ሰኞ 23 ኤፕሪል 2012

ሐሙስ 19 ኤፕሪል 2012

ውረድ


ተው ተው ሲሉህ
 ሲያፈራሩህ
አቅማቸውን አተው
ማንነትህን ዘንግተው
አቅራሩ ሸለሉ
ፎከሩ
ፍጥረት በሙሉ
አንድም ሳይቀሩ
ለአመድ ባንድነት
ለትርፍ ሳይሆን ለጉድለት/ለክስረት/
ተው ተው እያለሁ
እያስፈራሩህ
ውረድ ወይ ፍረድ
ብለው ተሳለቁብህ
ትወርዳለህ ወይስ ትፈርዳለህ?
ቅል ልመናውን ለማያውቅ ፍርዱ
አዕምሮ መስጠት ነው
በትዕግሥት ማለፍ ነው
የፈጣሪ/ የአባት ልምዱ
እላለሁ
አትውረድ
አትፍረድ
ይቅር በለኝ እንጂ
በምህረትህ እንድንዋጅ
ተው ተው ተው አለህ
በመፍጠርህ ሊያስቆጩህ
22/01/03
ደረሰ ረታ
visit us again!

ሰኞ 9 ኤፕሪል 2012

Deresse Reta's Views የደረሰ ረታ እይታዎች: ‘’Disqualify’’

Deresse Reta's Views የደረሰ ረታ እይታዎች: ‘’Disqualify’’: Disqualify   የሚለው ቃል የእንግሊዝኛ ቃል ሲሆን ‘’verb’’ ወይም ግስ ብለን የምንጠራው ሲሆን መዝገበ ቃላት ‘’to put out of a competition’’   ወይም ‘ ’to make unfit for...

ቅዳሜ 7 ኤፕሪል 2012

‹‹የዱር አራዊቶች አቤቱታ››

coming soon.

‹‹ሰባት ቢሊዮን››


ዛሬ ዛሬ ነገሮችን በሚሊዮን አይደለም በቢሊየን መቁጠር ይህንን ያህል ገረሜታን የሚፈጥር አይደለም፤ ሁሉም ነገሮች እጅግ በፍጥነት እያሻቀቡ ከመሆናቸው የተነሳ ቁጥራቸው ጨምሯል የሰው ልጅ ቁጥር እየጨመረ ለሰው ልጆች መሠረታዊ የሚባሉ ነገሮች እየቀነሱ፣ የዓለም ኢኮኖሚ እየጨመረ የነፍስ ወከፍ ገቢ እየቀነሰ፣ በዓለም ላይ ቋንቋዎች እየጨመሩ መግባባት እየቀነሰ …. መጥቷል፡፡ በአስገራሚ ሁኔታ የዓለም ህዝብ ቁጥር በፍጥነት መጨመሩን የዓለም መገናኛ ብዙኋን፣ ምግባረ ሰናይ ድርጅቶች፣ የዓለም መንግሥታት፣ የሚመለከታቸውም የማይመለከታቸው ሁሉ (ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ የማይመለከተው ሠው የለም) የቁጥሩ መጨመር ካለን የዕድገት ደረጃ፣ ከሚጨምረው የቁጥር መጠንና በዓለም ላይ ካንዠራበበው የሙቀት መጠን መጨመር፣ የነፍስ ወከፍ ገቢያችን ሥጋት አንፃር አሉታዊ ተጽዕኖዎች እንዳሉት ያመላክታል በአንፃሩም የአምራች ኃይል በብዛት መኖር የተጠቀሱትን አስከፊ ነገሮች ሁሉ በአዎንታዊው ገጽ ሊቀይረው እንደሚችል እሙን ነው፡፡
     ጥቅምት 20 ቀን 2004 ዓ.ም የዓለም ህዝብ ሰባት ቢሊዮን ይሆናል ተብሎ ተገምቷል ይህ ቁጥር በእያንዳንዳችን ጆሮ ሲሰማ ምን ይመስለናል? ምንስ እናስባለን? ያኔ ከዛሬ ብዙ ዓመታት በፊት ዓለም ሲፈጠር ብቻውን የነበረው አዳም፣ ብቻውን መሆን መልካም አይደለም ተብላ የተፈጠረችው ሴት የአዳም ውድ ባለቤቱ ሔዋን ምን ይሉ ይሆን? የሃላፊያትንና የመፃኢያትን ጊዜ ጠንቅቆ የሚያውቅ እግዚአብሔር እንደ ሰው ቢሆንና ‹‹ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት›› ያለው ትዛዙን ሞልተን እንዲህ ሰባት ቢልየን ሰዎች ስንሆን ሰው ቢሆን ኖሮ ምን ይል ነበር? አዳምና ሔዋን እነዚህን ሰባት ቢሊዮን ህዝብ እንደ ወላጅ ዛሬም በህይወት ኖረው ቢያስተዳድሩን ምን ይሆኑ ነበር?
     እስኪ ወደ ቁምነገሩ እንመለስ በተለያዩ የዓለም አገራት መንግሥት የህዝብ መጨመር ሥጋት ውስጥ ስለከተታቸው ህዝባቸው እንዳይራብ መሠረታዊ ነገሮችን በማጣት እንዳይጎዳ የቤተሰባቸውን መጠን እንዲቀንሱ አልፎ አልፎም የቁጥሩን መጠን በመገደብ ህዝቡን ያስተዳድራሉ፤ ከዚህም አልፎ በጤና ተቋማት በመገናኛ ብዙኅን በተለያዩ አጋጣሚዎች የቤተሰብ ምጣኔን ያስተምራል፡፡ እኛስ የቤተሰባችንን ቁጥር መጠን በዕቅድ ነው በአጋጣሚ የምንወስነው? የዓለም መንግሥታት የዓለምን ህዝብ ቁጥ በበጎ አመለካከት ለመቀነስ ከሚያደርጉት ጎን ለጎን በአሰቃቂ ሁኔታ አስከፊ በሽታዎች የዓለምን ህዝብ እየቀጠፉት ይገኛሉ፤ ይኼ ብቻ አይደለም ጦርነቶች፣ ድርቆች፣ የምግብና የንፁህ መጠጥ እጦት፣ ድንገተኛ አደጋዎች ለምሳሌ፡- የመሬት መንሸራተት፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ እሳተጎመራ፣ የህንፃዎች መናድ፣ የእሳት ቃጠሎ፣ ተላላፊ በሽታዎች ወዘተ… የዓለምን ህዝብ ቁጥር በፍጥነት እየቀነሱ ይገኛሉ መብዛት እንዳለ መቀነስ፣ መፈጠር እንዳለ መሞት፣ ባይኖር ኖሮ የዓለም ህዝብ ቁጥር ስንት ይሆን ነበር? ዛሬ ሰባት ቢልየን ሆንን የዛሬ ዓመት ስንት እንሆን ይሆን? የዛሬ አሥርና ሃያ ዓመትስ?
     ሰባት ቢሊዮን መሆናችን ብቻ አይደለም የሚገርመው ብዙ አይነት ህዝቦች እዚህ ቁጥር ውስጥ መካተታቸውም እንጂ ቅሩበ እግዚአብሔር የሆኑ ፃድቃን፣ የዓለምን በደል የሚያፀኑ ግፈኞች፣ ራሳቸውን አሸባሪ እያሉ የሰየሙ በቡድን የተደራጁ፣ ርህሩሆች፣ ጨካኞች፣ የዕለት ጉርሳቸውን የዓመት ልብሳቸውን ለማሟላት በቅንነት ደፋ ቀና የሚሉ ሚሊዮኖች፣ ሽፍቶች፣ አጭበርባሪዎች፣ ደጋግ ህዝቦች፣ አምባገነን መሪዎች፣ የሃይማኖት ሰዎችና እምነት አልባዎች ወዘተ … እነዚህ ሁሉ ይህንን ሰባት ቢልየን ቁጥር መጋረታቸው የሚደንቀው አንዱ ገፅታው ነው፡፡ እስኪ ለአንድ አፍታ ይኸ ሁሉ ህዝብ አንድ ፆታ አንድ ብሔር አንድ ቋንቋ አንድ ገጽታ አንድ አይነት ቁመትና ተክለቁመና አንድ አይነት ባህርይ አንድ መሪ ወዘተ… ቢኖረው ብላችሁ አስቡት እግረ መንገዳችሁን ይኸንን ሁሉ ያላማካሪ እንዲህ ውብ አድርጎ የፈጠራና የሚገዛ የሚመግብ እግዚአብሔርን ሥራህ ዕፁብ ድንቅ ብለን እናመሰግነው፡፡

‹‹ቆሼ››


በመዲናችን በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ የጅማ በር /መውጫ/ ለአራት አሥርት ዓመታት በደረቅ ቆሻሻ መጣያነት /ማጠራቀሚያነት/ ስንገለገልባት/ ስናቆሽሸው/ የነበረ በአሁኑ ሰዓት ከረጅም ዓመታት በኋላ የአዲስ አበባ መስተዳደር መልሶ መጠቀም ክፍል ቦታውን ለተሻለ ለከተማዋ ልማት ሊጠቀምበት በቀን ብዙ መቶ ሺዎች ካሬ ሜትር ከመንግሥትና ከግል ተቋማት ሲጣልበት የነበረውን በማፅዳትና በተለያዩ አቅጣጫ ተተኪ ቆሻሻ መጣያ ሥፍራዎችን አዘጋጅቷል፤ የሚገርመው ግን ቆሻሻዎቹን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋልም /Recycle/ ሆነ በተለያየ ምክንያት ቦታ ሲያገኙ ብዙ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ፣ ሥራቸውን ጠቃሚ የሚባሉትን ነገሮች ከቆሻሻው በመልቀምና በመሸጥ የሚተዳደሩ፣ የህልውናቸው መሠረት በቆሼ ዙሪያ የጣሉ፣ … ብዙ አሥር መቶዎች ቦታ አልተፈለገላቸውም /አልተገኘላቸውም/ አስታዋሽ ይሻሉ ቢቻል በማህበር መደራጀት ካልተቻለ ግን ቆሻሻውን ያሰበ መንግሥትም ሆነ እግዚአብሔር መውደቂያቸውን ከቆሻሻው ሥፍራ አልያም ለምለም መሥክ ይሻሉ፡፡ ካልሆነ Recycle መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡

አዲስ አበባ ከተማችን ለብዙ ዓመታት ‹‹ፅዱና አረንጓዴ›› እያልን ሥንፎግራት ከከረምን በኃላ ጋሼ አበራ ሞላም ብዙ ከደከመላት ከሰለቸውና ጥሏት ከተሰደደ በኃላ አርባ ዓመታትን እና ከዚያ በላይ አስተዋጽኦ አጥታ ከኖረች በኃላ መቶ ሃያ አምስተኛ የልደት በዓሏን በማክበሪያዋ ሰዓት መፅዳትን ከቆሼ ጀምራለች አሁን ወቅቱ ኅዳር የዘልማድ የመጽጃ ወቅት ስለሆነ መልኩን ከቀየረ የማቆሸሽ ዘዴ አየር ሳንበክልና ቆሻሻን ሳናቃጥል በተገቢው ሁኔታ ደረቅ ቆሻሻን ልናስወግድ የመዲናችን የመጪ ዘመን ዕጣ ፈንታ አደራ በእጃችን ነው፡፡

ጽዳትን ለማፅዳት በዘልማድ በዓመት አንድ ጊዜ /ህዳር ሲታጠን/ በሚል ሳይሆን ሁላችንም በዘመናዊነት ተለውጠን በየጓዳችን፣ በየግቢያችን፣ በየቢሮአችን … ያለውን ቆሻሻ ልናፀዳ ቃል እንግባ፣ እናቅድ፣ እንተግብር፣ የመጥረጊያዎቻችን Vision, mission, Goal ማፅዳት /ፅዳት/ ይሁን ያኔ ነው ‹‹ፅዱና አረንጓዴ አዲስ አበባን›› ማግኘት የሚቻለው አለበለዚያ እኛም አዲስ አበባም አስተሳሰባችንም ‹‹ቆሼ ቆንቦሬ›› ሆነን እንቀራለን፡፡

ከአዲስ አበባ መስተዳደር እስከዛሬ ያለውን መዘናጋት ሳይሆን ዛሬ መንቃትን እንማር መስተዳድሩ ለከተማዋ ፅዳት ተግቶ ከሰራ እኛ ዳግም ለግል ንፅህናችን እና ለግቢያችን ልናንስ አይገባም፡፡ የቆሼ ተሞክሮ እዚያው ሊያከትም አይገባም የመልካም ነገር ጅማሮ ሊሆን እንጂ፤ የአዲስ አበባ መስተዳድር ይህንን ጉልህ ተግባር እንዲከናወን እና አራት አሥርት ኣመታትን ያስቆጠረ ችግር ወደ ዘላቂ መፍትሔነት እንደተሸጋገረ መፍትሔ የሚያሻቸው እንደ ቆሼ የበከቱና የቆሸሹ የልማትን ሥራ ቦታ የያዙ ሊወገዱ እና እርምት የሚያሻቸው ድርጊቶች በተለያዩ በመንግሥትና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት፣ በዕምነት ድርጅቶችና ሐይማኖቶች፣ በፖለቲካ ድርጅቶች፣ በምግባረ ሰናይት በተቋቋሙ የእርዳታ ድርጅቶች፣ በመሪዎችና በተመሪው ህብረተሰብ፣ በማኅበራት፣ … ተበራክተው ይገኛሉ ለነዚህ የአገር ካንሰሮች ተቋማት ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡ በማያዳግም ሁኔታ ሊያፀዷቸው የሚታረሙና መልካም ሥራ ላይ መሠማራት የሚችሉ ከሆነ እሠየው ካልሆነ ግን የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ሊያስወግዳቸውና የጥፋት ቅጣት ማስተማሪያ ሊያደርጋቸው ይገባል፡፡

የፀረ-ሙስና ተቋም ጅማሮው መልካም ቢሆንም ማሻሻል የሚገባው ጉዳይ የህዝብ ንብረት የሃገር ሃብት በጥቂት ግለሰቦች ተበልቶ /ተመዝብሮ/ ከማለቁ በፊት /እንደ ቆሼ ለረጅም ዓመታት በቆሻሻ ተወሮና በክቶ/ ‹ሳይቃጠል በቅጠል› እንደሚባለው ሁሉ በሙስና ምክንያት ሆዳቸው ሲሞላ ደረታቸው ሲቀላ ቁጭ ብሎ ‹መረጃ› እና ‹ማስረጃ› በማለት ነገሮችን ከሚያድበሰብስ እስር ቤት ሆነው የሚቀለቡትን እስከ ሰባት ትውልድ ሊያኖር የሚችል ሃብትና ንብረት ካካበቱ በኃላ እስር ቤት አስቀምጦ ከሚያዝናናቸው በአጭሩ ሳይመሽ በጊዜ ቢያፀዳቸው መልካም ነው፤ አፋጣኝ እርምጃን ቢወስድ ኖሮ ዛሬ መሬት እንደ ሻማ በጨለማ ባልተቸበቸበች ነበር፤ ዘመዶቻቸውን በየቦታው ያለምንም በቂ እውቀትና የሥራ ልምድ ባልሰገሰጓቸው ነበር፣ ‹ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋልን› እንደ ትኩስ ተረት ባላስተረቱት ነበር፣ … አሁንም አልረፈደም፡፡ መሬትን በአግባቡ ሥልጣንን በልኩ መከፋፈል የሚሻል ይመስላል እንደ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ማዕረግ ከማብዛት ከዋና ምናምንነት እስከ ፀሐፊነት ከማጋብስ፡፡

ፀድተዋል በየምንላቸው ተቋማት ደግሞ የ‹ቆሼ› ቆሻሻ /ሙስና፣ የዘመድ ሥራ፣ ሥልጣንን ያለአግባብ መጠቀም፣ … /እንደገና እንዳይጣል /እንዳያንሰራራ/ አድርጎ እርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ የዕምነት ተቋማት ክህነት አሰጣጥ፣ የሥራ ኃላፊ አሻEEም ከዝምድና ሥራ ሲፀዳ፤ ሲኖዶሱ እንደዛሬዉ የቤተዘመድ ቤት ሳይሆን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ፣ ጉባኤው በሠው ሳይሆን በመንፈስ ቅዱሰ የሚመራ፣ በጭቅጭቅና በኃሜት ባለመግባባት የሚጀምር ሳይሆን በፀሎትና በሱባኤ የሚጀመርና የሚጠናቀቅ ምዕመኑም በሰላም እንደገቡ በሰላም እንዲወጡ መንፈስ ቅዱስ የምንፈልገውን ሳይሆን የሚበጀንና የሚያስፈልገንን እንዲያስወስን ልንፀልይና ሱባኤ በመግባት ልንጠባበቅ እንጂ ዛሬ ደግሞ ምን ተባለ በማለት ወሬ በማነፍነፍ ጊዜያችንን የምናባክንበት ዘመን ሊብቃ ይገባል፡፡

በየመሥሪያ ቤታችን (በግልም በመንግሥትም በዓለም አቀፍ ድርጅቶችም በእርዳታ ሠጪ ድርጅቶችም) የምንሠራም የየክፍላችንን ቆሼ (ቆሻሻ)፣ የተከመሩ ችግሮች ልንቀርፍ፣ የዘመናት ችግሮቻችንን ማስወገጃ ጊዜያችን አሁን ነው፡፡ ቆሻሻ ነገርን /ሙስናን/ እርም ልንል ጊዜው ዛሬ ነው በየእምነት ተቋማት ለምዕመኑ ከሚያስተምሩት የሃይማኖት ትምህርት ጎን ለጎን እንደ መምህራቸው እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ /ነቢዩ መሐመድ/ እንደ ሆሳዕናው ዕለት ቤቱን ማፅዳት ‹‹ቤቴ የፀሎት ቤት እንጂ የገበያ ቦታ አይደለም›› እንዳለ ሥራቸውን ለመጀመር ሰባኪያን፣ መጋቢያን አስመላኪዎች፣ … ግዴታ አለባቸው፡፡ እንዲሁ ሚኒስተር መሥሪያ ቤቶች በሥራቸው ለሚገኙት ክፍሎች ሁሉ እንዲሁ ሊያደርጉ ፅዳትን ከራስ ሊጀምሩ ይገባል፡፡ ምደባን፣ እድገትን፣ አዲስ ቅጥርን፣ ዝውውርን፣ ሹመትን፣ … ከዝምድና፣ ከእጅ መንሻ፣ በሃይማኖት፣ በቋንቋ /በብሔር/፣ በአገር ልጅነት … መደረጉን በቃ ልንል የረጅም አመት ጥፋታችን በአንድ ጀንበር ባይፈፀም ሂደቱን ዛሬ እንጀምር ማፅዳቱን ዛሬ እንጀምር፡፡

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...