በአንድ ወቅት ነው አሉ ቀበሮ እስከማንዘሮቿበወይን ፍሬ ትተዳደራለች
ልጆቿን ታሳድጋለች(የልጆቿን ነፍስ ትታደጋለች) እናም ከዕለታት አንድ ቀን የወይኑ ጌታ ለወይኑ ቅፅር/ አጥር/ ቀጠረለት ማስገቢያ
ቀዳዳዎችን ደፈነ፤ ቀበሮ መግቢያ አይደለም የትንኝ መግቢያ መንገድ አልተገኘም ነበር፡፡ ነገር ግን ከጊዜ ብዛት ሾልካ የምትገባበትን
ቀዳዳ መንገድ አገኘች መግባትም ጀመረች ነገርግንእንደድሮው ወይም እንደምትጠብቀው አልነበርም ወይኑ ከመብሰሉ የተነሳ እንዳይበላሽ
በአውሬም እንዳረጋገጥና እንዳይበላ ተደረጎ በባላ ከፍ ተደርጎ ተሰቅሏል፡፡ እስከ ልጆቿ የመጣቸው ቀበሮ በመደናገጥ መዘየድ ጀመረች
ይባስ የተራቡ ልጆቿ እየተንጫጩ እያቀለሱአስጨነቋት የነርሱ ርሃብና ልቅሶ ደግሞ የበለጠ ግራ አጋባት፡፡ የወይኑን ዘለላ እያየች
ምራቋን ትውጥ እየዘለለች እየፈረጠች ለማውረድ መጣር ጀመረች፤ ጥረቷ ግን ሊሰምር አልቻለም የወይኑ ተክል ረጅም ቁመቱ አጭር ሆነባት፡፡
ዘለለች ዘለለች …. ምንም ሊሆንላት አልቻም፡፡ ተስፋ ስትቆርጥ ወደ ልጆቿ ዘወርበማለት እንዲህ አለቻቸው “ወይኑ አልበሰለምና አይረባም
እንሂድ ሌለ የሚበላ ጥሩ ምግብ እንፈልግ” አለቻቸው ነገር ግን እንኳን ጥሩ ነገር ረሃባቸውን ሊያስታገስ የሚችል ምግብ አልሰጠቻቸውም፡፡ወይንን
“አይረባም” ብሎ ስም ከማጠፋት በስተቀር፡፡
ይህ የቀበሮ ህይወታችን ዛሬ ዛሬ በአብዛኛውህብረተሰብ ህይወት
ይንጸባረቃል ይህ ማለት ግን “የማይረባን “ ነገር አይረባም ከማለትየዘለለ አማራጭ ባይኖረውም የማይረባን ነገር የሚተካ ረሃብን
የሚያስታግስ መልካም ነገር እስካልመጣ ድረስ ከመንደር ወሬነት ባለፈ መፍትሔ አይሆንም ምን አልባት የተወሰነ ነገር ያመለክት ይሆናል፡፡
ነገር ግን ትችት ለበዛበት አገራችን መፍትሔ መጠቆምና ሥራ መሥራት እንጂ የሚረባት ጣት መቀሰርና አይረባም ማለት አይፈይዳትም፡፡
ለምሳሌ አይረቡም ከሚባሉት ተቋት ፓርላማው አይረባም፣ ሲኖዶሡ/ቤተክህነቱ/ አይረባም፤ ትምህርት ሚኒስትር /የትምርት ፖሊስው/ አይረባም፤
ማኀበረ ቅዱሳን አይረባም፣ የኢትዮጵያ ሬድዮና ቴሌቨዝን አይረባም፣EBS አይረባም፣ ESAT አይረባም፣ የመንግሥት ሚዲያ አይረባም፣የግል(የእንቶኒ) ጋዜጣ አይረባም፣ የግል ዩኒቨርስቲዎች አይረቡም፣ወንዶች
አይረቡም፣ ሴቶች አይረቡም፣ መ/ርእገሌ አይረባም፣ ፓስትረ እገሌ አይረባም፣ የነ እገሌ የዕምነት ተቋም አይረባም፣ አርቲስት እገሌ
አይረባም፣ህገ መንግስቱ አይረባም፣ ዳኞች አይረቡም፣ ጠበቆች አይረቡም፣ ብሄራዊ ቡድኑ አይረባም፣ አትሌት እገለወእገሊት አይረቡም፣NGO
አይረባም፣ የሃይማኖት ተቋም አይረባም፤ ዕድር አይረባም፤ ዕቁብ አይረባም፣ ፌዴሬሽኑ አይረባም፣
የቻይና እቃ አይረባም፣የእንትና መንግሥት አይረባም፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፓሊሲው አይረባም፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች አይረቡም፣ የፖለቲካ
(የዲሞክራሲ) ስርዓቱ አይረባም፣ የፍርድ ሂደቱ አይረባም፣ አስተሳሰባችንም አይረባም….. ወዘተ ብቻ የማይረባ ነገር የለንም ምክያቱም
ከምናመሰግነው ይልቅ የምንነቅፈው ስለሚበዛ ነገር ግን ከዚህ ነቀፋ በስተጀርባ ጸሐፊው የታዘበው ነገር ሰልነበረ ይህን ጽሁፍ ለመፃፍ
ተገዷል ብዙዎችን አይረባም ከማለት ባሻገር ምን ፈየድን ምን መፍትሔ
ምንስ የተሻለ ነገር አቀረብን? ምንም፡፡ አወራን እንጂ ምን ሰራን?ምንም ለአገራችን ማደግ ለህብረተሰባችን መለወጥ ስራ/ድርጊት/
እንጂ ወሬ አላጠረውም፡፡ ማውራት ማስረጃ አይጠይቅምና እናወራለን ሥራ ግን ትልቅ አቅምና ትልቅነት ይጠይቃል ታዲያ ለምን ራሳችንን
አንመዝንም? በመሥራት!
እስኪ የወቀስነውን የትምህርት ፖሊስ እንመልከት እንኳን እኔ/እኛ/
መንግሥትም እንደማይረባ መሻሻል እንዳለበት ያምናል ነገር ግን አይረባም ከማለት የዘለለ ምን አደርግንለት? ምንም፡፡ ነገር ግን
ይህ የትውልድ ምንጭ የዜጋ መቅረጫ ሥፍራ ሊወራበት ሳይሆን ሊሰራበት የሚገባ ነበር፡፡ በቃ! መንግሥት ሊሠራ የሚችለውን አደረገ
ከኛስ የሚጠበቅ ነገር የለም? ትናንት የተማርንበት ነገር ልጆቻችን ዕውቀትን የሚቀስሙበት የትምህርት ፖሊስያችን የፖሊስ ለውጥ ከእኛ
ይጠብቃል ከወሬ ይልቅ ሥራ ይናፍቀል፡፡ ፓርላማውም እንዲሁ ገብቶ የሚተኛ የሚያስቅ ነገር ሲነገር የሚባንንና የሚያጨበጭብ እጁን
የማውጣትና የማውረድ የሚቆጠር ሳይሆን ውሳኔ ሰጪ፣ ጥሩ አቋም ያለው፣ ራዕይ ያለው፣ የተቀመጠበትን ዓላማ ግብን የሚመታ ማኀበረሰብን
ማዕከል ያደረገ ሥራ የሚሰራ የፓርላማ አባል ያስፈልጋል ከዳር ተቀምጦ አይረባም ከማለት ረሃባችንን ሊያስታግስ ስደታችንን ሊቀንስ
የሚችል መፍትሔ የሚያመጣ አባላት ያስፈልጉናል፡፡
ሲኖዶሱ/ቤተክህነት/ አይረባም ሲባል ሁለት አሥርት ዓመታት
አስቆጥሯል ታዲያ መፍትሔው ሃያ ዓመት ሙሉ ስአለመርባቱ ማውራትነው ወይስ የሚረባበትን መንገድ መቀየስ፣ አንዲረባ ማገዝ፣ ወይስ
ምን ይሻላል ባለው አቅም መልካሙንም የሚስነቅፈውን እስከአሁን ሠራ ከአሁን በኋላስ የዘመንድ ቤት፣ የሙስና የተዘፈቀ፣ የተኩላ የመሸሺጊያ…
እንዳሆነ ይቀጥል ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ደም እንደተመሰረተች “የሲኦል ደጆች አይችሏትም” ተብላ በኛ ዘመን የወላድ
መካን ሆና ታንባ? ታልቅስ? ክፉ ነገር አውርተንባት ተጠቋቁመንባት ለጠላት አሳልፈን እንስጣት? በሌሎች የዕምነት ተቋማትም በመስኪድ
የፀሎት ሥርዓቱን የሚመራው፣ ምዕመኑን የሚያስተዳድረው፣
የሚያስመልከው፣ መጋቢው …..መንገድ ሲስት አርአያነት ሲጎለው እናውራ? አይረቡም እያልን እንቀመጥ? ወይስ ድራሻችንን እንወጣ
? እንዴት የተቻለ ፖሊሲ፣መተዳደሪያ ደንቦችን፣ እንቅረፅ እንሳተፍ ውጭ ከማውረት ጠጋ ብለን የሚረባ ነገር ረሀብን የሚያስታግስ
ከሽሽት ከስደት የሚመልስ ለአምልኮ እግዚአብሔር የሚጋብዝ ሥራ እንስራ፡፡
ማኀበረ
ቅዱሳን ማኀበሩ እንደሚለው ከ120,000 በላይ አባላት በመላው አገሪቱ እና በውጭው ክፍለ ዓለም ከሰንበት ትምህርት ቤት እስከ
ግቢ ጉባኤ /በዩኒቨርስቲዎች/ ያሉት ሲሆን በቤተክርስቲያኑልማታዊና መንፈሳዊ ግልጋሎቶችን ሲሰጥ ሃያ አመቱን ደፍኗል፤ ማኀበሩም
እንደሚያምን በድካም ውስጥ ጠንካራ ነገሮችን ሰርቷል “ኃይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ሁሉ እንችላለን” በማለትም አሁንም በስራ ላይ
ይገኛል::ከመምሪያው ኃላፊዎች ጀምሮ ብዙዎቹ አይረባም ይሉታል ታዲያ ይገኛል ከመመሪያው ኃላፊዎች ጀምሮ ብዙዎች አይረባም ይሉታል
ታዲያ ይህን የመሰለ በጎ ሥራ እየሰራ ያ ተቋም የቤተክርስቲያን ደጆች ሳይዘጉ፣ከወድቀታቸው እያንሰራሩ የአብነት ትምህርት ቤቶች
ቀኑ ሳይጨልምባቸው... እንዴት ይርባ? እንዴት ወደተሻለ አኳኃን ይሻገር? ጥያቄው እዚህ ጋር ነው ጥቄቶች “ይዘጋ” ይላሉ ይህ
የጠላት ወሬ ካልሆነ በቀር እንኳንስ ይህን የመሰለ ተግባር ያለው ቀርቶ ሃሳብ ይዞ የመጣ ይቋረጥ ሳይን እንዴት ይቀጥል በሚባልበት
ዘመን አይመከርም፡፡ እሺ ምን ይደረግ? ሥንል የሚሻሻልበትን መንገድ እንጠቁም ይህ ነው አገርን፣ ተቋመን፣ ህብርተሰብን… የሚጠቅመው
ችግሩን እንኳንስ እኛ ተቋሙም ያምናል ጠንካራ ነኝ ብሎ አይከራከርም፡፡
የኢትዮጵያ
የእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አይረባም፡፡ አዎ! አይረባም ታዲያ መፍትሔው ምንድን ነው? ሜዳ ገብተው ሲጫወቱ አትርቡም አንበላቸው
ወይስ ከሜዳ ውጭ ሜዳ ከመግባታቸው በፊት አሰልጣኝ እንቅጠርላቸው? ዳጎስ ያለ ደሞዝ/አበረታች/ ይከፈላቸው? የሚጎድላቸውን እናሟላላቸው?
በቂ የስልጠና ሥፍራ እናዘጋጅላቸው?... ወይስ ቁጭ ብለን ስለ አለመርባታቸው
እንነጋገር? የቱነው የኳስ ፍቅር ርሃባችንን የሚያስታግሰው? የቱስ የአገራችንን ስም በተሸለ ውጤት የሚያስጠራው? መነቃቀፍ ወየስ
መደጋገፍ?
የቻይና
ዕቃ አይረባም በኢህአዴግ ዘመነ ሥልጣን ቻይና 81 ብሔር ትሆናለች ብለው ይተነትናሉ ቀልደኞች እውነትም ከገጠር እስከ ከተማ ቻይናዊ
የማይገኝበት ድንበር የለምያገባት የስራ ዘርፍ ሻይና ፓስቲመንገድ ላይ መሸጥ ብቻ እስኪመስለን ድረስ ሁሉም ተቆጣጥረውታል አብዛኛው
ወደ አገር ወስጥ የሚገቡ ቃዎች የትውልድ አገራቸው ቻይና መሆኑን መርካቶን በእማኝነት መጥራት አሰገዳጅ አይደል ሁላችንም ምስክሮች
ነንና፡፡ነገር ግን ይህቺ ለአሜርካን ለአውሮፓ አምርታ የምታቀርብ አገር ወደ ኢትዮጵያ የምትለካቸው ዕቃዎቿ አይረቡም ይባላ?እንደያውም
ካጅማ የተባለው የመንገድ ስራ ተቋራጭ ከአዲስአበባ ደጀን ያለውን መንገድ ሲገነባ በጫማዋ ያቃጠለችን አንሶ በመንገዷ ልታቀጥለን
መጣች የሚል ምሬት አዘል ቀልድ ሲቀለድ እንደነበር የቅርብ ትዝታ ነው፡፡ አዎ አይረባም ነገር ግን ምን ይደረግ? የማይረባ ነገር
ምርት አገር እንደልሆነች የኢኮኖሜ ዕደገቷ ምስክር ነው ችግር የመግዛት እቅማችን የፈጠረው አቅርቦት ነው፡፡ ደሃ ከመሆናችን የተነሳ
የመግዛት አቅም አጠረን አዎ ቻይና የሚረባውንም የማይረባውንም እንደ መግዛት አቅማችን ትልካለች ብዙዎቻችን የመግዛት አቅማችን የወረደ
ከመሆኑ የተነሳ የምትልከው አይረባም፡፡ ባለመርባቱ ቻይና ተጠያቂ ናት? የሚረባ ነገር እንድትልክ ምን ይደረግ? እንዲህ በደፈናው
የቻይና እቃ አይረባም ማለት የተሟላ ወቀሳ አለመሆኑን የአሜሪካና የአውሮፓ ገበያ ምስክርነው፡፡ እነ ኢትዮ ቴሌኮም፤ እነ መብራት
ኃይል፣ የውሃናፍሳሽ፤ መንገድና ትራንስፖትስ አትረቡም ሥንላቸው እነርሱም
እንደማይረቡ ያውቁት ይሆን? ልብ ይስጥልን፡፡
ለማመላከት
ያህል ይህን ያህል ፀሐፊው ከተጋራ ቀሪውን ደግሞ አንባቢያን ልብ እንደምትሉት ተስፋ ያደርጋል፡፡ አዎ ሁሉም ቦታ ችግር አለ ሁሉም
ቦታ የማይረባ ነገር አለ እኛስጋ ረሃብ የሚያስታግስ፤ ከስደት የሚመልስ፤ ዕምባ የሚያብሰና ጫጫታውን የሚቀንስ ምን መፍትሔ አለ?
ወይንስ “ችግር አለ፤ “አይረባም” እያሉ ማውራት ብቻ ይሆን? የተፀናወተን ችግርን የሚፈታው ችግርን መጠቆም ብቻ ሳይሆን መፍትሔን
ማምጣት ነውና፡፡
እነዚህ
የጠቀስናቸውና ሌሎችም አይረቡም ብለን ተስማማን ግን ለዚህ ማህበረሰብ እነረሱ ካደረጉት አስተዋጽኦ የተሻለ ያደረግነው ነገር ምን
አለ? ለዚህ ማህበረሰብ ከቻይና ልብስና ጫማ ውጭ እኛ ምን ሰጠነው? ምን አጫማነው /ምን አለበስነው?/
ለዚህች
አገር ባለው ነባራዊ ሁኔታ ካለው “መንግሥት” ምን የተሻለ ነገር አደረግን ባለመርባት ውስጥም እያስተዳደረ እያለ የምንተችው መንግሥት
ነው: ለቤተክርስቲያንስ ቢሆን ከማኃበረ ቅዱሳን በተሻለ ምን ፈየድንላት? ካለው የትምህርት ፖሊሲ የትኛው ተቋም ትምህርት ሊያደርስ
ማን ቻለ? የተሻለ ፖሊስና አሠራር ያለው እኔ ነኝ ይበል ተንፍሱ ተያዩበት ተችቱ፣ አመስግኑ፣ አቅጣጫ አመልክቱ፣……(ልብ በሉልኝ
ቤተመንግስትም ሆነ ቤተ ክህነት ይረባልም አይረባምም ማለት አልፈልግም መለኪያ የለኝምና፣ ራሴን ማግለሌ ከፍርሐት እንዳልመነጨ ይታወቅልኝ
ተከባበሩ እንጂ አትፈራሩ እግዚአብሔርን ፍሩ ሠውን አክብሩ፡፡)
God bless Ethiopia!