ሰኞ 26 ጃንዋሪ 2015

ሊሰራ የማይወድ አይብላ



ዳንኤል ክብረት "ቁስል ተራ " ብሎ የፃፈዉን ካነበብኩ በኋላ በልቤ ሲላወስ የነበረ ሐሳብ ስለነበር ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ ልተነፍስ ተነሳሁ፤ የርሱን ሐሳብ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡፡ http://www.danielkibret.com/2015/01/blog-post_20.html#comment-form ወዳጄ ዳንኤል ሥራ አልሆን ሲለን ወደ ልመና ከገባንኮ ቆይተናል፤ አንተ የአካሉን ሥትል ሰዉኮ ለመለመኛ ብሎ ልጅ መዉለድ ከጀመረ ሰነባበተኮ፡፡ በአንድ ወቅት ትራንስፖርት ዉስጥ ቁጭ ብዮ የሆነ ሰዉ ጋቢ ተከናንቦ የጉሉኮስ ዕቃ ታቅፎ አጥሚት አፉ ላይ እንደደረቀ ህፃን እየበረረ ታክሲ ዉስጥ አስጥሉኝ እያለ ገባ ከበስተጀርባዉ ስንመለከት ማንም የሚከተለዉ ሰዉ ስናጣ የባሰ አትኩሮቶቻችንን ሳበዉ …. ይህ ሰዉ ለካንስ ይህቺ ዘዴዉ የመለመኛ መንገዱ ነበረች ……. ወንበር ከመያዙ የልመና ቃላት ማዥጎድጎዱን ተያያዘዉ፤ ( ባጭሩ ታሞ ጥቁር አንበሳ ተኝቶ እንደነበረ፣ ከሁለት ወር በላይ እንደቆየ፣ ከክፍለ ሃገር እንደመጣ፣ በህመሙ ምክንያት ረጅም ጊዜ ስራ ገበታዉ ላይ ስላልተገኘ ከሥራ እንደተቀነሰ፣ በዚህ ምክንያት ቤተሰቡን ማስተዳደር ባለመቻሉ የልጆቹ እናት ጥላዉ ቤተሰቦቿ ጋር እንደሄደች፣ አሁን እንዲህ ሆኖ የተገኘበት ምክንያት ለህክናዉ የሚሆን ገንዘብ በመጨረሱና መድሐኒቱን ከወሰደ በኋላ/ በፊት የሚመገበዉ ምግብ በማጣቱ ከአልጋዉ ተነስቶ ለልመና እንደወጣ ነበር የነገረን፡፡ አስጥሉኝ ማለቱም ከሆስፒታሉ ሲወጣ ያዩት የጥበቃ ሰወችም ሆኑ ሲወጣ ያዩት የጤና ባለሙያዎችን ማለቱ ነበር፡፡) ሁላችንም ያለንን ያህል በተለመደዉ ኢትዮጵያዊ ሩህሩህ ባህሪያችን ሰጠነዉ፡፡ሰዉየዉም ለምስጋና እንኳን ጊዜ ሳያገኝ፣ ሊሄድበት የፈለገዉንም ፒያሳ ሳይደርስ እዉነት ይሁን ዉሸት ለጊዜዉ ባናዉቅም "የምበላዉ ካገኘሁ በቃ ወደ ሆስፒታል ልመለስ" ብሎ ወረደ፡፡
ከቀናት በኋላ ደግሞ ይኸዉ ሰዉ ራሱ በምሰራበት መስሪያ ቤት ጉዳይ ኖሮት ሊስተናገድ በጣም አምሮበት ጥቁር ሙሉ ልብስ በነጭ ሸሚዝ ለብሶ ጥቁር መነፅር ሰክቶ ከተፍ አለ፤ ድኖ በማየቴ ፈጣሪዬን ጤናዉን ስለመለሰለት አመሰገንኩት፡፡ ያንን ዕለት ስላደረግነዉ መልካም ነገር ደስታ እና ኩራት ተሰማኝ … … የአንድ ሰዉ ህይወት ታድገናልና፡፡ሥራ ቦታ መሆኔ ነዉ እንጂ እንኳን እግዚአብሔር ማረህ፣ እንኳን ደስ አለህ፣ … ብለዉ ደስ ይለኝ ነበር፤ ባለማለቴ እጅግ ቆጨኝ፡፡
በዚያኑ ሳምንት ቅዳሜ ዕለት አራት ኪሎ ወደ ፒያሳ ሄጄ ሲኒማ አምፔር ጋር ስወርድ ወርቅ ቤቶቹ ጋር ያደፈ ጋቢ ለብሶ ያቺ የፈረደባትን የጉሉኮስ ዕቃ ታቅፎ እያቃሰተ ወገን አድኑኝ እያለ የመጀመሪያ ቀን ያቀረበዉን ምክንያት እየደረደረ ይለምናል፤ በሱ ቦታ እኔ አፍሬ እያማተብኩ አለፍኩት የዋሁ ህዝብ ጉዳዩን አላወቀ ሳይኖረዉ ካለዉ ላይ የቀረችዉን እያነሳ ሳይሳሳ ይሰጣል፡፡ የሌለዉ ከንፈሩን በሀዘኔታ እየመጠጠ "እግዚአብሔር ይማርህ እያለ ያልፋል" የሰዉ ልጅ ለምንድነዉ ርካሽ የሆነ ባህሪ የሚመቸዉ ብዬ ታዘብኩ፤ ….
ከጊዜ ብዛት ከተማ ዉስጥ ስዘዋወር በተደጋጋሚ ሳገኘዉ ባህሪዉ መጥፎ የምንለዉ አይነት ሰዉ ነበር ( ያጨሳል፣ በጣም ይጠጣል፣ ቁማር ይጫወታል፣ … ) ከረጅም ጊዜ በኋላ ለሆነ ንግስ በዓል ነጭ በነጭ ለብሶ ከጓደኞቹ ጋር አገኘሁት የኔ ቢጤ ሲለምነዉ መርጦ አዉጥቶ 10 ሳንቲም ሲሰጥ አየሁት፤ ፈራ ተባ እያልኩ "መስጠትም ታዉቅበታለህ? " አልኩት፡፡ "ምነዉ መስመር ላይ ተገጣጥመን እናዉቃለን እንዴ ?"አለኝ፤ ….
ባጭሩ ከዚህ ሰዉ ጋር ባደረግነዉ ዉይይት የቅድሙ ታሪክ ሁሉ ዉሸት እንደሆነና ከመስራት መለመን አዋጭ እንደሆነ በድፍረት ነገረኝ፤ ሰዉ ሆይ ስራ መስራትን ጠልተን ልመናን የምንኮራበት እና የምንመርጠዉ እስከ መቼ ነዉ?ልንሰራስ የማንወደዉ ለምንድን ነዉ?
ሊሰራ የማይወድ አይብላ! ያልሰራ አይብላ አላልኩም ስራ አጥቶ ሊሆን ይችላልና፤ በየስራ ገበታዉም ያላችሁ ለታይታ የምትሰሩ፣ የአለቃን ፊት እያያችሁ የምታለምጡ፣ የሰዓት መቆጣጠሪያ ላይ ለመፈረም ብቻ የምትገቡ፣ … እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ፡፡

ማክሰኞ 13 ጃንዋሪ 2015

Ethiopia Zone9: " ህልም አንደሆነ አይታሰርም " ጦማሪ አቤል ዋበላ

Ethiopia Zone9: " ህልም አንደሆነ አይታሰርም " ጦማሪ አቤል ዋበላ: ‹‹ ስሜ አቤል ዋበላ ነው፡፡ አዲሱ አመት ሲጠባ በአዲስ መንፈስ አዲስ ህልም ለአገሬ ማለም የነበረኝንም ማጠናከር እፈልጋለሁ፡፡ ኢትዮጵያችን የብሄር፣ የሃይማኖት፣ የሀብት፣ የትምህርት፣ የፖለቲካ አመለካከት እና ሌሎች...

እሑድ 4 ጃንዋሪ 2015

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: የትልቁ ዋርካ ትልቁ ቅርንጫፍ

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: የትልቁ ዋርካ ትልቁ ቅርንጫፍ:   click here for pdf ታኅሣሥ 19 ቀን 2007 ዓም በቤተ ክርስቲያን ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ከታወቁት ሊቃውንት መካከል አንዱን አጥተናል፡፡ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየን፡፡ ስለ ሥርዓተ ...

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: እንደ ሰው ወይስ እንደ እንስሳ

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: እንደ ሰው ወይስ እንደ እንስሳ: click here for pdf   The Indian Folktales በተሰኝ ከዛሬ 100 ዓመት በፊት በ1919 እኤአ በታተመ መጽሐፍ ላይ እንዲህ ይላል፡፡ አንድ የሕንድ ጠቢብ ደቀ መዝሙሮቹን ሥራ እንዲሠሩ አዘ...

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...