እሑድ 14 ኤፕሪል 2013

ሥንት ሰዓት ሆነ?




ይመሻል ይነጋል አንድ ቀንም ሆነ
ብሎ ከሰየመው የቀንን አቆጣጠር
የዘመን መቁጠሪያ ስሌት ሲመነዘር
ፈጣሪ ፍጡሩን ዕድሜ ሊለካለት
ከቀኑ እንዳያልፍ  ልጓም ሲያበጅለት
የኔ እና ያንቺን ፍቅር፣
የኔ እና ያንቺን ትዳር፣
የኔ እና ያንቺን ሰላም፣
የኔ እና ያንቺን ጸጋ፣
ከለካው  ፈጣሪ፣
ስንት ዘመን ሆነ?
ስንት ዘመን አለፈ?
እየኖርን ላለመኖር
እየሞትን ላለመሞት
የተሟገትንበት፣ የተታገልንበት
ከዘመን ልንቀድም የተሯሯጥንበት
ከዘመን የበላይ ለመሆን የተላፋንበት
ኧረ  ለመሆኑ መኖር ከተጀመረ፣
ዘመን ከተቆጠረ፣
ጊዜው ከባከነ፣
ሥንት ሰዓት ሆነ?
                                                                                ደረሰ ረታ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

በትዳር ውስጥ መወያየት ለምን ከባድ ይሆናል?

  በትዳር ውስጥ መወያየት ለምን ከባድ እንደሚሆንባቸው ጥንዶች በርካታ የስነ - ልቦና እና የማህበራዊ ምክንያቶች አሉ። በተለይም አብሮ መኖር በጀመሩበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበረው “ የ...