ሰላም ወዳጆቼ እየደጋገመ/እየተመላለሰ ወደ አዕምሮዬ
እየመጣ የሚያስቸግረኝ በየአጋጣሚዉም የተለያዩ ጓደኞቼም ሲያነሱት የምሰማዉ ሲነሳም አጨቃጫቂነቱ ሰላም የሚነሳ ጉዳይ ዛሬ ልተነፍሰዉ
ፈለኩ፤ "ትዳር" በመፈላሰፍም/መንፈሳዊ በመሆንም/በመዘመንም … ዉስጥ ሆነን እናየዋለን አንባቢ እንደመሰለዉ ሊያቀናዉ
ሊያጣምመዉ ሊተቸዉ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ትዳር
የሚለዉን ቃል የከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት " ሰዉ ሁሉ በንብረቱ የሚተዳደርበት የቤት ስራ ፣ ባለ ጠጋም ሆነ ድሃ እንደተሰጠዉ መተዳደር" ብሎ ይፈታዋል፤
የትዳር ዉስጥ ድራማዎች
በመሰረቱ ድራማ እንደሚታወቀዉ በመድረክ የሚተወን፣ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚተላለፍ እና
የአጭር ጊዜና የረጅም ጊዜ ድራማዎች አሉ፡፡ እነዚህ በአጭርና በረጅም ጊዜ ተመጥነዉ የሚሰሩ ድራማዎች በባህሪያቸዉ
ü
ኮሜዲ (አስቂኝ )ወይም አዝናኝ
ü
ትራጀዲ
ü
ሆረር ( አስፈሪ) ከማዝናናት
ከማስተማር ባለፈ በአስፈሪነታቸዉ የሚታወቁ፤ ነገር ግን ምንም አስፈሪ ቢሆኑ መልዕክት ከማስተላለፍ ወደ ኋላ የማይሉ ናቸዉ፡፡
ልክ ከዚሁ ጋር ተመሳሳይነት ያለዉ ትዳርም በምድራችን ሁለት ነጠላ ሰወች " ትዳርን " ሲመሰርቱ የሚተዉኑት የህይወት ድራማ ይሆናል፡፡ እነዚህም፡-
ü
የማስመሰል ( በአንድ ቤት
መኖር ብቻ ህይወት አልባ ዓላማ የለሽ )
ü
እዉን የሆነና ህይወት ህይወት
የሚል
ü
ማስፈራሪያና ዛቻ የሞላበት
ከፍቅር ይልቅ ፀብ ጭቅጭቅ የነገሰበት
ü
የሚፈልገዉን (የምትፈልገዉን
) በማድረግ ብቻ (በማሟላት ብቻ) ፕሮዲዉሰር(አዘጋጅ ) መሆን ( እንደቤት ሠራተኛ) በማገልገል ድራማዉን የሚሰሩ ወዘተ
ታድያ ትዳርም ህይወት አልባ እንደሆነና ሌላን
ሠዉ መስለዉ የሚተዉኑበት ከሆነና የማይኖሩት ሁለቱ ነጠላ (ሲንግል) ሠወች በእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነዉ
እንደ አንድ ልብ አሣቢ ሆነዉ የማይኖሩት በድን አሻንጉሊት ከሆነ የሠዉ ልጅ ለምን ይጋባል? ለምንስ ትዳር ይመሰርታል? የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል፡፡
መቀጠሉ አይቀርም፤ እንቀጥላለን
ማሳሰቢያ ፡- የምንቀጥለዉ ግን በዉስጥም በዉጭም ባለዉ አስተያየታችሁ ላይ ተንተርሰን ነዉ፡፡