ረቡዕ 1 ኖቬምበር 2017

ትዳር ክፍል ፪



በይደር ያቆየነዉን ጥያቄ እንመልስ ካልን እና እንደዚህ አይነት እንደምናገባ/ለወንድም ለሴትም ያገለግላል/ ቢታወቅ እግዚአብሔር ለአዳም ከጎኑ ሔዋንን በፈጠረ ጊዜ አዳም ባላንቀላፋ ነበር፡፡ቅዱስ ጳዉሎስም ስለ ትዳር/ጋብቻ ሲናገር " ቢቻላችሁ …" በማለት ባላቅማማ እና አግቡ ብሎ ባስተማረ እና እሱም ባገባ ነበር፤ ነገር ግን ቅዱስ ጳዉሎስ አላገባም፡፡ ከገሚሶቹም በቀር ከሐዋርያት አላገቡም ያገቡትንም ቢሆን ከጥቂቶቹ መልካም ሚስቶች በቀር መፅሐፍ ቅዱስ ሚስቶቻቸዉን አይጠቅስም፤አልጠቀሰምም፡፡ለምን ካሉ ልሂቃን መልስ ይስጡበት፡፡
የሰዉ ልጅ ክፉ ሆኖ እንዳልሆነ እሙን ነዉ እኔ ክፉ ነዉ ብዬ ለመናገር ያዳግተኛል፤ እንደዉ ሌላዉ ቢቀር እነዚህ ሁለት ጥንዶች እንዃን በጓደኝነት ወቅት እንቅፋት ሲመታቸዉ እኔን ብለዉ የሚንሰፈሰፉ፣ ማዕድ እንዃን ሲቋደሱ ቀድመዉ የማይጎርሱ፣ ትን ሲላቸዉም ሆነ ምግብ ሲያንቃቸዉ ምራቃቸዉን እንዃን ለመስጠት ወደ ኋላ የማይሉ፣ ያፈለገዉን ያህል ቀጠሮ ቢያረፍዱ በትዕግሥት የሚጠብቁ ፣ … ሁሉንም ዘርዝሮ መጨረስ ስለማይቻል በወዘተ መገላገል ሳይሻል አይቀርም፤ ስለሰዉ ልጅ ጥሩነት ለመግለፅ በቂ ናቸዉና (ለማያምን ግን ሺም ቢዘረዘር አያሳምነዉም)፡፡ ከትዳር ማግስት ግን እነዚያ ሃሜትም ምክርም የማይሰሙ ጥንዶች ጆሮአቸዉ በኦዙን የሳሳ ይመስል ሽንቁር ይሆናል፡፡ ሆድ ይብሰዋል፣ ቶሎ ይከፋዋል፣ ቂም ይቋጥራል፣ ወሬ ይሰማል፣ ነገር ይጠመዝዛል፣ በአጠቃላይ ማንነቱ ላይ የሆነ ነገር ዞር ይለበታል፡፡ አጋሩን/ሚስቱን እንቅፋት ሲመታት እያየሽ አትሄጂም ምን ወሬ ታያለሽ፣ምግብ ሲያንቃት ቀስ ብለሽ አትበይም ምን ያጣድፍሻል ዉድድር የለብሽ እያለ ይነቅፋታል፣እሷም አባወራን የሚያህል ነገር ከዉጭ ቀርቶ ሲያመሽ ስለጤንነቱ ሳይሆን ቅናት ፀጉሯን አቁሞት ሰላም አመሸህ እንደማለት የት አመሸህ ብላ በነገር ትቀበለዋለች፣ ከመነጋገር በግል መወሰን ይጀምራሉ ይህ ነገራቸዉ ለብቻ ወስኖ እስከማርገዝ አልፎተርፎም ለብቻ የህክምና ክትትል ይጀመራል በአጋጣሚ ሃኪም ባለቤትሽስ ሲላት አልሰማም ለምን ከተባለች አርግዤ አምጬ የምወልደዉ እኔ እሱ ምን አገባዉ ድረስ ይዘልቃል፤ ….
ሳምንቱ ከምኔዉ አልቆ/ዕለቱ ከምኔዉ መሽቶ

ዓርብ 20 ኦክቶበር 2017

ትዳር ክፍል ፩



ሰላም ወዳጆቼ እየደጋገመ/እየተመላለሰ ወደ አዕምሮዬ እየመጣ የሚያስቸግረኝ በየአጋጣሚዉም የተለያዩ ጓደኞቼም ሲያነሱት የምሰማዉ ሲነሳም አጨቃጫቂነቱ ሰላም የሚነሳ ጉዳይ ዛሬ ልተነፍሰዉ ፈለኩ፤ "ትዳር" በመፈላሰፍም/መንፈሳዊ በመሆንም/በመዘመንም … ዉስጥ ሆነን እናየዋለን አንባቢ እንደመሰለዉ ሊያቀናዉ ሊያጣምመዉ ሊተቸዉ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ትዳር የሚለዉን ቃል የከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት " ሰዉ ሁሉ በንብረቱ የሚተዳደርበት የቤት ስራ ፣ ባለ ጠጋም ሆነ ድሃ እንደተሰጠዉ መተዳደር" ብሎ ይፈታዋል፤
የትዳር ዉስጥ ድራማዎች
በመሰረቱ  ድራማ እንደሚታወቀዉ በመድረክ የሚተወን፣ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚተላለፍ እና የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ድራማዎች አሉ፡፡ እነዚህ በአጭርና በረጅም ጊዜ ተመጥነዉ የሚሰሩ ድራማዎች በባህሪያቸዉ
ü  ኮሜዲ (አስቂኝ )ወይም አዝናኝ
ü  ትራጀዲ
ü  ሆረር ( አስፈሪ) ከማዝናናት ከማስተማር ባለፈ በአስፈሪነታቸዉ የሚታወቁ፤ ነገር ግን ምንም አስፈሪ ቢሆኑ መልዕክት ከማስተላለፍ ወደ ኋላ የማይሉ ናቸዉ፡፡
ልክ ከዚሁ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ  ትዳርም በምድራችን ሁለት ነጠላ ሰወች " ትዳርን " ሲመሰርቱ የሚተዉኑት የህይወት ድራማ ይሆናል፡፡ እነዚህም፡-
ü  የማስመሰል ( በአንድ ቤት መኖር ብቻ ህይወት አልባ ዓላማ የለሽ )
ü  እዉን የሆነና ህይወት ህይወት የሚል
ü  ማስፈራሪያና ዛቻ የሞላበት ከፍቅር ይልቅ ፀብ ጭቅጭቅ የነገሰበት
ü  የሚፈልገዉን (የምትፈልገዉን ) በማድረግ ብቻ (በማሟላት ብቻ) ፕሮዲዉሰር(አዘጋጅ ) መሆን ( እንደቤት ሠራተኛ) በማገልገል ድራማዉን የሚሰሩ ወዘተ
ታድያ ትዳርም ህይወት አልባ እንደሆነና ሌላን ሠዉ መስለዉ የሚተዉኑበት ከሆነና የማይኖሩት ሁለቱ ነጠላ (ሲንግል) ሠወች በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነዉ እንደ አንድ ልብ አሣቢ ሆነዉ የማይኖሩት በድን አሻንጉሊት ከሆነ የሠዉ ልጅ ለምን ይጋባል? ለምንስ ትዳር ይመሰርታል? የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል፡፡
መቀጠሉ አይቀርም፤ እንቀጥላለን
ማሳሰቢያ ፡- የምንቀጥለዉ ግን በዉስጥም በዉጭም ባለዉ አስተያየታችሁ ላይ ተንተርሰን ነዉ፡፡

እሑድ 13 ኦገስት 2017

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: ‹ድኻ ወርቅ አይግዛ›

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: ‹ድኻ ወርቅ አይግዛ›: ‹ድኻ ወርቅ አይግዛ ከገዛም ይጥፋበት› ይላሉ የምንዳዬ እናት አባዬ፡፡ ‹ምነው አባዬ ድኻ በመከራ የገዛውን ወርቅ እንዴት ይጥፋበት ይላሉ› ብለን ሞገትናቸው፡፡ ‹እይውልህ እኛ ሠፈር አራት ኪሎ አዲሴ የሚሏት አንዲ...

ማክሰኞ 14 ጁላይ 2015

ሳይማር ያስተማረን … … … ሳይማር ያስመረቀን ትዉልድ




የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
የሚሊንየም አዳራሽ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች በተለያየ የትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ፣የሁለተኛ እና የዶክትሬት ትምህርታቸዉን ያጠናቀቁ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ለግማሽ ቀን ያህል አስተናግዶ ዉሎአል፡፡ይህንን ታላቅ የምርቃት በዓል አስመልክቶ ታዋቂዉ የኤፍ.ኤም.ሬድዮ ጣቢያ እዚያዉ ከሚገኘዉ ጊዜያዊ ጣቢያዉ የተማሪዎችን፣ የዩኒቨርስቲዉን መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች፣ የተመራቂ ተማሪዎችን ወላጅ ዘመድ ጓደኞች የእንኳን ደስ አላችሁ እና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ቀጥታ ስርጭት እያስተላለፈ ይገኛል፡፡
አድማጮቻችን ዛሬ በልዩ ፕሮግራም ከቦሌ አዉሮፕላን ማረፊያ ፊት ለፊት በሰፊዉ ሜዳ ላይ ተንጣሎ ከሚገኘዉ የሚሊንየም አዳራሽ ጊዜያዊ የማሰራጫ ጣቢያችን ይህንን በዓይነቱ ልዩ የተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ቀጥታ ተቀብለን ለማስተላለፍ እና ከማለዳዉ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ከስፍራዉ በመገኘት ለስለስ ባሉ ጣዕም ባላቸዉ ሙዚቃዎች ስናዝናናችሁ መቆየታችን ይታወሳል፡፡
ለስለስ ያለዉን ሙዚቃ ከዚህ ጊዜያዊ የማሰራጫ ጣቢያችን ያስደመጡንን የስቲዲዮ ባለሞያዎቻችን፣ የደቡብ ሱዳኑን፣ የቻይናዉን እና የደቡብ ኮርያዉን አቀንቃኞች በቅደም ተከተላቸዉ ላመሰግን እወዳለሁ፡፡
አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ የዛሬዉ በዓል እጅግ ልዩ ነዉ፤ ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት እዚህ ጎረቤታችን ኬንያ መጥተዉ ጎብኝተዉ በተመለሱበት ማግሥት እና ወደ ኢትዮጵያም በተመሳሳይ ሁኔታ ጉብኝታቸዉን ያደርጋሉ ተብሎ ከሚጠበቅበት ዋዜማ መሆኑ ነዉ፡፡
አድማጮቻችን እንግዲህ የምረቃ መርሀግብሩ እየተጠናቀቀ እና በስፍራዉ የታደሙ የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች ከአዳራሽ እየወጡ መሆኑ በርቀት ይታየኛል፤ በዚህ ታላቅ የምረቃ በዓል ላይ ክቡር ሚኒስትሩ ባይገኙም የተከበሩት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የአንድ ቋሚ ኮሚቴ ሠብሳቢ የሆኑት እኚህ ሠዉ ከክልል ከመጡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋራ በጋራ በመሆን ተማሪዎቹን ለማስመረቅ ተገኝተዋል፡፡
ክቡራን አድማጮቻችን እነኚህን ሁለት የአገራችን ታላላቅ ሰወች ስለምርቃቱ እና አንዳንድ ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች አንስተን በሰፊዉ እናወራቸዋለን በጥሞና ተከታተሉን፡፡ እስከዛዉ በጣም የምንወደዉ እና የኢትዮጵያ ወዳጅ እና ባለዉለታ የቦብ ማርሊን stand up for your right የሚለዉን ተጋብዛችኋል፡፡
አድማጮቻችን ሁለቱን የአገሪቱን ታላቅ ባለስልጣናት አየር ላይ ልናቀርብላችሁ የሞከርነዉ ሙከራ ባለስልጣናቱ ለአስቸኳይ አገራዊ ጉዳይ ተጣድፈዉ ባልጠበቅነዉ የመዉጫ በር ስለወጡብን ሙከራችን አልተሳካም፡፡
አድማጮቻችን እንደሚታወቀዉ ብዙ ተማሪዎች ጥሩ ዉጤት በማስመዝገብ የዋንጫ እና የሚዳልያ ተመራቂዎች እንዳሉ ሰምተናል፤ ከነዚህ መካከል አንድ ልጅ እዚህ አጠገቤ አለ ከእርሱ ጋር የማደርገዉን ቆይታ ተከታተሉን፡-
እስኪ ስምህንና እዚህ የተገኘህበትን ምክንያት ለአድማጮቻችን ግለፅልን
̋ ሴባ እባላለሁ የመጣሁት የትምህርት ጊዜዬን አጠናቅቄ ለምርቃት ነዉ የተገኘሁት ˝
እንኳን ደስ አለህ
̋እንኳን አብሮ ደስ አለን  ̋
ሴባ በዛሬዉ ዕለት በመመረቅህ ምን ተሰማህ?
˝ እንዴ! … በጣም … በጣም … ግልግል ነዋ! ትልቅ ግልግል ̋
በምን የትምህርት ዘርፍ ነዉ የተመረከዉ?
˝̋ በFBI ነዉ የተመረኩት፤ ˝
ከFBE ፋክልቲ ማለትህ ነዉ?
˝ ያዉ ነዉ … ምን ልዩነት አለዉ ፍሬንድ  ̋
ከየት አካባቢ ነዉ የመጣኸዉ?
˝ እዚሁ ነኝ ከየትም አልመጣሁም  ̋
ሥምህ ለየት ያለ ነዉ ትርጉሙን ብትነግረኝ?
˝ ጓደኞቼ ናቸዉ ያወጡልኝ እንደምታየዉ ፀጉሬን ሹሩባ መሰራቴን ተከትሎ እና ሴባስቶፖል የሚለዉን ሲያቆላምጡ ነዉ ሴባ ያሉኝ  ̋
ኦ! ሴባስቶፖል ነዉ ሰምህ?
˝ ኖ! ስሜ ቴዎድሮስ ነዉ  ̋
በጣም ጥሩ የዋንጫ ተሸላሚ ነህ መሰለኝ ዋንጫም በእጅህ ሜዳልያዉንም አንገትህ ላይ እንደማየዉ ባለድርብ ድል ነህ፤
˝ አቦ ለገተታ ነዉ ባክሽን … … ከፍሬንዳችን ለፎቶ ተቀብዬ ነዉ  ̋
እናመሰግናለን፡፡
አድማጮቻችን የመጀመሪያዉን ቆይታችንን ተከታትላችሁታል በጣም አዝናኝ እና አስተማሪ ነበር ቀጣዩን ደግሞ አንዲት ወጣት ተመራቂ ከጎናችን ትገኛለች ከእርሳ ጋር ጋር ያለንን ቆይታ ተከታተሉን፡፡
እህታችን እንኳን አደረሰሽ ደስም አለሽ
˝ እንኳን አብሮ ደስ አለን  ̋
ስምሽን እና ስለዛሬዉ በዓል ለአድማጮቻችን የሚሰማሽን ነገር በአጭሩ ብትገልጭልን?        
˝ ስሜ እንኳን ይለፈኝ በአጭሩ የማስተላልፈዉ በዛሬዉ በደስታዮ ዕለት ሳይማሩ ያስተማሩኝን አርሶ አደር ቤተሰቦቼንና ሳይማሩ እዚህ በክብር እንግድነት ተገኝተዉ ያስመረቁንን የክብር እንግዶች፣ የትምህርት ቤቱን ማህበረሰብ ፣ አራት ነጥብ አምጥቼ እንድመረቅ ላበቁኝ መምህራኖቼ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፤ ˝
አድማጮቻችን መርሀግብሩ እንደቀጠለ ነዉ ተከታተሉን … …

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...