ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ተስፋዬ ማን /ምንድን/ ነው? ከወደየትስ ነው?
እንደምን አደርክ እንደምን ዋልክ እንዳልልህ ባህሪህን መመራመር አይቻለኝም ስለጤንነቴም እንዳልነግርህ ሁሉን የምታውቅ ቸር አምላክ ነህ እንዳላምንህ ሁሉን ነገር ሳይጠይቁህ በልግስና አውቀህ የምትሰጥ ነህ ስላደረክልኝ ዋጋ እንዳልከፍልህ እንደምድራዊ ነገስታትና መኳንንት እጅ መንሻን የምትሻ አይደለህምና ብቻ የባህርይ ገንዘብህ የሆነውን ምስጋና ብቻ ላቅርብልህ ዘወትር ከኔ ሳትርቅና ሳትለየኝ የረድኤት እጅህ ሳይታጠፍብኝ የምህረት አይንህ ከእኔ ሳይነቀል እንዲሁ የምትናፍቀኝ ከውኃ ጥማት ከእንጀራ ረሃብ ሁሉ የምትብስብኝ መለኪያ መጠን የሌለው ፍቅርህ የሚስበኝ አምላኬ ሆይ አስቀድመህ ሰማይና ምድርን ፣ በምድርም ላይ የሚመላለሱ በእግር የሚሽከረከሩ በልባቸው የሚሳቡ በክንፋቸው የሚበሩ በሰማይና በምድር ለኔ ፈጠርክ፣ እፅዋትንም ሳይቀር ከአዝርዕት ጋር እመገባቸው እገለገልባቸው ዘንድ ለእኔ አዘጋጀህ /አደረግህ/ ከዚያን ባሻገርም ከሁሉ በላይ ራስህን በማዕከለ ምድር በቀራንዮ አደባባይ አይሁድ ምራቃቸውን እየተፉብህ እንደብርሃን የሚያበራ ፊትክን በጥፊ ተፀፋህ ቸርና ለጋስ እጆችህን የወንጀለኞች መቅጫ በነበረው አሁን ግን ትምክህታችን በሆነው መስቀል ቀኝና ግራ እጆችህን ቸነከሩህ ደረትክን በጦር ተወጋህ ደምህን አፍስሰህ ሥጋህን ቆርሰህ ለኔ ተሰዋህ፤
ለእውራን ብርሃን ለአንካሶች መሄጃቸው ጤና ላጡ ጤናቸው ሰላም ላጡ ሰላማቸው የሆንክ ደግ አምላክ ሆይ ለእንደኔ አይነቱ ደካማ ፍጡር ብርታት የሆንክ አምላኬ ሆይ ባህሪህን ካላስቆጣሁና ካላስከፋሁህ አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ እባክህ አምላኬ ሆይ ተስፋዬ ምንድን ነው? ማንስ ነው? ከወደየትስ ነው? ብዬ ጥያቄ ሳቀርብልህ ዘወትር የማይለኝን አፅናኝ መልስህን ከምድር በማንጋጠጥ የምጠይቅህ የዘወትር ጠያቂህ /ለማኝህ/ ምዕመን ነኝ፡፡
ተፃፈ ለልዑል አምላክ
በአንድም በሌላም እንናገራለን:ጆሮ ያለዉ ይስማ:ልብ ያለዉ ልብ ይበል፡፡ የታዘብነዉን የምንናገርበት፣ የምናዉቀዉን ለትምህርት እና ለእርምት የምናዉልበት ከወገንተኝነት ነፃ የሆነ መድረክ ነዉ፤ …ሁሌም ቢሆን አስተያየቶችን እና መልዕክቶችን ለመቀበል ዝግጁ ነን፡፡
ማክሰኞ 2 ኤፕሪል 2013
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
አስተያየቶች ለጥፍ (Atom)
ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!
መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡
-
የእግር ኳስ የኦፍሳይድ (Offside) ደንብ ብዙ ጊዜ ግራ የሚያጋባ ቢሆንም፣ ዋናው ዓላማው ተጫዋቾች በተጋጣሚ የግብ ክልል ውስጥ ብቻቸውን ቆመው ኳስ በመጠበቅ በቀላሉ ጎል እንዳያስቆጥሩ (አድፍጠው እንዳይቀመጡ) ለመከ...
-
“የህዳር ሚካኤል ካለፈ አንድ ወር ሆኖታል ታህሳስ ከገባ ደግሞ 11ኛ ቀኑ ነዉ እንደከዚህ በፊቱ በፌስ ቡክ እናወራለን፣ ምሥጢሬን ሁሉ ነዉ የምነግረዉ አንድም የምደብቀዉ ነገር አልነበረኝም፤ እህቴ እቤት ዉስጥ የጤና ባለ...
-
ዳንኤል ክብረት " ቁስል ተራ " ብሎ የፃፈዉን ካነበብኩ በኋላ በልቤ ሲላወስ የነበረ ሐሳብ ስለነበር ይህንን አጋጣሚ ተጠቅሜ ልተነፍስ ተነሳሁ፤ የርሱን ሐሳብ ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ፡፡ http://...
በትዳር ውስጥ መወያየት ለምን ከባድ ይሆናል?
በትዳር ውስጥ መወያየት ለምን ከባድ እንደሚሆንባቸው ጥንዶች በርካታ የስነ - ልቦና እና የማህበራዊ ምክንያቶች አሉ። በተለይም አብሮ መኖር በጀመሩበት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት የነበረው “ የ...
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ