Believe
That Success Is Your Birth Right
የስኬት
ህጎች
መጀመሪያ
ሊያዉቋቸዉ የሚገባዎትን ጠንቅቀዉ ሳያዉቁ ስኬታማ ለመሆን አስበዉ ያዉቃሉ?
ስለስኬት ህጎች ሳያዉቁ ስኬታማነትን ማሰብ ፡- ስለማሽከርከር ህግ ሳያዉቁ እና የመንገድ ደህንነት ህጎችን ሳይረዱ መኪና እንደማሽከርከር ይቆጠራል፡፡
ሆኖም ስኬት የምርጫ ጉዳይ እንጂ በሌላ ሰዉ የሚጫኑት አይደለም፡፡
የስኬትን
ህግ ካወቁና ከተገበሩ ስኬታማነትን ባይፈልጉ እንኳን የተሳካለት ሰዉ ነዎት፡፡ የተለያዩ የሰዉን ልጅ ለስኬት የሚያበቁ ክንዉኖች
አሉ የእርስዎ ስኬት የትኛዉ እንዲሆን ይፈልጋሉ?
Ø
ሃብት ፡- የገንዘብ
ብዛት ከአስተሳስብ ድኅነት አያድንምና የእርስዎ ሃብት ምን እንዲሆን ይሻሉ?
Ø
ዕዉቀት፡- ወደ ተግባር
የማይለወጥ ዕዉቀት የጋን ዉስጥ መብራት ነዉና የእርስዎ እዉቀት ለርስዎ እና በዙሪያዎ ላለዉ ምንድን አደረገ?
Ø
ጥበብ፡- ጥበብን
መፈለግ እንቁን ከመፈለግ በእጥፍ ይሻላል እርስዎ ጥበብን ለመፈለግ ምን ያህል ዋጋ ይከፍላሉ?
Ø
ትዳር/ቤተሰብ፡-
ቤተሰብ የአገር መሰረት ነዉና ትዳሮትን ምንድን ላይ ነዉ የመሰረቱት አለት ላይ ወይንስ አሸዋ ላይ?
Ø
ስራ፡- ዕለት ተዕለት
ጥሮ ግሮ የሰዉ ልጅ ህይወቱን እንዲመራ የአምላክ ትዕዛዝ ነዉ እርስዎ ስራዎን ሲሰሩ ዉጤታማ ለመሆን ነዉ ስራዎን ለማጠናቀቅ ብቻ
ነዉ የሚሰሩት …
Ø
ወዘተ …
1.
የመፈለግ ህግ
"አንድን ነገር እጅግ ጠንካራ በሆነ ፍላጎት ከፈለጉት እንደሚያገኙት
አይጠራጠሩ ፤"
Ø ጠንካራ ፍላጎት የስኬት መነሻ ሲሆን እንዲሁም ግብን ያሳያል አንድ ሰዉ ጠንካራ ፍላጎት
ካለዉ በልቡ የሞላዉን ፍላጎቱን ለማሳካት ይጥራል፤ ያሳካዋልም፡፡
Ø ጠንካራ ፍላጎት ነገሮችን በድል ለመስራት ትልቅ ሃይል ነዉ፤ (እኤአ 2000 ላይ ኃይሌ
ገብረ ስላሴ በሲዲኒ ኦሎምፒክ ህመሙን ታግሶ አንደኛ በመዉጣት ያሸነፈዉ ፖልቴርጋት ቀሽም ስለሆነ ወይንም ተወዳዳሪ ስላልነበረ ሳይሆን
ኃይሌ የማሸነፍ ጠንካራ ፍላጎት ስለነበረዉ ነዉ፡፡ለኃይሌ
መሸነፍ ወይም ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቅ አማራጭ አልነበረም / አይደለምም) ፤ ለጊዜዉ ስሙን የማላስታዉሰው የጦር ጀነራል የነበረ አንድ ሰዉም የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር ተልዕኮዉን ለመወጣት
ሰራዊቶቹን ይዞ ባህር አቋርጦ በሄደ ጊዜ የተሻገረበትን መርከብ በማቃጠል እና ድልድዩን በመስበር ነበር ጦርነቱን የጀመረዉ ምክንያቱም
ጠላትን ድል ሳያደርግ የሃገርን ዳር ድንበር ሳያስከብር ወደ ኋላ የመመለስ ህልም አልነበረዉምና፤ ጠንካራ ፍላጎቱ ድል እንጂ ወደ
ኋላ መሸሽ/መመለስ አልነበረምና ነዉ፡፡ መርከቡ እና መሸጋገሪያዉ ድልድይ ቢኖር ፈሪዎች ወደ ኋላ መመለስን እንደ አማራጭ ይጠቀሙበት
ነበርና ነዉ፡፡ ስለዚህ እኛም ወደ ኋላ የሚመልሱንን ከስኬት ከተሻለ ለዉጥ ወደ ኋላ የሚያሰቀሩ መንገዶችን ልናቃጥል አዉጥተን ልንጥል
ይገባናል፡፡
Ø ምኞትና ተራ ፍላጎት ስኬትን አያስገኙም፤ ምኞት ማለት የቀረበን እንጀራ