ሐሙስ 5 ኤፕሪል 2012

“የኛ ሰው”


ሐምሌ 11 ቀን 2003 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡27 መነሻ ቦታ ሚኒሊክ አደባባይ ሚኒሊክን ለማያውቅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ይህንን ላላወቀ መነሻዬን ልንገራችሁ 59 ቁጥር አንበሳ አውቶብስ መነሻ ሐሳብ የኛ ሰው መድረሻ ቦታ አዲሱ ገበያ መድረሻ ሐሳብ እኔም አላውቀውም፡፡
ለጽሑፌ መግቢያም መውጫም እንደባለሞያ የለኝም በቃ የኛ ሰው ብዬ ጀመርኩ መብቴ ነው ማን የሰጠህ ካላችሁ የናንተም የመጠየቅ መብት ይከበራል መልሱን የሚሰጠውን እኔም እናንተም ባታውቁት ይሻለናል፡፡
የኛ ሰው የሚለውን እንዳነበባችሁ ሲፈልጋችሁ “የኛ ሰው በአሜሪካን ” ወይም የኛ ሰው በ… ያስታውሳችሁ ማስታወስ የማትፈልጉትም፣ ማስታወስ የማትችሉትም መብታችሁ ነው ፡፡
የኛ ሰው የሚለውን ሐሳብ የወሬ ቋንጧ ሳላደረገው የወሬ የፆም ሰዓትም ሳይገባ በትኩሱ ለጆሮአችሁ ላሰማችሁ የአንበሳ አውቶቡሱ ከብዙ ሱባኤ ከብዙ ምህላ በኋላ ከቺሊ ምድር ሥር ለብዙ ቀናት እንደሰነበቱት ማዕድን አውጪ ዎች በነርሱ ምድር ተከድናባቸው በኛ ላይ ደግሞ የአንበሳው ደጃፍ ተዘግቶብን ከቆየንበት ሥፍራ ተንቀሳቅሰን መንገድ ጀመርን ለምን የሚሉ ጥያቄዎች ያላችሁ መልሱን ራሱ ነገር ይመልሰዋል ጆሮአችሁን እያከካችሁ ቆዩን አለበሊዚያም ጉርርር በሉት ለጆሮአችሁ ወይም እንደየምነታችሁ በስመአብ - ቢስሚላኂ -በየሱስ ስም… ወዘተ ማለት ትችላላችሁ፡፡
ልክ እሳት አደጋ ዋና መስሪያ ቤት ጋር እንደደረሰን የሆነ ነገር አየሁየኛ ሰውመነሻ ሐሳብ የሆነውን የኛ ሰው ነገር ምን ተዳዳሪ እንደሚባሉ አላውቅም ወይም ምን ልላቸው ወይም ምን ዓይነት ሥም ላወጣላቸው እንደምችልና የትኛው ሥም እንደሚመጥናቸው አላውቅም አንድ ነገር ግን አውቃለሁ በታችኛው የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉትን ሠዎች ፍላጐት በየጐዳናው እየተዘዋወሩ እንደሚያሟሉ እኔን ጨምሮ ብዙ እቃ ገዝቼአቸዋለሁ ሲሸጡልኝ ዋስትና አለው ብለው  አልዘላበዱልኝም የማጣሪያሽያጭ ብለው አይኒን አላጭበረበ
ሩኝም  አንዳንዴ ጆሮዩን አደናቆሩት እንጂ እየተንጫጩ እነዚህየኮንትሮባንድ ዕቃ ሻጮች እነዚህህገወጥ ነጋዴዎችእነዚህ  የቤት ኪራይ ወጪ፣ የመንግሥት ግብር፣ የሠራተኛ ደመወዝ ወጪ የሌለባቸውወዘተዎች ፤እነዚህ ምኑ እንዳተነካ የንብ መንጋ ብትን አሉ አቅማቸው ግር ማለት ሳይሆን ብትን፣ ብን ማለት ነውና ያሳደዳቸውን ወይንም ያባራራቸውን አላውቅም ወይም አላየሁም የሚያባርራቸው እንደሆነ የለም እነርሱም የሚያያቸውን በንስር ዓይናቸው አዩት የሚያስድዳቸውን ሸሹት ነገረኛን መፍትሔው  መሸሽ ነውና የተቻለኝን ያህል የሚያሳድዳቸውን ለማየት በዚያች ቅጽበት አማተርኩ ፖሊስ ወይም ደንብ አስከባሪ ፍለጋ አላየሁም ምናልባት ቀይ ለባሽ ወይም ነጭ ለባሽ አለበዚያም ሌላ መልክ የለበሰ አዲስ አሰዳጁ መጥቶባቸው ይሆናል እነርሱም መሰደዳቸው አሳዳጁም ማሳደዱን ሳያቆም እኔ እይታዬን አቁሜ መንገዴን ቀጠልኩ ማየቴን ማቆም ፈልጌ ሣይሆን የነበርኩበት 59 ቁጥር አውቶቡስ እንደኔ በዚህ እይታውስጥ ሳይሆን ጐዳናውን  እየቃኘ ስለነበረ ይዞኝ ነጐደ እኔም ከዚህ መነሻነት የኛን ሰው ማየት ጀመርኩ በዕዝነ ምናምኔ ዘልዬወደ ሰማሁት አንድ ነገር ሄድኩ ደቡብ አፍሪካና ሌሎች ዓለማት ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ ህይወት ያላቸው ልምድ እየዞሩ በየጐዳናው መሸጥ ወይም የሚያሳድዷቸው ማስቸገር ነው መሰለኝ እንዲሁ ነው ሲሯሯጡ ሲኳትኑ የሚውሉት አሉ የሚያሳድዷቸውም ህግ ተሰርቶ ይሁን በኛ አገር ሠርታችሁ አለፈላችሁ ብለው ቀንተው ይሁን አይታወቅም ያሳድዷቸዋል ይዘርፋቸዋል ይገሉዋቸዋል….ወዘተ አሉ ለነገሩ ምን ይገርማል እንኳንስ ባዕዱ በሰው አገር ወገኑ ራሱ በአገሩ ያስድደው የለ አንድ ነገር አስታወስኩ አንድ ጊዜ በጆሮዬ ጥልቅ ያለችውን አዳምን ከገነት አምላኩ ሲያባርረው ጥረህ ግረህ ብላ የሚለው አባባል ወይም ታሪክ (መጽሐፍ ቅዱሳዊ) ታዲያ ኢትዮጵያዊ ተሳደህ ተሰዳደህ (አንዱ አንዱን አሳዶ) ኑር ተብሎ ተፈርዶበት በታሪክ አልተነገረ በመጽሐፍ አልተፃፈ ይሆን ይኸውላችሁ የኛ ሰው ዕጣ ክፍሉ አንዱ አንዱን ማሳደድ አንዱ በአንዱ ላይ መቅናት አንዱ በሌላው የላብ ውጤት ንብረት ላይ መነሳት ማሳደድ ሆነ እላችኋለሁ፡፡
ይኸንን ነው እንግዲህ የኛን ሰው በደቡብ አፍሪካ የኛን ሰው በገናናዋ አገር በአሜሪካ የኛን ሰው በአገሩ በመንደሩ በቀዬው የታዘብኩትን በዚህች የሰው ጉዳይ በማይለው ጭንቅላቴ ምን አገባኝ ብዬ ትቼው መለከ ከማለት አንድ የኛ ሰው ጉዳይ በዓይኔ በብረቱ ጥልቅ አለ ምን በሉኝ መከታተላችሁን ከኔ ጋር መሆናችሁን እንዳውቅ… ድሮ የኔታ እግር ስር ሆነን ሥንማር ሲያስነጥሳቸው … የኔታን ይማርልን እንዳልነው ከኔ ጋር ሁኑ ብዙ ነገር ስለ የኛ ሰው የምነግራችሁ አለ ከአገር ውስጥም ከአገር ውጭም ቅድም ሚኒሊክ አደባባይ ጋር ለሁለት ተሰልፈን እንደዳቦ ቤት ዳጁ ደጅ ስንጠና መግቢያ ቲኬቱን ለመቁረጥ ስንጠባበቅ ከፈለጋችሁ ‘ቪዛ’ በሉት እንደሆነ የኛ አገር ትራንስፖርት አሜሪካ መግቢያ ቪዛ ያህል ችግሩ ጠንክሯል እንደሆነ ተሰልፈን እያለ ወረፋ አለመጠበቅ በዘመድ መስተናገድ ለሚያውቁት ሰው ቁረጥልኝ ብሎ ሐቀኛውን ወደ ኋላ ማስቀረት የአውቶቡስ ተራ አሪፍነት እንደሆነ ተጠቃሚዎችና የደረሰባችሁ እርር ብላችሁ ለማንም መተንፈስ አቅቷችሁ አይታችሁ ታዝባችሁ በደሉ ተፈፅሞባችሁ ዝም ብላችሁ የሄዳችሁ ታውቃላችሁ፡፡
ከዚያ በኋላ ተሰልፈን እያለ አንዲት ሴት ፈጠን ብላ መጥታ ገንዘብ የምተሰበሰበዋን አንድ ብር ይዛ ቀራበቻት በቃ ሰው ዓይን አወጣ መከባበር ተራ መጠበቅ ቀረ ይቺ የህግ ኩሬ የሆነች አገር ላይ ህግ የሚያውቅ እንጂ የሚያከብር ጠፋ ብዬ በውስጤ ሳጉተመትም ቆርጣ ለመግባት እግሯን ስታነሳ ሳያት እርጉዝ ነበረች በሆዴ ላወራሁት በሆዴ በሆዷ ያለው ምን እንደሆነ ስላላወኩ ገና ለገና ነገን ፈርቼው በሆዷ ያለውን ይቅርታ ጠየኩት እርሷም ገባች እኔም ገባሁ እርሷም ቆማለች እኔም ቆምኩ እርሱንም አርግዘሻል አንተም ተበሳጭተሃል ብሎ ተቀመጡ ያለን አልነበረም ሰው ‘ሼም’ አያውቅማ የተጨካከነም መሰለኝ እኔ ግነ የኛ ሰው ዝም ቢላትም‘ሼም ቆነጠጠኝና’ አንድ ሰው አስነስቸ አስነስቼ ሁለት ሰው የሚያስቀምጠው ላይ ለሶስት እንዲቀመጡ አደረኩ  በእናቴ ሆድ ውስጥ እያለሁ የማይመቹ ነገሮችን ቀስሜ ነው መሰለኝ እንዳለተመቻት ገባኝ እንደማይመች አርግዞ መማር አይጠይቅም እድሜ ለቴክኖሎጂ ‘በአልትራሳውንድ’ ማወቅ ይቻላል ከቴክኖሎጂ (ዘመን አማጣሹ) ጋር መግባባት ካልቻላችሁ ልጁ  (ልጁቱ) ተፅዕኖ እንዳላሳድር በፆታ ላይ ሁለቱንም ተጠቅሜአለሁ ጊዜው የዕኩልነት ነውና እንዳልተመቻቸው አፍ አውጥተው ከሆነ ይነግሯችኋል አፍ ካለውጡ ጊዜው ቢያልፋም የምታምኑት እንደየምነታችሁ መጠን ማታ በህልም ይግለጡላችሁ እርጉዟ የጠረጠርኩት እውነት ሆኖ የተቀመጠችበት አልተመቻትም ለማስነሳት የኛን ሰው ፀባይ ጠንቅቃ ታውቃለችና እንዲነሱላት አስባ ለመነሳት ተግደረደረች አይገርማችሁም የኛ ሰው መጨካከን የጀመረው መቼና እንዴት በማን አማካኝነት እንደሆነ ባይታወቅም ተጨካክኗል የተግደረደረችውን ጨክና አደረገችው ተነሰታ ቆመች የገረመኝ ነገር ወንዱ ልጅ ገና ጐረምሳው አርግዞ ወይ አስረግዞ የማያውቀው ነፍሱ ሹክ ብላው አውቆ ነው መሰል ሲነሳ አጠገቧ የነበሩት ሲያጣብቧትና ሲያስነሳት የነበሩት ሴት ለዚያውም ሴት ወይዘሮ ስንት ጊዜ አርግዘው ያማጡ ዕርግዝና የልጅ ልጅ ባይኖረውም የልጅ ልጁን የሚያውቁት ሴትዮ ጨከኑባት ፍቅራቸውንም ፀባቸውንም ባላውቀውም አይዋደዱም የሚባለውን ስሞታ ሳይሆን አይቀርም ለማለት ደዳኝ እንዳላምን ግን አፍራሽ ነገር አጋጠመኝ ምን በሉ እንጂ አድማጭ አንባቢዎች ተረት ተረት ስንባል የመሰረት ስንል እንቅልፍ እየወሰደን እንዳደግነው መድረሻችን እስኪለየን፡፡
እንደእኔ ያለው ፈሪ በሆዱ ሲረግማቸው ግማሹ ሲገላምጣቸው ጨኻኝ ሲላቸው መቼስ የኛ ሰው ብዙ መልክ አይደል ያለው አዎ በሉ ከበስተኋለው የነበሩ ሰዎች ተመካክረው ነው መሰል እንጃ ሁለቱ ተነስተው አንዱ በዕድሜ የገፋ በሽበት የበለፀጉ እናትን ጨምረው ለሁለት አመቻችተው አሰቀመጧት አቤት የኛ ሰው ሥንት አይነት አለመሰላችሁ የኛ ሰው በሰው አገር የኛ ሰው በአገራችን…
በነገር እንዳያዝኳችሁ አውቶብስ እየሄደ እየሄደ ሰሜን ሆቴልን ተሻግሮ ቆመ በየመቆምያው መቆምና ሰው ማውረድ ብቻ ሣይሆን ሰው መጫንም ግድ ይለዋልና እንደእኛ የአንበሳ አውቶቡስን በየፌርማታው ዓይኑን ለማየት የልባቸውን ፈቃድ ለመፈፀም ወደ መደራሻቸው ለመድረስ ዓይናቸውን ስቅለው የሚጠብቁት ብን ብለው ሳይሆን ግር ብለው ወደ ትኬት ቆራጫ ተመሙ ውስጥ ካለነው አብዛኛው የቅድሙን የራሱን የዓይን ናፍቆት ገብቶ ተወጣውና ነገሩን ሁሉ ረሳውና ሾፌሩን በቃ በሩን አትክፈት ሞልቷል የት ለማስገባት ነው እያለ ማጉረምረም ጀመረ ለራሱ ቢሆን መሙላት አይደለም ቢተርፍ አይደለም አውቶብሱ ውስጥ አንበሳው ጫንቃ ላይ ተቀምጦ መሄድ የሚናፈቀው ወገኑን ተጨናንቆ ገብቶ ወደቤቱ እንዳይገባ አሳደደው በልቡ ከአንበሳው ደጅ አሳዳዳቸው አይገርምም የኛ ሰው ነገር የኔስ ነገር ብትሉ መንገዴ መንጐድ ትቼ የትዝብት ምች እንደመታው ሰው ምን አስታዘበኝ እኔንጃ ይግራማችሁና አንድ የገረመኝን ነገር ልንገራችሁ የኛ ሰው ክፋቱ እንደደግነቱ ሁሉ ወደር የለውምና የዘዋሪው/የሹፌሩ/ የትኬት ቆራጩ አሰማሪ/ሥምሪት ክፍል/ናት አሉ በዚህ ዋሉ በዚህ ውጡ በዚህ ግቡ ብላ የምታስጨንቃቸው ያ ሁሉ ምድረ ሰው ከአፋ እስከ ገደፍ ሞልቶ አንበሳውን አላስፈሳ አላስገሣ ያለውን ህዝብ ማን ጫን አለህ አውርድ ብላ ማንቁርቱን ያዘችው አሉ ዘዋሪውን ዓይኔን ወደዳጅ ጣል ሣደርግ ለተቀማጭ ሠማይ ቅርቡ አይደል ርዝመቱ ምን ያህል እንደሆነ ባታይወቅም ታታክረዋለች እርሱ ሊያስረዳት ይሞክራል ትኬት ቀንጣሿ ቶሎ ደርሰን እንመጣለን ብላ ትማፀናለች ከጐኔ የነበሩት መሄድ ያማራቸው ተጓዥች “ይኼ ሁሉ ህዝብ ቆርጦ ሲገባ የት ነበረች አለቃነቷን ይህ ሁሉ ሰው ይወቅልኝ ብላ ነው?”:‘የሴት ነገር ድሮም’…ወዘተ ይላሉ ፍርዱ ለመስጠት አንቀፅ ለመጥቀስ፣ቀነ ቀጠሮ ፣ምስክር፣ክርክር ፣ ግርግር ፣ ውዥንብር  ወዘተ … ስለሚያስፈልግ እኔ በድምፅ ተአቅቦ አልፌዋለሁ የኛን ሰው ግን ታዘቡልኝ፡፡
መቼስ ጥፊም ይደገም የለ አንድ ልድገማችሁ ጥፊ ቢደገም ያማል የኔ ደግሞ ትዝብት ይጨምራል ከመግቢያው እስከ መውጫው ጢም ያለው ሰው ለመግባት እንዳልቸኮለ ለመውጣት ያረገዘችው ሳያምጣት ምጥ የያዘቸው ዘዋሪውን አሰጨነቁት ኃላፊዋን በምልጃ ተሳፋሪውን የሆነ ጥግ ፈልጐ በውረጃ ተገላገላቸው የኛ ሰው ግን አይገርምም? ይገርማል ፡፡
የኛ ሰው መቼስ የማይለው የለም 59 ቁጥር ወይራ ሠፈር /ቤቴል/ መሄዷን ትታ ባህር ዛፍ ሠፈር ወደ አዲሱ ገበያ ምን ትሠራለች ሳትሉ አትቀሩምና ሾፌሩና ትኬት ቀንጣሿ መዘወር ያማራቸው ሳይሆኑ ሰው የመርዳት ፍቅር ያደራባቸው ነበሩና ተራቸው /ሰዓታቸው/ እስኪደርስ እንደ አፈር የፈሰሰውን ህዝብ ወደየቀየው ለመበተን ለአሰሪ መስሪያ ቤታችውም የማይነጥፍ ኪሳችውን ለማሰብ ነበር ፡፡
የኛ ሰው በኛ አገርም የኛ ሰው በሰው አገርም ቢወራለት ጉንጭ አልፋ ነውና እናንተ በቃ ባታውቁም እኔ ትዝብቴን በዚህ ላብቃ ሌላ ጊዜ እንዲሁ ሃሳቤን ካልሸወራረው የኛን ሰው እታዘባለሁ፡፡
የሆነ ቀን ነው አሉ ማን እንደሆነ ባላውቅም ስለ የኛ ሰው አስተያየት ለመጠየቅ እግዚአብሔር ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያለ ሰውን ጨምሮ ሃያሁለቱን ፍጥረት ሰብስቦ የታዘባቸሁትን ንገሩኝ አስተያየታችሁንም ስጡኝ ቢል ቀበሮ ቀድማ ተነስታ የኛን ሰው ታዝባ ታዝባ ሰው ምን እንዳረጋት ብትጠየቅ ብዙ የምትለው ቢኖራትም ‘ለሰው ሞት አነሰው’ ብላ ተቀመጠች አሉ እናንተስ ስለሰው መቸስ “ስለሰው ስለሰው ቀድጄ  ልልበሰው” እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ የኛን ሰው ገና እንታዘባለን፡፡

ፊርማዬ


የኔነቴ ምልክት የጣቴ አሻራ
መጠሪያ ነቁጤነሽ ብዙ የሚያኮራ
የቃሌ ማሰሪያ ማረጋገጫ

ፊርማዬ፤…….
ሽቅብ ቁልቁል አግድም
ስርዥ ደልዥ

የማስቀምጥሽ የጣቶቼ ቅምር
ሀ፣ለ፣…… 0,1,2…..
ተብሎ የሚደረደር
ፊርማዬ
የነገር ማብቂያዬ
23/02/95
ደረሰ ረታ

ሐሙስ 29 ማርች 2012

‘’Disqualify’’


Disqualify  የሚለው ቃል የእንግሊዝኛ ቃል ሲሆን ‘’verb’’ ወይም ግስ ብለን የምንጠራው ሲሆን መዝገበ ቃላት ‘’to put out of a competition’’  ወይም ‘’to make unfit for some purpose’’ብሎ ይፈታዋል በመጠኑ ወደ አማርኛ ሳንመልሰው ‘’የማይመጥን፣ከጨዋታ ውጭ ማድረግ፣…… ወዘተ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡
    ይህንን  ነገር ጫር ጫር  ለማድረግ አንድ ነገር አጋጠመኝ ገጠመኙ እንዲህ ነው ‘’ታቦት ከመንበሩ ሰው ከሃገሩ የሚወጣው ችግር ሲኖር ነው’’ ይላሉ የአክሱም ሰዎች እናም አንዲት እህቴ  ኑሮ ሲከብዳት ሥራ ካለዘመድ፣ ካለ እጅ መንሻ፣ ሴትነትን ካልገበሩ በቀር፣ (እንዲያውም በአንድ በአገራችን ባለ ትልቅ ተቋም B.P.R ወይም Transformation የሚባለው ነገር ሲሰራ ለምደባ እና ለሹመት እንደ መወጣጫ አገልግሎ ነበር አሉ) ብቻ ምን አለፋችሁ ለብዙ ዓመታት ለረጅም ወራት ብዙዎች ሥር አጥተው እቤት አንደሚቀመጡት ሥራ አጣች፣እቤት ተቀመጠች፡፡’’ በእንቅርት ላይ…. ‘’ እንደሚባለው ሥራ በማጣት ላይ ይህችን አገር ጠላች፡፡  መጥላት በአገራችን በሰፈነው ዲሞክራሲያዊ መብት የተለገሳት ነውና፡፡  እንኳን እርሷ ሥንቶች ሄደው የለ? እንኳን እርሷ አንድ ግለሰብ ይቅርና ቱባ ቱባ የአገሪቱን ሥልጣን ተሸክመው አገርና ህዝብ ሲመሩ የነበሩትስ ጠልተው ወይ ተጣልተው  ሄደው የለ? ታዲያ ይመሯትና ያስተዳድሯት የነበሩትን ታማኝ የአገሯን ባለሥልጣናት ተከትላ ብትሄድ ምኑ ነው ክፋቱ? ወንጀል ሰርታ ለመሰወር፣ የአገሪቱን ሃብት ንብረት መዝብራ ለመደበቅ አስካልሄደች ድረስ፡፡
     ሊቁ ወደ  ጥንተ ነገራችን እንመለስ እንዳለው ወደ ጥንተ ነገራችን እንመለስና  በቃ ሥራ አጣች አገር ጠላች ሥደት አማራት ይቅርታ ከአገር ወጥታ ሌላ አገር ሄዳ ሥራ ለመፈለግ  ተመኘች ሰው አገር ሄደች ከመሄዷ በፊት ግን እንዲህ ሆነ እርሷ ለመሄድ ተመኘች ፣ ቤተሰብ መክራ ወዳጅ ዘመድ ወንድም እህት ገንዘብ አሰባስባ፣ደላላ ተፈለገ፣ /ተገኘ/ ኤምባሲ ተሄደ፣ ቪዛ ተመታ፣ደላላ ብሬን ክፈሉኝ አለ ከአገር የምትወጣበት ቪዛ ማግኛ ሳይሆን ከአገር  ለመውጣት የምታቆራርጥበት የመኪና መግዣ የሚያክል  ዋጋ ጠየቀ፣ አለመግባባት ተፈጠረ፣ ፓስፓርቷን ነጥቋት ሄደ፣ ሽምግልና ተጀመረ እንዲህ አለ፡፡……’’የምላትን ገንዘብ አስካልከፈለችኝ ድረስ የትም አትሄድም ፓስፓርቷን  አቃጥለዋለው ከዚህ በኃላ  ወደውጭ አገር የመሄድ ሙከራ እንዳታደርግ  የእርሷን ጉዳይ Disqualify አደርገዋለሁ አለ፡፡’’ እጅግ በጣም በማን አለብኝነት፣ በትቢዕት፣ ከ’ኔ ወዲያ አድራጊ ፈጣሪ የለም በሚል ሥሜት፣….. ምን አለፋችሁ  ብዙ ብዙ  ነገር ሆነ………..ግን ሄደች የልቧ ደረሰ እንባ እራጭታን ተሸኘች፡፡
     ነገሩ ወዲህ ነው አስኪ በህይወታችን ውሰጥ ሰዎች በሥልጣናቸው፣ ሰው በማወቃቸው፣ ገንዘብ ሥላላቸው፣ አካሄዱን ሥለሚያውቁበት፣ ብቻ ምናለፋችሁ በሆነ በሆነ መንገድ አድርገው ይገባሉ ገብተዋል ለመግባት አድብተዋል፡፡  ግን! ግን ይህን ለማድረግ እነርሱ ማን ናቸው? እነርሱ በኛ ህይውት ላይ ይህንን ሲያደርጉ መብት ካላቸው በእኛ ላይ እንዳይደረግ ፍትህ የለም እንዴ? ምን ይደረግ ‘’ገንዘብ ሲናገር ፍትህ ዳጥ’’ ይላል ተብሎ የለ፡፡
    አንድ ነገር ልበላችሁ ሰዎች ብዙ ነገር ሆነው ይሆናል ለመከላከል ብዙ ደክመው ድካማቸው ከንቱ ሆኖ ይሆናል እናንተ ግን አትሸነፋ ብዙዎች ታላላቅ ብለን ታሪካቸውን  የምንዘክርላቸው ታዋቂ  ባለሃብቶች፣ ምሁራን፣ቅዱሳን፣……. ከብዙ መውደቅ መነሳት በኃላ፣ ከብዙ ሽንፈት  በኃላ፣ ከብዙ መንገላታት  በኃላ ነውና ለዚህ የበቁት ለውድቀታችን መንስኤ የሚሆነው  መጀመሪያ የራሳችን መውደቅ ስለሆነ ጥንቃቄ እናድርግ ራሳችንን ሥንጥል ነውና ሰዎች እኛን ለመጣል የሚበረቱት፣ በደካማ ጐኖቻችን ሥለሆነ እየገቡ የሚጥሉን እጅግም ራሳችንን ለጠላቶቻችን ክፍት እናድርገው ማንነታችንን ይጫወቱበታልና እንቁዎቻችሁን በእርያዎች /ዓሣማዎች/ ፊት አታስቀምጡት እንዳይስብሩባችሁ’’ እንዲል እንቁ ማንነታችንን እንጠብቅ ብዙዎች በዚህ የተነሳ  ከሥራ ገበታቸው፣ ከሚያምር ትዳራቸው፣ ተምረው ይመጥናሉ  ተብለው ካገኙት ሥልጣን /የሥራ ደረጃ/ ከክብራቸው (ከድንግልናቸው)፣ በሰው ዘንድ ተዓማኒ ከመሆናቸው፣…… ወዘተ Disqualify ተደርገዋል ሊደረጉ ተዝቶባቸዋል፣ እየተደባባቸው ይገኛል፡፡ ግን ለምን?
    ወደኃላ ተመልሰን ታሪኩን ሥንዳስስ ያ ሰው ፓስፓርቷን ቪዛዋን…… እንዲያውም ይባስ ብላ የትም አገር እንዳትሄድ ጭምር ብሎ ሲዝት በየቦታው በየስራ ክፍሉ ለእውነት የቆመ የለም?  ፍትህስ የለም?  እውነትስ ወደየት ሄደች?  ልብ አርጉ ይህ ሰው አንድ ብቻውን ነው ብዙ ኤምባሲዎችን የመንግሥት ተቋማትን /ኤሜግሪሽንን/ ጨምሮ ማለት ነው የሚያምሰው እርሱን የመሰሉ ህብረተሰቡን የሚያውኩ ተቋማትን ለመጣልና አላማቸውን ለማሳት ባለሥልጣናትን ለማሰናከል ላይ ታች የሚሉትን ቤት ይቁጠራቸው፡፡

    ዛሬ በየማረሚያ ቤቶች /እስር ቤቶች/ ሥንት ባለስልጣናት የኃላፊነት ቦታ ላይ ሲሰሩ የነበሩ በንፅህና ህዝቡንና መንግሥትን ሲያገለግሉ ከነበሩበት እነዚህ ሰዎች እየገቡ ክፋ ዘር ዘርተውባቸው ጉድ የሰሯቸው ገሚሶችም እንሰሳትን ጨው በማላስ ወደ መታረጃው እንዲወስዷቸው እንዲሁ ጨው የተባለ ጥቅምን /ገንዘብ/፣ ውዳሴን፣ዝናን ወዘተ በማቅመስ ወደ እስር ቤት ያስወረወሯቸው ዘመድ፣ የቅርብ ወዳጅ በመምሰል የሃሰት ፈገግታቸውን በማሳየት እየሳቁ የገደሏቸው ቤተሰባቸውን የበተኑባቸው፡፡
     አንድ ነገር አጥብቄ መናገር እፈልጋለሁ የትም ይሁን የት በቀበሌ ከጥበቃ  እስከ  ቀበሌው ሊቀመንበር መታወቂያ አንሰጥም፣ የቀበሌ ቤት አንሰጣችሁም ጉዳያችሁን አንፈፅምላችሁም ብሎ ጉዳያችንን Disqualify የሚያደርጉብንን፣ በየመሥሪያ ቤታችን  የዓመት ፈቃድ (ዕረፍት) ከመስጠት እስከ ዕድገትና ዝውውራችን ላይ የሚቀልዱትን፣ሆስፒታል ሄደን ከካርድ ክፍል እስከ ሐኪሙና የመድኃኒት ወይም ላብራቶሪ ክፍል ድረስ፣ በትምህርት ቤት ከዩኒት ሊደር፣መምህር ዳይሬክተር ድረስ ፣በዕድር፣በዕቁብ፣ በትዳር ውሰጥ የእኛን ጉዳይ Disqualify በማድረግ ሽባ  ሊያደርጉ  አሰፍሥፈው የሚጠብቁትን በቃ ልንላቸው ይገባናል፡፡ ይህንን ለማስከበር  ከተቋቋሙ የፀጥታ ኃይሎች፣ የሰብዓዊ መብት፣ ዕንባ ጠባቂ ፣ ፀረ-ሙስና ኮምሽን፣በአጠቃላይ ከመንግሥት ጐን ልንቆም ይገባናል፡፡ ለመብታችን ዘብ እንቁም  እንዚህን ሰዎች እናጋልጥ ችግሩን ከምንጩ እናድርቅ ተዋናዬችም ካለን እንታቀብ፡፡

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...