"ሰዉ
እናቱንና አባቱን ይተዋል፤ … " ባል ከሚስቱ ሚስትም ከባሏ ጋር ይተባበራሉ ሁለቱም አንድ ስጋ ናቸዉና፡፡ በትዳር ዓለም
ዉስጥ በባህልም በሃይማኖትም የምንስተዉ ስህተት ይህ ነዉ አንድ አለመሆናችን አለመተባበራችን፡፡ ትዳር አዲስ አለም መመስረት እንደመሆኑ
መጠን ሁሉ ከአዲስ መንደር ባልተናነሰ መልኩ ብዙ መሟላት ያለባቸዉ የህይወት መሰረተ ልማቶች አሉ፡፡ እስካልተሟላ ድረስ ችግሮች
መኖራቸዉ አይቀሬ ነዉ፡፡ ወደ አንድ የሚያመጣ የፍቅር መንገድ፣ ቁጣን የሚያበርድ የትዕግስት ዉሃ፣ ብዥታን የሚያጠፋ የመተማመን
ብርሃን (መብራት)፣ አረፍተ ዘመን እስኪገታን ስንቅ የሚሆን የፍቅር ምግብ፣ አንዳችን ለአንዳችን መከታ ሆነን የምንኖርበት የተስፋ
መጠለያ፣
… ወዘተ ግድ ያስፈልጉናል፤ ይህን ጊዜ ሰዉ እናት እና አባቱን ይተዋል፡፡
ባል/ሚስት
ይህን መሰረተ ልማት (ትዳር) ሲያጡ የፍቅር ረሃብ ለማስታገስ እናታቸዉ ጋር፣ ተስፋ በማጣት መከታ ወደ ሆነ አባት መሄድ ግድ ይሆናል፡፡
ስለዚህ ለነዚህ ችግሮች መፍትሔ ሁለቱም ግዴታ አለባቸዉ፡፡ በመሰረቱ እነዚህ ጎደሉ ተብሎ የትም አይኬድም፤ ስንጀምር እንዳነሳነዉ
በባህልም በሃይማኖትም የምንስተዉ ስህተት ስለሆነ እንጂ፡፡
ብዙሃን
ኢትዮጵያዊያን ትዳር የምንመሰርተዉ እስከቤተሰቦቻችን ስለሆነ አብዝቶ ችግሩ ይስተዋላል፤ ባልም ሚስትን ቤተሰቦቼንማ አትንኪብኝ፣
ሚስትም ባልን በቤተሰቤማ አትምጣብኝ፣ ወዘተ መባባሉን ይጀምራሉ፡፡ ችግሮችን በጋራ እንደመፍታት ችግር ለመፍጠር እንደተደራጀ ቡድን
እለት እለት ጭቅጭቅ እና ንዝንዝ የበዛበት ህይወት ይመራሉ፡፡