ሐሙስ 25 ኤፕሪል 2013

ተስፋዬ ማን ነው?


ልዑል እግዚአብሔር ሆይ ተስፋዬ ማን /ምንድን/ ነው? ከወደየትስ ነው?
       እንደምን አደርክ እንደምን ዋልክ እንዳልልህ ባህሪህን መመራመር አይቻለኝም ስለጤንነቴም እንዳልነግርህ ሁሉን የምታውቅ ቸር አምላክ ነህ፤ እንዳለምንህ ሁሉን ነገር ሳይጠይቁህ በልግስና አውቀህ የምትሰጥ ነህ፡፡ ስላደረክልኝ ዋጋ እንዳልከፍልህ እንደምድራዊ ነገስታትና መኳንንት እጅ መንሻን የምትሻ አይደለህምና፣ ብቻ የባህርይ ገንዘብህ የሆነውን ምስጋና ላቅርብልህ፤ ዘወትር ከኔ ሳትርቅና ሳትለየኝ የረድኤት እጅህ ሳይታጠፍብኝ የምህረት ዓይንህ ከእኔ ሳይነቀል እንዲሁ የምትናፍቀኝ ከውኃ ጥማት ከእንጀራ ረሃብ ሁሉ የምትብስብኝ መለኪያ መጠን የሌለው ፍቅርህ የሚስበኝ አምላኬ ሆይ አስቀድመህ ሰማይና ምድርን በምድርም ላይ የሚመላለሱትን በእግር የሚሽከረከሩ፣ በልባቸው የሚሳቡ፣ በክንፋቸው የሚበሩ፣ በሰማይና በምድር ለኔ ፈጠርክ፤ እፅዋትንም ሳይቀር ከአዝርዕት ጋር እመገባቸው እገለገልባቸው ዘንድ ለእኔ አዘጋጀህ /አደረግህ/፡፡ ከዚያም ባሻገር ከሁሉ በላይ ራስህን በማዕከለ ምድር በቀራንዮ አደባባይ አይሁድ ምራቃቸውን እየተፉብህ እንደብርሃን የሚያበራ ፊትክን በጥፊ ተፀፋህ ቸርና ለጋስ እጆችህን የወንጀለኞች መቅጫ በነበረው (አሁን ግን ትምክህታችን በሆነው) መስቀል ቀኝና ግራ እጆችህን ቸነከሩህ ደረትክን በጦር ተወጋህ ደምህን አፍስሰህ ሥጋህን ቆርሰህ ለኔ ተሰዋህ፤
       ለእውራን ብርሃን ለአንካሶች መሄጃቸው ጤና ላጡ ጤናቸው ሰላም ላጡ ሰላማቸው የሆንክ ደግ አምላክ ሆይ ለእንደኔ አይነቱ ደካማ ፍጡር ብርታት የሆንክ አምላኬ ሆይ ባህሪህን ካላስቆጣሁና ካላስከፋሁህ አንድ ነገር እጠይቅሃለሁ፤ እባክህ አምላኬ ሆይ ተስፋዬ ምንድን ነው? ማንስ ነው? ከወደየትስ ነው? ብዬ ጥያቄ ሳቀርብልህ ዘወትር የማይለኝን አፅናኝ መልስህን ከምድር በማንጋጠጥ የምጠይቅህ የዘወትር ጠያቂህ /ለማኝህ/ ምዕመን ነኝ፡፡
ተፃፈ ለልዑል አምላክ

በቅርብ ለማውቅህ ወንድሜ‹‹ … የቀድሞ ፍቅርህን ትተሃል›› ክፍል - 2


ጊዜው ከባለፈው ምንም ለውጥ የለው ሁለመናው ተመሳሳይነትና አንድነት አለው ግን እኔና አንተ ተለውጠናል ነቀፌታ በዝቶብናል በሥጋ ሥራ ወጥመድ ተጠምደን በውዳሴ ከንቱ ተጠልፈን በትዕቢት ወድቀናል የትላንት ማንነታችንን ዘንግተን ዛሬን ጠፍተናል ለሁሉ ነገር የነበረንን የቀድሞ ፍቅራችንን ትተናል፤
ወንድማለም በደንብ በቅርብ አውቅሃለሁ ታውቀኛለህ የቀድሞ ፍቅርህን ትተሃል ባለፈው በክፍል አንድ እንደፃፍኩልህ

የአጋጣሚ ነገር ….


ዛሬ ሰኞ መጋቢት 9/2005 ዓ.ም. ነዉ፤ ሰኔና ሰኞን አለመሆን እንዳለ ሆኖ ለሰራተኛና ለተማሪ ደሞ የባሰዉን ነዉ፡፡
የትራንስፖርት ችግር ደግሞ ሰኞ አያዉቅ ማክሰኞ የለ ሁሌ ችግር ነዉ ለነገሩ ለእናንተ መንገር ለቀባሪዉ አረዱት ይሆንብኛል፡፡
አሁን ስለትረንስፖርት ችግር ላወራ አይደለም፤እንዲያዉም እናቴ በአፍ ይሄዳል ትል ነበርና  … … መተዉ ሳይሻል አይቀርም፡፡
……….. ነገሩ እንዲህ ነዉ፡- በጠዋት ተነስቼ ወደ ሥራ ገበታዬ እያመራሁ ነበር ፤ መኪናዉ ጉዞዉን ጀምሯል እንሄዳለን፣ እንሄዳለን … መንገዱ አያልቅም ወይ አያስኬድም፡፡
አንዳንድ  ሰዎች የትራንስፖርት መዘጋጋቱን ምክንያት(ተገን) በማድረግ ትዉዉቅ ይጀምራሉ (በአራዳ ቋንቋ ይጀናጀናሉ!) ፡-
በተለይ የከተማ አዉቶቡስ ላይ፤

ማክሰኞ 23 ኤፕሪል 2013

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: አማርኛ ከሠላሳ ዓመት በኋላ

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: አማርኛ ከሠላሳ ዓመት በኋላ:   click here for pdf የዛሬ ሠላሳ ዓመት በ2035 ዓም በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች መካከል የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ውድድር ይደረጋል፡፡ በውድድሩም ከዚህ በታች የማቀርብላችሁ ወግ ‹እኔና ትምህር...

ቅዳሜ 20 ኤፕሪል 2013

‘’ለመጪው ትውልድ ልማትን እንጂ ልመናን አናወርስም’’

‘’ለመጪው ትውልድ ልማትን እንጂ ልመናን
አናወርስም’’

ጐበዝ ለካ ታክሲ መያዝም ይከብዳል!(ተራ አስከባሪዎች ባይኖሩና በሰልፍ ባያደርጉት እንጃ ወደየቤታችን መግባታችንን(አደራችሁን ዘይት፣ዳቦ፣ስዃር፣ መብራት፣ ዉሃ እና ኔትዎርክ በሰልፍ ይሁን እንዳትሉ ) ) እውነቴን ነው የምላችሁ እስከዛሬ በነበረኝ “ጥልቅ” ግንዛቤ የገንዘብ እንጂ “የዕውቀት” ችግር ያለ አይመስለኝም ነበር፤ (ብዙ ዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ ስለተከፈተ አለማወቅ አገር ለቆ ጠፋ ብዬ ነበርና የማምነው) በመሐላ ማረጋገጥ ካለብኝ እምላለሁ፤ ደሞ ለመሐላ መርካቶ በጠቅላላ መሐላ በመሐላ አይደል እንዴ ምን ችግር አለው ሳልምል እመኑኝ፤ በታክሲ ከመሔድ በእግር መሔድ በስንት እጥፍ ይበልጣል መሰላችሁ ሲመሽማ ‘’ወክ’’ በማድረግ ዘግዘቅ ማለት ነው ወደ ሰፈር፡፡

ያኔ አዲስ ዓመት መስከረም ሳይጠባ የነበረብኝን አባዜ ጦሴን ጥንቡሳሴን ብዬ በጳጉሜ ፀበል እና ህክምና ከላዬ ልይ ጥዬ አዲሱን አመት በአዲስ ጤና ለመቀበል ወደ ሆስፒታል አመራሁ የጳጉሜ 3 ፀበል ጥሩ( ለዚያዉም የጳጉሜ 3 የሩፋኤል ዕለት ከሁሉም ይበልጣል እጣ መጣል አያስፈልገውም) ሰፈር እስከ ማወክ ቤቶች እስከ መገለባበጥ በደረሰ ዝናብ ተፀበልኩ ጐበዝ!! አትሉኝም? (ለነገሩ ወረኛ ብትሉኝ ይሻላል ወሬ ከጀመርኩ አንዱን ሳልጨርስ ወደ ሌላ እሱን ትቼ ደግሞ ወደ ሌላ እሄዳለሁና) ሐኪሜ MRI ታየው ብሎኝ ለወገቤ ህመም ‘’ቤቴል ሆስፒታል’’ ላከኝ (አላውቅም ማለት ነውር አይደል?! ቦታው የት ነው? እንኳን ሳልል ተፈትልኬ ወጣሁ) ለነገሩ ምን ላድርግ ብላችሁ ነው ሄጄ እንድታከም ሲልከኝ ማስተባበያ ቃላት ጣል አደረገልኝ ይቅርታ ማከም አቅቶኝ አይደለም እዚያ የምልክህ የተሟላ ነገር እንኳን የለንም ለዚያ ነው ታየኛለህ አይደል ‘’ጓንት’’ እንኳን ሳይኖረኝ በእጄ ሥጠቀም ለዚህ ነው ይቅርታ አለኝ፡፡

ዓርብ 19 ኤፕሪል 2013

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: የዓመቱ ‹በጎ ሰው›

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: የዓመቱ ‹በጎ ሰው›: click here for pdf   የዳንኤል ዕይታዎች ‹የዓመቱ በጎ ሰው› የምርጫ ኮሚቴ ሰባት አባላት ነበሩት፡፡ እነዚህ አባላት ከተለያዩ ሞያዎችና አካባቢዎች የመጡ ሲሆን በ‹የዳንኤል ዕይታዎች› አማካኝነት ...

እሑድ 14 ኤፕሪል 2013

ሥንት ሰዓት ሆነ?




ይመሻል ይነጋል አንድ ቀንም ሆነ
ብሎ ከሰየመው የቀንን አቆጣጠር
የዘመን መቁጠሪያ ስሌት ሲመነዘር
ፈጣሪ ፍጡሩን ዕድሜ ሊለካለት
ከቀኑ እንዳያልፍ  ልጓም ሲያበጅለት
የኔ እና ያንቺን ፍቅር፣
የኔ እና ያንቺን ትዳር፣
የኔ እና ያንቺን ሰላም፣
የኔ እና ያንቺን ጸጋ፣
ከለካው  ፈጣሪ፣
ስንት ዘመን ሆነ?
ስንት ዘመን አለፈ?
እየኖርን ላለመኖር
እየሞትን ላለመሞት
የተሟገትንበት፣ የተታገልንበት
ከዘመን ልንቀድም የተሯሯጥንበት
ከዘመን የበላይ ለመሆን የተላፋንበት
ኧረ  ለመሆኑ መኖር ከተጀመረ፣
ዘመን ከተቆጠረ፣
ጊዜው ከባከነ፣
ሥንት ሰዓት ሆነ?
                                                                                ደረሰ ረታ

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...