ በሉ አለን፡፡  ቀኑን ሙሉ ቁጭ ብለን ለመዋል /ለመቀመጥ/ ወደ መቀመጫችን አመራን ችኳ በመገረም  ነበር የምትከልመው ሥትሾፍ ገጌ ብላ ስለነበር መጣሁ  አልኩና እጥፍ አልኩ ወደበሩ፡፡ ያገር ባለገር ከች አይልም፣ … ወይኔ ሲያሳዝኑ  አየተግተለተሉ ገቡ ወረፋ አያውቁም …  አስትናጋ መጠየቅ ጀመረች ሥም ምናምን ተሞላ ዕድሜ 25 ቀና ብላ አየቻት ሥንት ነው ያልሽው  25 ዓመት ያንቺነኮ ነው የምጠይቅሽ አዎ የራሴ ነው ብላ ድርቅ አለች፡፡ በትዕግሥት መጠየቁን ቀጠለች አይዞሽ ከመሄድ አትቀሪም 25 ዓመቱን ትደርሽበታለሽ የማይደረስበት ነገር የለም ያኔ ባልደረሰ የምትይበት ቀን ይመጣል ለማንኛውም እውነተኛውን ንገሪኝ ብላ መለመን ጀመረች ከብዙ ድርድር በኃላ 15 ዓመት መሆኗን ነገረቻት ግትርነቷ የሚገርም ነው የዕድሜው በዚህ ተጠናቀቀና የትነው የምትሄጂው? አለቻት /ጐጃም በረንዳ/ ብትል ምን ይላችኃል፡፡ በቃ ቤቱ በአንደዚህ ዓይነት የተፈጥሮ ኮሜደያን የተሞላ ነው እንዲህ ሆነው ነው እንግዲህ ሲመጡ ላላ እያሉ የሚያደነቁሩን አቦ ይመቻቸው እነርሱ ባይሄዱ ኖሮ እንኳን ፍሬንችዶር ይቅርና ሠፈራችን የለስላሳ ጠርሙስ ስባሪ ዝር አይልም ነበር፡፡  ዕድሜ ለአረብ አገር፡ ዕድሜ ለደላላ፡ ኧረ ቆይ ከዚያ በፊት የሚቀድም አለ …  የመሰደድን መብት የደነገገልን መንግሥታችን ይመስገን፡፡

     ቦሌ ሄጄ ሸኝቼ እንጂ ተቀብዬ የማላውቀው ሠውዬ አንድ ቀን ሲያንቀዠቅዡኝ የማላውቃት አክስቴ ከ15 ዓመት በኃላ ትመጣለች ተብዬ አንድ ሚኒባስ ሞልተን ቦሌን አጥለቀለቅነው፤ ከስንት ሱበዔ በኃላ  ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ዘግይታ ሳይሆን ሰንብታ መጣች ሻንጣ በሻንጣ ላይ ቆልላ ማሽ አላህ እያለች መጣች ብዙዎቻችን በመገረም ቆመን አየናት ላየን ሰው ባለስልጣን  የምንቀበል ሚኒስተሮች ነበር የምንመስለው ፍዘታችን፣ ተመልከቱ እንግዲህ  የኛ ሠፈር ሠው ሲፈዝ ለአክስት ቺኩ የመጣች ሠው እንዴት ሊሆን ነው በአፈጉባኤም እናታችን መሪነት እገሌ …  እገሌ ይባላሉ አያለች ታስተዋውቀን ጀመር ተራው እኔ ላይ ሲደርስ ይሔ ደሞ ጭንቅሎ ነው ብላ … መቸስ አታውቂውም  አይደል ያኔ ገና  ህፃን ነበረ፡፡  ሹ!፣ ሚን!  የማን ልጅ ነው?/ጉድ በል ጐንደር አለ ኮማኪው አይገርምም አማረኛ  ሣታጣራ ሄዳ መፃፍ ማንበብ የማትችልም አክስቴ በፅሁፍ የማታቃትን  ሥትጠራት እማዬም የኔው ጉድ ነዋ! ብላ ማርዳት;“ማሽ አላህ” ብላ አቅፋ ሳመችኝ እኔም ወገቧ ላይ እንደቤታችን ቁንጫ ጥምጥም ብዬ ሙጭጭ …  ፍቅር በፍቅር ሆንን ሜትሮሎጂ መቸስ ሥለፍቅር አይዘግብም እነጂ የዕለቱ ታላቅ ፎንቃ ተብሎ ይመዘገብልኝ ነበር፡፡ላላ አሳነስኩት አይደል ጊነስ ቡክ ላይ ይመዘገብልኝ ነበር ካልሆነም የቦሌ ልጆች በፌስ ቡክ ይለቁት ነበር፡፡
      ሰላምታው በድል ከተጠናቀቀ በኃላ ጉዞ ከቦሌ ወደ ጉለሌ:አሰፋፈራችንን አስቀድሞ እንጂ የሠፈሩ ኩታራበጠቅላላ  እኔና ማሚን ሳይጨምር ወደ ሚኒባሱ እኔ ማሚ አንድ ቀድማ የመጣች የአክስቴ ጓደኛ  አክስቴ በቦሌዋ ላዳ ቃ ዋናዋናው ከላዳው ላ ሌላው በሚኒባስ፣ ዝርዝር  አሰላለፍ ማሚ ጋቢና እኔ እንደተለጠፍኩ ከአክስቴ በቀኝ ክን
ፍ፣ያቺኛዋ ጀለስ በግራ ክንፍ በሚኒባሱ እየተመራን ወደቤት፡፡
     መቸስ ከአረብ አገር ስለመጣች ሠሞኑን ታስከብረኛለች ብዬ እንጂ እንዴት ጭራ እንዳሰበቀለችኝ ልነግራችሁ አልችልም ሠፈር እስክንደርስ አንዲት ነገር አላናገረችንም ከጀለሷ ጋር ግራ ቀኙን እያዩ  ሙድ እየያዙብን  አገራችን ዱባይ ሆና የለ እንዴ? ትላለች ፎቆቹን እያየች ገና መች አየሽና መንገዱስ ብትይ ቆይ ይኼ ሁሉ መቼ  ነው የተሰራው እዛኮ የሚወራው ሌላ ነው ደግሞ ይሄ ሁሉ ፎቅ ምን ይሰራል? ቀበል አድርጌ ሠፈራችን ፈርሶ እዚህ ልንገባ ነው ምነው በሠላም? አለች እንደመደንገጥ ብላ::እናቴ እርር ብላ ተዛዝለለን እንዳልኖርን ልጆቻችን አዝለን እንዳላደግን መንግሥታችን ዛሬ ደግም ዕድገት ተዛዝላችሁ ሙቱ ሲለን  ይኸን ሠርቶ ህዝቡን እዚህ እያጠራቀመ ነው ስሙ ደሞ ኮንደም ነው የሚባለው  አክስቴ እንደውሽት አትቁጠሩብኝና እግሯን አንስታ ነው የሳቀችው ያው ያላነሳችው ታክሲዋ እግር ለማንሳት አይደለም ለማንቀሳቀስ ስለማትመች ነው፤ ሣቃቸው ገርሟትም አናዷትም ዞር ብላ ሥታየን ሰው ሣትሆን አራስ ነብር ነው የምትመስለው ሥትናደድ ሥኳሯ ፡ደም ግፊቷ፣ ልብ ምቷ፣… ባንድ ላይ እንዳይነሱባት ብዬ ቶሎ አልኩና ሥህተቱን እርማት  ሠጠሁበት እማዬ ኮንደም ያለችው ኮንደምንዬም ለማለት ፈልጋ እንጂ ኮንደም መለየት አቅቷት አይደለም  አልኩ፡፡ ሠው ሠፈር የሙዝ ልጣጭ ሲያዳልጥ እኛ ሠፈር ሠውን ለአካል ጉዳተኝነትና ለቁም ነገር የዳረገው የወዳደቁ ኮንደሞች ስለሆኑ ከታዳጊ እስከ አዳጊ ሁላችንም ሥለምናውቀው በእፍረት አክስቴና ጓደኛዋ አፋቸውን በመያዝ እንደመሣቅ አሉ፡፡
     በእቅፋ ሥር እንዳለሁ የትምህርት ቤት ሥምህ ማነው? ብላ ጠየቀችኝ ሠፈርም ትምህርት ቤትም የምታወቀው ጭንቅሎ ነው እኔ ግን የፈተና ወረቀት ላይ ንጉሱ ብዬ እሞላለሁ ንጉሱ ሲባል ግን ማንም አይገርመውም ምን ሆነህ ነው ቀጫጫ የሆንከው? አሁንኮ አይደለም ሲፈጠርም ቀጫጫ ነኝ ባይሆን ኖሮማ የሠፈራችን አሽማጣጮች  ጆከር ስቦ ዱቤ እየጠበቀ ነው ይሉኝ ነበር፡፡
እማዬ ስለኔ ቀጫጫነት ማስረዳት ጀመረች 
ምን እባክሽ ዝም ብሎ ያመዋል፡
አድዬ በስለት ነው እንዴ የወለድሽው? ጉድ በል የጉለሌ ሠው አዳነች ተቆላመጠች አልኩ በልቤ እነዚህ የአረብ አገር ሴቶች ከቁልምጫ ወዲያ የሚያዉቁት ነገር የለም እንዴ? አልኩ በፈረደባት ሆዴ፣
 ምናቃለሁ ብለሽ ነው?ይሆናላ!
አክስቴ በስለት ሳይሆን በሰህተት ነዉ የተፈጠርኩት! አሁን ማን ይሙት እኛ ቤት ሠው መፈጠር አለበት? ሲታመም ፀበል ባይኖር ኖሮ ኃኪም ቤት የማይኬድበት ቤት ውስጥ ለዚያውም እኔ ንጉሳዊ ሥርዓት  ተገርስሶ ፓርላሚንታዊ ሥርዓት በሰፈነበት አገር ንጉስ ላልሆን“ንጉሱ” መባልስ ነበረብኝ?  እስኪ ፍረጂኝ!
     አክስቴ አረብ አገር መንገድ የለም መሰለኝ በተሠራው መንገድ ገርሟት እቤት ሣትደርስ መንገድ ላይ ልትሞት ነው የሰፈራችንን ኮብል እስቶን ሲታይ የኮብልስቶን ቴክኖሎጀ አረብ አገር እንዳልደረሰ አረጋግጥኩ በግርምት ተመልክታ ሥትጠይቀኝ ምንድን ነው ይሄ? ብላ ጥያቄ ብጤ ለሁላችንም አሻማችን፡፡
     የድንጋይ ዳቦ ዘመን ተመልሶ ነው ዳቦ ነው አልኳት ጓደኛው ሆዷን ይዛ ትስቃለች  አክስቴ በብዙ ጥፋትና ድካም መንገድ መሆኑን ደረሰችበት እኔም ሥሙ ኮብል እስቶን መሆኑን አረደኃት፡፡
አገራችን በጣም ተሻሽሏል መንግድ በመንገድ ሆኖ የለንዴ?
መንግሥታችን መሄድ ስለሚያበረታታ ነው፡፡
አንተ አሽማጣጭ ሆነህ የለንዴ!
    እናቴ ቀበል አርጋ ምን አሽሟጣጭ  ይህ ቆንጅት ነው ጡንጅት የሚባለው በ97 ዓ.ም. አገራችን ከገባ በኃላ ህፃኑ ሁላ ተቃዋሚ ሆኗል፡፡ መንግሥትማ ምን ያልሠራው ነገር አለ ብለሽ  ነው እኛ በእድሜያችን አይተን የማናውቀውን ፎቅ አሥፋልት ምንድን ነው ቅድም  ስትባባሉ  የነበረው መንገድ፣ መብራት፣ ኧረ ስንቱ እነርሱ ግን ይሄን ያህል ዓመት ሙሉ ገዝቶ ይሄ ብቻ  አይበቃም ባይ ናቸው ታላቅየውማ ሀይለኛ ቦለቲካኛ ሆኖልሻል ከኔ ጋር  ጦርነት ሊገጥም  ትንሽ ነው የሚቀረው አንድ መቶ ሺ የቀበሌ ቤት አፍርሶ 10 ሺ ኮንደም … ማን ነበር ስሙ መገንባት ልማት አይደለም ይላል፡፡  ሠው የሚበላ የሚጠጣ የለው መንገድ ምን ይሰራለታል ይላል ይሄ ገፊ ነገር ሊያመጣብኝ፡፡
      ላላ  መንገድማ መሠረታዊ ነገር ነው: መንገድ ከሌለ እድገት የለም:ሌሎችአገሮችኮ ያደጉት መንገድ ስላላቸው ነው፡፡
አክስቴኢህአዴግ ነሽነዴ? ዕድገት በአስፋልት ላይ ነው የሚመጣው ያለሽ ማነው? ከማለቴ እናቴ  ይድፋህ አፍህን አትዘጋም  የሰው ማንነት ሣታውቅ ብላ ፊቷን ቅጭም በማድረግ ወደ ሾፌሩ አመለከተችኝ፡፡
     ለካስ ሠውን ማመን አፍን ዘግቶ ነው የሚሉት ጓደኞቼ ወደው አይደለም ዝም ብዩ መቀደዴን ሣሥበው ወደቤታችን የምንሄድ ሳይሆን ወደ 3ኛ የሚወስደን ያህል ነዘረኝ፡፡  ጐመን በጤና ብለን የላዳዋን ሳሎንና ጓዳ ጭር አደረግናት ፀጥ ብለን፤ ወንድሜ ያለኝ ታወሰኝ መቸስ ስለመንግሥት ደና ነገር አያወራ ለአራት ሚሊዮን የአዲስ አበባ ነዋሪ የአዲስ አበባ ፓሊስንና ፌዴራል ፓሊስን  ሣይጨምር ስንት መቶ ደህንነት ነበር አለ ያለው ሠውየው ደህንነት መሰለኝ አሥሬ  በውስጥ መስታወት  ሾፍ  ሲያደርገኝ፡፡ ለነገሩ አክስቴንና ጓደኛዋን እየከለማቸው ይሆናል፣ እኔን አስሬ ቢያየኝ የጨው ማስቀመጫ አያደርገኝ ምናስፈራኝ ከሆነም ከቁም እስር ወደ ተከበረ  እስር ቤት መሄድ ነው ከግማሽ እንጀራ ወደ ታሰረ ሳህን ሽግግር አደርጋለሁ መንግስቱን አሻፈረኝ ቢል  ንጉሱ ምን ይገደዋል፡፡  ላላ ን ተወት አርገን መንገዳችንን ጠበቅ ጉዞ  ወደ ሰፈር !! ቸር ይግጠመን! ሴቶቻችንን ከፎቅ ላይ ከመወርወር ይጠብቅልን! ላላ፡፡
የደረሰ ረታ እይታዎች

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...