ማክሰኞ 13 ጃንዋሪ 2026

እንዴት ልጆችን በሁለንተናዊ መስክ እናሳድግ?

መግቢያ 
 ማሳደግ የወላጅ ሥራ/ሚና ነዉ፤
 ወላጅ ማለት
  የሥጋ ወላጅ (እናት እና አባት) 
  መንፈሳዊ ወላጅ (መምህረ ንሰሐ፣ መምህራነ ወንጌል፣ ልጆችን በእለተ ሰንበት የሚያስተምሩ) 
  የእዉቀት ወላጅ (በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙ መምህራኖች)
  በእድሜ የገፉ ሰዎች ወላጅነት (በሰፈር፣ በጎረቤት)
  የአከባቢ ሰዎች
  ሞግዚቶች (በቤት ዉስጥ እና ከቤት ዉጪ)
  ቴክኖሎጂ የወላጅነት ድርሻን እንደ ወላጅ ሆኖ ፈቃድ ተሰጥቶን ሚናችንን እየቀማን ያለ ወላጅ

‹‹ ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራዉ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይለም›› መጽሐፈ ምሳሌ 22÷6

ü  ኦርቶዶክሳዊ ልጆች ለማሳደግ መጀመሪያ ወላጆች ኦርቶዶክሳዊ መሆን አለባቸዉ፤

ü  ስለልጆች ስናስብ ከወላጆች ስብዕና መጀመር አለብን ‹‹ምንጩ ከደፈረሰ ወንዙ መደፍረሱ አይቀሬ ነዉና››

ü  ጌታችን ሲያስተምር ‹‹ ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?›› የማቴዎስ ወንጌል 7÷16 እንዲል

ü  ሐዋርያትም ‹‹ሰዉ የዘራዉን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል›› ብለዋልና፤ ገላትያ 6÷7 ስለዚህ መምህራን በዚህ ሁሉ መንገድ ዉስጥ የመጡትን ልጆች ማሳደግ፣ ማስተማር፣ ማብቃት፣ … ይጠበቅባቸዋል፡፡

በሁለንተናዊ መስክ ስንል ምን ማለታችን ነዉ?

ሰዉ በሁለንተናዊ ነገሩ ማደግ አለበት ስንል በአካል፣ በእዉቀት፣ በማኅበራዊ ኑሮ፣ በመንፈሳዊ እድገት ማለታችን ነዉ፡፡

እንዴት እናሳድግ?

1.     ልጆችን ለማሳደግ ልጆችን ማወቅ ይገባል፤

2.     ልጆችን ስናሳድግ ለልጆቻችን አርአያ እንሁን፤

3.     ልጆችን ስናሳድግ ፍጹማን መስለን አለመታየት፤

4.     ልጆችን ስናሳድግ ሥነምግባር እናስተምራቸዉ፤ 

ልጆችን እንዴት እናስተምር/ምንስ እናስተምራቸዉ?

ይቀጥላል …




ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

እንዴት ልጆችን በሁለንተናዊ መስክ እናሳድግ?

መግቢያ   ማሳደግ የወላጅ ሥራ/ሚና ነዉ፤  ወላጅ ማለት   የሥጋ ወላጅ (እናት እና አባት)    መንፈሳዊ ወላጅ (መምህረ ንሰሐ፣ መምህራነ ወንጌል፣ ልጆችን በእለተ ሰንበት የሚያስተምሩ)    የእዉቀት ወላጅ (በትምህ...