ስምዖን ጌታን ታቅፎ
ክፍል ፪
ባለፈዉ ክፍል አንድ ላይ ረድኤተ
እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ጀምረን ስለ አዉግስጦስ ቄሳር አመጣጥና ንግስና ተመልክተን አዉግስጦስ ህዝቡ እንዲቆጠር ለምን እንዳደረገ አንስተን ነበር ያቆምነዉ፤
እነሆ እግዚአብሔር ለዚህ አብቅቶን ክፍል ሁለትን እንዲህ ይዘን መጥተናል ይከታተሉን። ያስጀመረን በሰላም ያስፈጽመን!
ክፍል ፪ እንዲህ ይቀጥላል፡ ማስተዋሉን ይስጠን!
ዩሴፍ፡- ከሽማግሌዎች
ወገን ስለነበር /ስለተወለደ/ ስሙን ብልዮስ ቄሳር ብለዉታል።ብልዮስ ቄሳር ጋስዮስ ቄሳርን ጋስዮስ ቄሳር አዉግስጦስ ቄሳርን ይወልዳል፤የአዉግስጦስ
ቄሳር አመጣጥ እንግዲህ ይህንን ይመስል ነበር።አነጋገሱ ደግሞ ህዝቡ
በሀገራቸው አንድ ኃይለኛ ጠላት ተነስቶ አስቸገራቸዉ አጥፋልንና እናነግስሀለን
አሉት፡፡ እርሱም ኃያል ስለነበር በኃይሉ ተማምኖ ከአነገሣችሁኝ እሺ
በእጄ ብሎ አጥፍቶላቸዋል፡፡ እነርሱም ቃል እንደገቡለት አንግሰውታል፡፡በቃ…..
-ታዲያ አውግስጦስ ቄሳር ሕዝቡ እንዲቆጠር ያደረገው ለምንድነው?
ዩሴፍ፡-
ከእርሱ
በፊት የሶሪያ አገረ ገዥ የነበረው ቄርኒዎስ አስቆጥሮ ነበርና እርሱም በሮም ውስጥ ሊያስቆጥር ችሏል፡፡ እኛም ለመቆጠር በቅተናል፡፡
-ወደዚህ ቆጠራ ስትሄድ አብራህ ማሪያም የምትባል እጮኛህ እንደነበረች
ይነግራል ፡፡ ይህ አንዴት ነው?
ዩሴፍ/- አዎ/ እጮኛዋ/ጠባቂዋ/ የነበርኩት እኔ ስለነበርኩ የማይካድ ነው፡፡ አብራኝ በቆጠራውም ላይ ከዚያም በኋላ ልጇን ወልዳ ከዚያም ደገሞ ስተሰደድ
አብራኝ ነበረች፡፡ እንዲያውም እነሰሎሜ የዓይን እማኞች ናቸው፡፡ እዚያው ሣለን ነበር ምጧ መጥቶባት ልትወልድ የደረሰችው፡፡
-እሺ አባታችን እንግዲህ እስካሁን
የጥያቄያችንን መንደርደሪያ ወይም የታሪኩን የስር መሰረት ነበር ስታጫውተን የነበረው አሁን ደግሞ ወደ ዋናው ጉዳያችን እንመለስና
ያንን የስደት ጉዞ እንዴት ነበር ያሣላፍከው? ብትብራራልን፡፡
ዩሴፍ፡- እንግዲህ ስለጉዞ ብዙ ካልኩህ እኔንም አንተንም ደስ ባለን ነበር፣ በቃላት መግለጹ ግን በዓይን
እነዳዩት እና እንደተሣተፉበት አይሆንም፡፡ለማንኛውም ግን፡- (ቅዱስ
ዮሴፍ እጅግ በሃዘን ተዋጠ) ጉዞው በጣም ግራ የሚገባ ነበር፡፡ ሳላስበው
ድንገት ነበር ማሪያምን ይዤ እንድጓዝ በመልዐኩ በኩል ትዕዛዝ የተላለፈልኝ እንኳን ላልተወሰነ ወራት የሚጓዙት አስፈሪ ጉዞ/ስደት/ይቅርና
የመጓዝ /የመሰደድ/ አቅም አልነበረኝም፡፡ ነገር ግን እንደፈራሁት
ሳይሆን አብሮን የነበረው ኤልሻዳይ /ሁሉን ቻይ/ ህጻን ብዙ ተአምራትን እያደረገ ስንጓዝ በኋላም ተወልዶ ካደገና ብዙ ተአምራትን
እያደረገ ሲያበረታታንና ሲያጽናናን ደሰታ እየተሰማን ነበር የተጓዝነው፡፡
-ቅዱስ ዩሴፍ ስለጉዟቸው ከነገረን
ወዲያ ቅድስት ሰሎሜንም አግኝተን ቅድስት ሰሎሜ መቸስ ከስደቱ ከነበሩት
መካከል ሴት አንቺ ብቻ ነበርሽ ህፃኑ ሲወለድ እናቱ አንደ ሴቶች ልማድ የሚያስጨንቅ ምጥ ነበረባት? ብለን ለጠየቅናት እንዲህ ብላን ነበር፡-
ሰሎሜ፡- በእርግጥ ሴቶች ህፃኖቻቸውን
ሲወልዱ/ ሲገላገሉ/ በጣም የሚያስጨንቅ መዉለድን የሚያስጠላ ምጥ ያጋጥማቸዋል፡፡ ይህ የሴቶች ልዩ ስጦታ/ባህሪ/ነው፡፡ በማርያም
ግን እንኳን የሚያስጨንቅ ምጥ ይቅርና የሚያረጋጋ እና የሚያሰደስት ምጥ እንኳን ቢኖር (ፈገግ እያለች)አላጋጣማትም::ዩሐንስ በራዕዩ
ስለእመቤታችን በራዕይ 12፣1-17 በምሣሌ ስለእመቤታችን የጻፈውና “በምጥ ተይዛ ስትወልድ ጮኸች...” ማለቱ በሌሎች የሴቶች ልማድ
ማናገሩ ነው እንጂ በእመቤታችን ይህ ሁሉ የለባትም፡፡
ምክንያቱም በማህፀኗ የተጸነሰው
አምላክ ወልደአምላክ አስጨንቆ በምጥ፣ በጣር፣ በጋር የሚወለድ ሣይሆን ምጥን ጣርን ጋርን የሚያስወግድ: የድንግልና በሯን ሳይከፍት/ክብረንጽህናዋን/
ሳይጓድል እንደገባ ሳይከፈት የሚወጣ ነው፡፡
ነቢዩ ህዝቅኤል እና ኢሣይያስ ያሉትን
አልሰማህም እንዴ ህዝቅኤል “...ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም…” ያለው በር እኮ ማህፀኗን /ድንግልናዋን/ ነው፣
ታዲያ ሣይከፍት ገብቶ ሣይከፍት ከወጣ ምጥ ከምን ይምጣ? ህዝቅኤል 44፣1
ደግሞም ምጥ በእርግማን ምክንያት
የመጣ ነው፡፡ ሔዋንን “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛዋልሁ፡ በጭንቅ ትወልጃለሽ፣” ዘፍጥረት 3፣16 ተብላ ነበር፡፡እመቤታችን ግን
የአዳም ኃጢያት በዘር ያልተላለፈባት ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ ነጻ የሆነች ንፅህት: ቅድስት ናት ስለዚህ ምጥ የሚባል ነገር
አላያትም፡፡
-ቅድስት ሰሎሜ አንቺስ እንደ ሴትነትሽ
መጠን መቸስ ብዙ መከራን ከህፃኑ እናት ጋር በስደቱ ወቅት ተቀብለሻል የፀሐዩ ዋዕይ የሌሊቱ ቁር ረሀብና ጥሙ ቀላል አልነበረም፡፡
ታዲያ ይህ ሁሉ እንዴት አደረገሽ?
ሰሎሜ፡- ያልከዉ ከእዉነት ያልረቀ ሀቅ ቢሆንም
እንደስጋችን ድካምና እንደ ሴትነቴ ቢሆን የማይቻል ነበር፤ነገር ግን ስደታችን ኃያልና ኃይልን ከሚሰጠዉ ጋር ስለነበር ስደታችን
ምንም አልተሰማኝም።
-ጥያቄ እያበዛሁብሽ ከስደቱ ይልቅ
እኔ ሳላደክምሽ አልቀረሁም ፤ ለመሆኑ ስደቱን ጨርሳችሁ ከግብጽ ስትደርሱ የተሰማሽ ምንነበር?
ሰሎሜ፡- መጀመርያ ስደትን ስለማላዉቀዉ ገና
ስጀምር ወይም ስንሰናደድ ፍርሃት ነበረብኝ፤ ነገር ግን አብሮን የነበረዉ የኢሳይያስ ህጻን አይዟችሁ እያለ የሚያጽናናን ስለነበር
ፍርሃት ድካም ሰቆቃዉ ተወግዶ ብርታት ለማግኘት ችያለሁ። ስንመለስ ያለዉን ደስታ እንዴት እንደነበር በምን አይነት ቃላት እንደምገልጽልህ
ግራ ይገባኛል። የደስታ ምንጩ ጋር ቁጭ ብዬ እንዲህ ነበር ብዬ እንዴት ልንገርህ? አንደኛ የመከራዉ መገባደድ ያስደስተኛል፡ በሁለተኛ
ደረጃ ራሱ ህጻኑ ልጅ ሆኖ ሳለ በዚያ እድሜ ድንቅ ድንቅ ተኣምራትን ሲሰራ ያስደስተኛል። ከሁሉም በላይ ለማዳን ብለን ይዘነዉ የተሰደድነዉ
ህጻኑ ራሱም ተርፎ እኛንም አትርፎ ለዚያች ሰዓት ነፍሳችንን ይዘን ወደ አገራችን መመለሳችን አስደስቶኛል። በአጠቃላይ የተሰማኝ
ደስታ ነበር።
ለመሆኑ ቅድስት ሰሎሜ አሁን ካልሽዉ
መሃል ሕጻኑ የሰራዉ ተኣምራት እንዳስደሰተሽ ተናግረሽ ነበር የገለጽስሽልን፤ እስኪ በስደታችሁ ላይ ካጋጠሙሽ ተኣምራት መካከል ጥቂቱን
ብትገልጪልን?
ሰሎሜ፡-ተኣምሩ ብዙ ነበር፤ቢሆንም ዋናዋናዉን ማስታወሻም ያለዉን አንዳንዱን እነግራችኋለሁ፡-ይኀዉም
ጌታ በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ ቤተልሔም በእሳት ቅጽር ታጠረች፡ አጋንንት እናያለን ብለዉ ቢመጡ መላዕክት በሐጸ እሳት እየነደፉ
የማያስቀርቧቸዉ ሆኑ ሄደዉ ላለቃቸዉ ለዲያብሎስ ነገሩት እስቲ ተሸክማችሁ ዉሰዱኝ አላቸዉ፤ በኪሩቤል አምሳል እርሱም አራት ጸወርት
አበጅቷልና ተሸክመዉ ይዘዉት ቢመጡ የማይሆንለት ሆነ። ከዚህ በኋላ ከሄሮድስ
ላከበት የእኔን ሥልጣን መንግሥት የሚቀማ ንጉሥ ተወልዷልና እርሱን ግደል (እንግደል) ብሎ ላከበት፤ እርሱም እነደምን
ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ይልክበታል፡- ለዚህማ ምን ቸገረህ ዓመት ተመንፈቅ ሁለት ዓመት የሆናቸዉን ሕጻናት ልብስናቀለብ እሰጣለሁና
ሰብስቡልኝ ብለህ አዋጅ ንገር አለዉ፤ እነዳዘዘዉ አደረገ። በዚህን ጊዜ መልዐኩ ዮሴፍን ተነስ ሕጻኑንና እናቱን ይዘህ ሂድ ብሎታል።
ከዚህ በኋላ ያላቸዉ ልጆቻቸዉን የሌላቸዉ ቀለብ እንቀበልበታለን እያሉ ልጅ እየተዋሱ ሂደዋል።እንደዚህ አድርገዉ 14ሺ ከ4 ሕጻናት
አስፈጅቷል።ነገርግን ሕጻኑን/ጌታን/ ሊያገኙት አልቻሉም። ከዚያ በኋላ ግብጽ ወረደ ብለዉ ነገሩት፡አራት አለቃ ከነጭፍራዉ ሸልሞ
ይህ የዕለት ሽልማታችሁ ነዉ፡ይዛችሁትያመጣችሁልኝ እንደሆነ ሙሉ ሽልማት እሸልማችኋለሁ ብሎ ሰደዳቸዉ።እነዮሴፍ ሲሄዱ ከጊጋር ቤት
ሰንብተን ሄደናል፣ዮሳ የተባለዉም የዮሴፍ ልጅ ታሞ ከጊጋር ቤት ቀርቶ ነበርና የጊጋር ሰዎች አራት አለቃ ከነጭፍራዉ ይዛችሁ አምጡልኝ
ብሎ ሰደደ ሲሉ ሰምቶ ከዚያ ተነስቶ ሲሄድ ሰይጣን ከመንገድ ቆይቶ ወዴት ትሄዳለህ? አለዉ፡፡ እነዚያማ ቀድመዉህ ሄደዋል ይህን
ጊዜማ ገድለዋቸዉ ይሆናል፡ ተመለስ እንጂ ምን ያደክምሃል? አለዉ። አሁንም ሞተዉም እንደሆነ እቀብራቸዋለሁ ያሉም እንደሆነ እነግራቸዋለሁ
ብሎ ኃይል ተሰጥቶት ፈጥኖ ደረሰባቸዉ። ዮሴፍና ማርያም ደክመዉ ወድቀዉ ጌታ አካሉ ቢወዛ እያጠብኩት ሳለሁ አግኝቶኝ እናንተ!ከዚህ
በጤናችሁ አላችሁ? በዚህ ሕጻን ምክንያት አሁን በገሊላ በክንዷ ልጅ የታቀፈች ሴት አለችን? አለ። በዚህ ጊዜ ማርያም ደንግጣ ልጇን
ከእኔ ተቀብላ የቀን ሐሩር የሌት ቁር የተቀበልኩብህ ከሞት ላላድንህ ነዉ? ብላ አለቀሰች።
ልጇም ዩሳን አመጣጥህ ዋጋ የሚያሰጥ
መልካም ነበር ነገር ግን እናቴን ስለአስደነገጥካት በምፅአት አስገብቼ ዋጋህን እስክሰጥህ ድረስ ይህችን ድንጋይ ተንተርስህ ተኛ
ብሎት ከዚያ አርፋል፡፡ ከዚያ ተነስተን ስንሄድ ደርሰውብናል፡፡ ታላቅ
ሾላ እንጨት ነበረች ሰውሪን ብንላት ከነአህያችንና ከነሰዎቻችን ተከፍታ ሰውራናለች እነርሱም አህያው ከውስጥ ሆኖ ቢያናፋ የአህያውን
ጩኸት እየሰሙ ቦታው ጠፍቷቸው ሲዞሩ ሰንብተው አጥተውን ተመልሰዋል፡፡
ከዚያም ተነስተን እመቤታችን ከልመና
ሔደች ሰይጣን የሰውን ልቦና እያፀናባት የሚዘክራት አጥታ ብትመለስ ሰብዓሰገል ያመጡላትን የወርቅ ጫማዉን ሌባ ወሰደባት ልመናም
ሄጄ ላላገኝ የልጄን ጫማ አስወስድኩት ብላ ምርር ብላ አልቅሣለች በዚያን ጊዜ እንባዋ በልጇ ፊት ላይ ፈሰሰ። ከዚህ በኋላ
ጌታ ለቅሶዋን አይቶ ከድንጋይ ውሃ አፍልቆ አጠጥቶናል፡፡ አንድም
ከዚያ ተነስተን ስንሄድ ከትዕማን ቤት ልመና ገብተን ስንለምን ትዕማን እመቤታችንን አይታ “ከወደየት መጥተሻል?” አለቻት እርሷም
ከምድረ ይሁዳ አለቻት:“ደረቅ ኃይለኛ ብትሆኚ ይሆናል እንጂ እንዳንቺ ያለች ቆንጆ ከመጋረጃ ትወጣለች?” አለቻት ዩሴፍም:- ለትዕማን “ለለማኝ ቢኖር ይዘከሩታል: ባይኖር
ካለው ያድርስህ ይሉታል እንጂ እንደ ፍላፃ ልብ የሚወጋ ነገር ምን ያረግልሻል?” አላት፡፡ ኮቲባ የምትባል ወደል ባሪያ አለቻት ይህ የፍየል እረኛ እመቤቴን እንደምን
ይናገራታል ብላ ደርቡን እያነዋወጠች ወርዳ እሱን በጥፊ መታው ጌታን ከእመቤታችን ነጥቃ ከምድር ጣለችዉ ጌታ ትዕግስት ልማዱ ነውና
ዝም ብሏት ያለቅስ ጀመር በዚህ ምርር ብላ አልቅሣለች ዕንባዋ በፊቱ
ላይ ወርዷልና እንዲህ አለ፡፡ እመቤታችን ልታነሣው ብትሔድ ዩሴፍ “ተዓምራቱን ይዩ አምላክነቱን ይግለጽ ተይው አታንሽው” አላት፡፡
-
ትዕማንን ከነገረዶቿ ምድር ተከፍታዋጠቻት:
-
ቤተሰቦችዋም ጦጣ ዝንጀሮ እየሆኑ የገዛ ውሾቻቸው እያባረሯቸው ወጥተው ሄደዋል፡፡
-
ከጐረቤትም ጩኸት ሰምተው እንረዳለን ብለው ቢመጡ ግብር አበርነታቸውን አይቶ ከዚያው ደርሷቸዋል፡፡ ዩሴፍ እንደአዛዥ
እኔም እንደአበጋዝ ጌታ እንደ ንጉስ እመቤታችን እንደ ንግስት ሁነን ከቤቱ ገብተን መንፈቅ ተቀምጠናል፡፡
በመጨረሻም ከስደት ስንመለስ ከመንገድ
ደክመን በረሃ ለበረሃ ስንጓዝ ፈያታዊ ዘየማንና ፈያታዊ ዘፀጋም የተባሉ ሁለት ወንበዴዎች አጋጥመውን በዚህን ግዜ ሁላችንም ተደናግጠን ጌታን የተውልኝ መስሎኝ ልብሴን አውልቄ ሰጠኋቸው እነርሱም
ስድስት ቀን ጠፍተንባቸው በሰባተኛው ቀን አግኝተውን ነበርና ምነው እስከ ዛሬ ታደክሙናላችሁ አሁንስ እግዚአብሔር ከእጃችን ጣላችሁ አሉንና ሰብዓሰገል ያመጡለትን ስረወፅ
ቀሚስ ያቺን ወስደውብን ከሄዱ በኋላ
እልፍ እንዳሉ ፈያታዊ ዘየማን እኒህ ሰዎች የቤተመንግስት ሰዎች ናቸው መሰለኝ አሳዘኑኝ እንመልስላቸው አለ፡፡ ነገር ግን የሚቀሙት በተራ ነበርና ተራዉ የፈያታዊ ዘፀጋም ስለነበር አይሆንም
ብዙ ዋጋ ያወጣልኛል አለው ፈያታዋ ዘየማንም ከቤቴሌሔም ጀምሮ እስከዚህ የቀማነው የአንተ ይሁን ይሄ የእኔ ይሁን ብሎ መልሶልናል፡፡
ጥጦስ ጌታን ከእኔ ተቀብሎ ተሽክሞ ሰይፋን እየተመረኮዘ ሲሸኘን ተሰበረበት “ምነው ‘ወርቅ ላበደረ
ጠጠር እህል ላበደረ አፈር’ እንዲሉ በጐ ብሠራ ሰይፌን ሠበርክብኝ” ብሎ አዘነ ጌታም “የተሰበረውን ሰይፍህን ከሰገባው አስገባው:”
አለው እንዳለው ቢያደርግ ደህና ሆኖ አገኘው፡፡ እርሱም ደስ ብሎት
“ይሄ ብላቴና ከደቂቅ ነቢያት ወገን ነው” አለ፡፡
ሌላው ደግሞ እንደ ኦሪት ስርዓት
በስምንተኛው ቀን ወደቤተመቅደስ ይዘነው ሄደን ካህኑ ሊገርዘው ቢል ምላጩ ዉሃ ሆነ እንደገናም በገዛ ፈቃዱ ምላጭ ከሰውነቱ ላይ ሳያርፍ ተገርዞ ታይቷል፡፡ እንግዲህ ካየኋቸው ተዓምራት መካከል ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል፡፡
-እኛም ከቅድስት ሰሎሜ ጋር ለሰፊ
ስዓት አብረን ከተጫወትን በኋላ ወደ ቅዱስ ዩሴፍ ተመልሰን እንደዚህ ብለነው ነበር፡-በስደታችሁ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ እንደሄዳችሁ
ይነገራል መሄዳችሁ እዉነት ነው?
-ዩሴፍ፡- አዎ መሔዳችን እርግጥ ነው መሄዳችንም እኛ አውቀን ያደረግነው
ነገር ብቻ ሣይሆን ትንቢቱም በነቢዩ ዕንባቆም ተተንብዩ ስለነበር ነው፡፡ ዕንባቆም 3፣3-7
“...እግዚአብሔር ከቴማን ቅዱስም
ከፋራን ተራራ ይመጣል ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል፡፡ ፀዳሉም እንደ ብርሃን
ነው ጨረር ከእጁ ወጥቶአል ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል፡፡ ቸነፈር በፊቱ
ይሄዳል የእሳት ነበልባል ከእግሩ ይወጣል፡፡……… የኢትዮጵያ ድንኳኞች ሲጨነቁ አየሁ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ…” ብሏልና በትንቢቱ መሰረት የፋራን ተራራ የተባለችን እመቤታችን ስትሆን ከፋራን
ተራራ ይመጣል የተባለው ደግሞ የተወለደው ሕፃን/ኢየሱስ ክርስቶስ/ ነው፡፡
ድንኳን ደግሞ የሰደተኞች ማረፊያ ነው፡፡ “…የኢትዮጵያ
ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ”የሚለው ዐረፍተ ነገር የእመቤታችን ስደት ወደኢትዩጵያም እንደምንሄድ የሚያመለክት ነበርና ስለዚህ ተጉዘናል፡፡
ለጊዜው ከቅዱስ ዩሴፍ ጋር ያለንን
ቃለመጠይቅ ማገባደጃ የመሰልንን ጥያቄ ለዚህ ትውልድ ካያችሁት ከምታውቁት የምታስትላልፋት ምን መልዕክት አላችሁ? ብለን ጠይቀናል፡፡ እነርሱም ከተመካከሩ በኋላ በዩሴፍ አማካይነት እንዲህ ብለውናል፡፡
ዩሴፍ፡- እኛ የምንለው ብዙ ነገር አለም የለምም ምክንያቱም ትውልዱብዙ ያውቃልና፡ አንድም በሌላ
መልኩ ማወቅ ደግሞ የእግዚአብሔርን ማንነት ሊያሳውቀው እግዚአብሔር ከሚያድለው ክብር ስላላደረሰው እኛ የምንለው ይህ የተወለደው
ሕፃን ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑ ቀርቶ ሰው ብቻ ነው ብለው እናቱንም ወላዲተ ሰብዓ ብለው የሚረዱ ሰላሉ አምላክነቱን ለማረጋገጥ
እንዲችሉ ከፅንሰቱ ጀምሮ እስከ ልደቱና ከዚያ በኋላ ስላለው ፍፁም
አምላክነቱ ኢሳይያስ ከ740 ዓመት በፊት ፅፎት የነበረው የትንቢት ቃል መመልክት መልካም ነው፡፡ ኢሳ7፣14 ማቴ፣1፣23 የተወለደው
ሕፃን አማኑኤል የተባለው ቢወለድም አምላክ በመሆኑ ስጋን ነስቶ ፍፁም
ሰው መሆኑን ስለመገለጥ ነበር፡፡ ከዚህ ሌላ አሁንም በትንቢት… ሕፃን
ተወልዶናልና…. ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፡፡ የሚል ቃል እናገኛለን፡፡ ኢሳ 9፣6 በቤተልሔም ዋሻ ሰብዓ ሰገል ወርቅ ዕጣን ከርቤ መብዐ አድርገው
ያቀረቡላት እኛ የሰገድንላት ከብቶቻችንም በትንፋሻቸው ያሟሟቁት ሕፃን
ኢየሱሰ ክርስቶስ አምላክ ስለሆነ ስሙም ኃያል ተብሎ እንደሚጠራ ልንመክራቸው እንወዳለን፡፡
-
ከስደቱ እንዴት ነበር ልትመለሱ የቻላችሁት? ብለን ጥያቄ አቀረብንለት
-
ዩሴፍም፡- ተነስተህ ብላቴናውንና እናቱን
ይዘህ ወደምድረ እስራኤል ተመለሰ የዚህን ብላቴና ነፍስ ለማጥፋት የሚሹት ሰዎች ጠፍተዋልና… ብሎ መልዐኩ ስለነገረን ነዉ፡፡
-
እነዚህ የጠፉት እነማን ነበሩ?
-
ዩሴፍ፡- ዩሐንስ በፊጥሞ ደሴት ታስሮ
በራዕይ ካየው ራዕይ 12፣1-6 የተጻፈውና ዩሐንስ ዘንዶው እያለ የሚጠራው አጋንንት ያደሩበት ሄሮድስ ነው፡፡
-
መቸስ ይህንን ሁሉ ከመነጋገራችን በፊት የልደቱን ቀን ነበር ማወቅ ያለብን ለመሆኑ መቼ ነበር
የተወለደው?
-
አስቀድሞ ትንቢት እንደተነገረለት ያ አምስት ቀን ተኩል ሲፈጸም ነዉ፤ በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር
/በ5500/ በአንድ ዓ.ዓ. በዘመነ ማቴዎስ በታህሣሥ 29 ቀን ማክሰኞ
ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ነበር፡፡
-
አስቀድመን በጉዞአችሁ ያደረገውን ተዓምራት ነግራችሁናል በዕለተ ልደቱ የተደረገውን ብትነግሩን?
ስንላቸው እነርሱም፡--
-
1. የተወለደበት ሰዓት ሌሊት ሲሆን ብርሃን ከሰማይ ወርዷል ምክንያቱም መላዕክት ለእረኞች
ሲናገሩ አይተዋል ሉቃስ2፣39
-
2. የእግዚአብሔር መልአክ መጥቶ ለከብቶች
ጠባቂዎች ክርስቶስ መድኀን ተወልዶላችኋል ብሎ አብስሮአቸዋል ሉቃስ 2፣10
-
3. ብዙ መላዕክት ከሰማይ መጥተው
አመስግነዋል ሉቃስ 2፣13-14
-
4. የባቢሎንና የፋርስ ነገስታትም
አንድ ላይ መልዓክ እየመራቸው ወደ ቤተልሔም መጥተው ህፃኑ ኢየሱስን አግኝተው ሰግደው ወርቅ ዕጣን ከርቤ ግብር አቅርበውለታል ማቴዎስ
2፣1-12 መዝሙር 71፣10 ብለው ነገሩንና እኛም ቀጥለን ወደ ቅዱስ ስምኦን እና ወደ እመቤታችን ነበር የሄድነው፡፡
-
አባታችን ቅዱስ ስምኦን እንደሰማነው ከሆነ እና አንተም ከሥራችን ሰዓት ውጭ እንዳጫወትከን ይህ ያሁኑ
ቁመናህ ጥንት ያልነበረና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሆነ ነበር የነገርከን ይህ እንዴት እንደሆነ ብትነግረን?
ስምኦን፡-
ታሪኩ
ብዙ ነው እንደው ጥያቄያችሁን ለመመለስ ያህል በአንድ ወቅት የነቢያትን የትንቢት መጽሐፍ ለመተርጉም ተሰጥቶን ሣለ በመሐል ላይ
አንድ ግራ የሚገባ ከአእምሮ በላይ የሆነ ነገር አጋጠመኝ፡፡
-ይቅርታ አድርግልንና በመሐል ገባንብህ ይህ ከአእምሮ በላይ የሆነ ነገር ያልከውን ግልጽ ብታደርግልን?
ስምኦን፡- …ድንግል በድንግልና ትጸንሣለች.. ብሎ ኢሣይያስ የጻፈውን ነበር፡በእድሜዬ
ድንግል ሴት ወልዳ አይቼም ሰምቼም ስለማላውቅ ግራ ተጋባሁ ድንግል የሚለውንም ብዕሲት /ሴት/ ብዬ ፃፍኩት በዚህን ግዜ እንቅልፍ
ነገር አደረብኝና ተኛሁ ስንቃ ድንግል ተብሎ ተጽፎ አየሁት ለሶስት ግዜ እንደዚህ ካደረኩ በኋላ በሶስተኛው መልአክ ተገልጾ እንዲያውም
ይህንን ነገር ሳታይ አትሞትም አለኝ፡፡ ለረጅም ዘመናት ቆይቼ /በጣም አርጅቼ/ ከአልጋ ላይ እንደ ትኋን ተጣብቄ ከተኛሁበት ሥፍራ
ትንቢቱ ተፍጽሞ ሕፃኑ በቤተልሔም በከብቶች በረት ተወልዶ በስምንተኛው
ቀን ይዘውት ከኔ ዘንድ አመጡት፡፡ (የቅዱስ ስምዖን ፊት በጣም ያበራ ነበር ስለሁኔታዉ ሲያወራን)
§ ከዚያስ ይህ ድንቅ ነገር መፈጸሙን
ስታይ ምን ተሰማህ: ምንስ አልክ?
ስምኦን፡-
ይህንን ድንቅ ነገር ስሰማ ደስታ ነበር የተሰማኝ በተለይ ግን ታቅፌው ሳበቃ
ይንቀጠቀጥ የነበረው እጄ ሲፀና የጐበጠው ወገቤ ሲቃና አንደትኋን
ከአልጋ ተጣብቆ የነበረው ገላዬ ሲዝናና በጣም ነበር ደስታ የተሰማኝ ከዚያም በኋላ “አይኖቼ ማዳንህን አይተዋል በሰላም አሰናብተኝ”ብዬ
ተማፀንኩት፡፡
በመቀጠልም እመቤታችንን አነጋግርናት፡ ማርያም የታሪኩ ባለቤት እንደመሆኗ ብዙ የምናናግራት ነገር ነበር፡
ነገር ግን ለሌላ ጊዜ አቆይተነዋል፡፡ ላሁኑ ግን እንዲህ አልናት!
§ እመቤታች እኛ ሣናውቅ አንቺ አውቀሽ
የማታደርጊልንና የማታስደርጊልን አንዳች ነገር የለም የልቦናችንን
ሃሣብ/ ጥያቄ/ ምንም እንኳን ብታዉቂ ከፊትሽ ከቆምን ዘንድ አባሐርያቆስ እንዳለሽ እኛም የምንለሽ አለን.. ድንግል
ሆይ ርጉም በሆነ በሄሮድስ ዘመን ከእርሱ ጋር ካገር ወደ ሀገር ስተሸሺ ካንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ከዓይኖችሽ በፈሰሰው
እና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪሪ ዕንባ አሳስቢ ድንግል
ሆይ ረሀቡንና ጥሙን ችግሩንና ኃዘኑን ከርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ
ሁሉ አሳስቢ ... ብለናት ነበር፡፡ እርሷም፡-
ማርያም፡- ልጄ ዳግም ለፍርድ ሲገለጽ በክብሩ በመንግሥቱ
ያስባችሁ፡፡
አሜን! ይቆየን!
አሜን! ይቆየን!