ዓርብ 15 ሜይ 2020

ለምን ትኖራለህ? ወዴት ነህ? ምን ይታይሃል?


ለምን ትኖራለህ
ወዴት ነህ?
ምን ይታይሃል?
          በሳይንሱ ክፍለ ዓለም ስንጓዝ የሰው ልጅ ለመኖር ኑሮን ወይም ሕይወትን ለማሸነፍ በቂም ባይሆን አስፈላጊ የሚሆኑት ምግብ መጠለያ ልብስ ወሳኞች ናቸው ይህንን ለማሟላት ‹‹ጥራህ ግራህ›› ብላ ተብሏልና ይወጣል ይወርዳል ላቡን ያነጠፈጥፋል የሰው የበታችና የበላይ ይሆናል ለመኖር ለብቻውም በሕብረትም ይሁን ብቻ ይለፋል፡፡ ከሳይንሱ ዓለም መለስ ብለን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ስንመለከትና ወደ ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 4÷4 አካባቢ ስናነብ ‹‹ሰው ከእግዚአብሄር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም …›› የሚል እናገኛለን በዚህም መሠረት ቅድም ከተጠቀሰው በተጨማሪ የእግዚአብሔር ቃል /ቃለ ወንጌል/ ያስፈልገናል/ ለመኖር ማለት ነው፤ ግን ለምን እንኖራለን?

ሐሙስ 14 ሜይ 2020

ዘመድኩን በቀለ: ከራየን ወንዝ ማዶ


ዛሬ ለየት ባለ መልኩ የምንመለከተዉ በልዩ አፃፃፉ እና በብዙ ተከታዮቹ የሚታወቀዉ ስለ ዘመድኩት በቀለ (ዲያቆን/መምህር) ሲሆን እንደሚታወቀዉ በተደጋጋሚ ፌስቡኩን እንደሚዘጋ የሚታወቅ ሲሆን ወደፊትም እንደሚዘጋበትና አገልግሎቱን እንደሚያቋርጥበት ይታወቃል ስለዚህ ሌላ መፍትሔ ማምጣት ግድ ሆኗል፡፡
ራሱ ዘመድኩን እንዲህ ያቀርበዋልና ስሙት፤ ተከተሉት፡፡
         ወደፊት ልንሠራቸው ያቀድናቸውን ዕቅዶች በሙሉ አስፍሬያለሁና ጦማሯን አንብቧት። ለሌሎችም #SHARE በማድረግ አጋሯት።
#ETHIOPIA | ~ እንዴት ናችሁልኝሳ ? ሀገሩ፣ መንደሩ፣ ሰፈሩ፣ ቀዬው ሰላም ነው? እኔማ አምላክ ክብር ይግባው ደህና ነኝ።
ይኸው ፌስቡክ ድራሽ አባቴን ቢያጠፋኝም እኔ ዘመዴ፣ የድንግል አሽከር የማይሰበረውን የኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንደያዝነ፣ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ውበት አጊጠን፣ እንደ መስከረም ወር ጠሐይ ፈክተን፣ በገነት መካከል እንደ ቆመ የወይራ ዛፍ ለምልመን፣ እንደ ኃያሉ አንበሳ እያገሳን፣ እንደ ነብር፣ እንደ አቦ ሸማኔ እየፈጠንነ፣ እንደ ንስር ታድሰን እነሆ በአዲስ ጉልበት፣ በአዲስ ወኔ፣ አለን ነበረን እንል ከነበረው አቅም ላይ እጥፍ ጨምረን፣ እንደ አልማዝ እንደ ዕንቁ እያንጸባረቅን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የፌስቡክን ኳራኒትን ፈጽመን ይኸው ዳግም ተከስተናል። 
እንደተለመደው እንደ አማኝነታችን ስለ ቅድስት የኢትየጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን፣ የኢትዮጵያ ዜጋ በመሆናችን ደግሞ ስለ ውቢቷ ሃገራችን መወያየታችንንና መመካከራችንን፣ መሟገት፣ መፋጨታችንንንም አጠንክረን እንቀጥላለን። መፋታት፣ ማፈግፈግ፣ መሸሽ፣ ማምለጥና፣ ማስቀየስም የለም። ሰምና ወርቅ ፈልግ የሚል ጦማር እኔ ጋር አይሠራም። እንደ ሐረር፣ እንደ ሲዳሞ ግሩም ጣዕም ያለው ቡና አስሬ ተለክቶ እንደተለቀመ፣ ታጥቦ ተቀሽሮ፣ ተቆልቶ፣ ተወቅጦ ተፈልቶ እንደወረደ ቡና ጦማሬን ትጠጡት፣ ፉትም ትሉት ዘንድ ከሃገረ ጀርመን፣ ከራየን ወንዝ ማዶ ለእናንተ መቅረቡን ይቀጥላል።

ዓርብ 10 ኤፕሪል 2020

join us


እጅግ የማከብራችሁ እና የምወዳችሁ በመላዉ አለም የምትገኙ ታዳሚዎቼ እንደ አስፈላጊነቱ እንደዘመኑ መዘመን ግድ ይላልና ከዚህ በኋላ የሚለቀቁ አዳዲስ መረጃዎቼን በእጅ ስልክዎ ላይ በቀጥታ እንዲደርስዎ በአዲስ ቻናል መምጣት ግድ ስለሆነ አዲስ የቴሌግራም ቻናል ስለከፈትኩ እርስዎም ባሉበት መረጃ ይደርስዎት ዘንድ ቤተሰብ ይሁኑ፡፡

ማክሰኞ 7 ኤፕሪል 2020

ስኬታማ ተቋም ለመፍጠር Part Three


1. ሰው መምረጥ


*በብቃቱ፣ በክህሎቱ፣ በተሠጥኦው፣ በትምህርት ዝግጅቱ፣ ወዘተ ከአላማችን ጋር የሚቀራረብ ግባችን ለማሳካት የሚያስችል ሰው መምረጥ አስፈላጊ ነው።
ተቋማት የሥራ እድልን ከመፍጠር ጎን ለጎን ተቋምን ሊያሳድጉ ስኬትን ሊያስመዘግቡ የሚችሉ እና የአገርን ሥም በአለም መድረክ ጭምር ሊያስጠሩ የሚችሉ ሠራተኞችን ከጅምሩ ከላይ በተዘረዘሩት መሥፈርቶች መመልመል ይኖርባቸዋል።

ይህ ሠው ታድያ ግላዊ ጉዳዩን ወደ ጎን ያደረገ የአገር ፍቅር ለወገን ክብር ያለውና ሥራውን እሴት ጨምሮ የሚሰራ ተደርጎ መሠራት አለበት።

የማይረካ፣ የመማር፣ የመሥራት፣ ሁሌም ጀማሪ የሆነ፣ ሁሌም ለአዲስ ነገር ጉጉ የሆነ፣ ዘወትር ለውጥን አሻግሮ የሚያይ፣ ሁሌም ለሥራ የሚሮጥ፣ ጥማት ያለበት ሰው መምረጥ ይኖርብናል።

ሰዉ በመምረጥ ሂደት ዉስጥ መዘንጋት የሌለብን ነገር ምናልባት ከቦታዉ ጋር የሚሄድ ካልሆነ በቀር አለበለዚያም የትምህርት ዝግጅቱ ከመለያየቱ በቀር ‹‹የማይረባ›› የሚባል ሰዉ እንደሌለ ልብ ልንል ይገባል፡፡

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

የቀኝ ዐይን - ድንግል ማርያም

  የቀኝ ዐይን - ድንግል ማርያም   ( በዲ / ን ብርሃኑ አድማስ ) አፍጣኒተ ረድኤት ማርያም በጊዜ   ምንዳቤ ወአጸባ ለዐይን እምቀራንባ፤ አንቲ ውእቱ ረዳኢተ ያዕቆብ በቤተ ላባ፤ በኩ...