2ኛ.መስቀል ከቀራንዮ በኋላ
ብዙ ሰዎች መስቀልን የማክበራችን ምሥጢር ማወቁ ይሳናቸዋል፣ይከብዳቸዋል ፣ይፀናባቸዋል፡፡ እኛ ግን መስቀልን የምናከብረዉ ስላከበረን ነዉ፡፡ክብር ምስጋና ይግባዉና አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ መስቀልን ታግሶ በደሙ ክሶ፣ በቀራንዮ ዉሎ ዓለምን ከቀደሰልን በኋላ፣ መስቀል የርግማን፣ የኋፍረትና የኋጢያት ምልክት መሆኑ ቀርቶ
መስቀል መርገመ ኦሪት የተሸረበት፣ ሰላምና ነጻነት የታወጀበት፣የኛ ድህነት ፣ የበረከትና የነፃነት አርማ፣ የወለወደ እግዚአብሔር ክርስቶስ የሰለም ዙፋን ሆኖ ዓመተ ፍዳ እና ዓመተ ኩነኔ ተሸሮ ዓመተ ምህረት የታወጀበት የነፃነት ዋስትናችን ነዉ፡፡ ለዚህም ቅዱስ ጳዉሎስ፡- «ወለነሰ ተሣየጠነ ክርስቶስ እመርገመ ለኦሪት በዘወጽአ በእንቲአነ ወጾረ መርገማ፣እኛንስ ክርስቶስ በኦሪት መርገም ዋጅቶናል፡፡ ስለኛ ሕግን በመፈጸሙና የኦሪትን መርገም በመሸከሙ፡፡» ብሏል፡፡ ገላትያ 3፡13
በነብዩ « ዉእቱ ነስኣ ደዌነ ወፆረ ሕማማነ በእንቲአነ ሓመ፣ወንሕነኒ ርኢናሁ ሕሙመ ወዉእቱሰ ቈሰለ በእንተ ኋጢአትነ ወሐመ በእንተ ጌጋይነ ፤ ትእምርተ ሰላምነ፤ ወበቁስለ ዚአሁ ሐየወነ ቁኢስለነ፡፡»
እሱ ደዌያችንን ገንዘብ አደረገ፣ ሕማማችንንም ተሸከመ ስለ እኛም ታመመ እኛ ታሞ በመከራም ተጨንቆ አየነዉ፡፡ እሱ ግን ስለ ኋጢያታችን ቈሰለ ስለበዳላችንም ታመመ፣የፍቅር የአንድነታችንም (የሰላማችንም) ምልክት እሱ ነዉ፡፡ በእሱ ቁስልም ከቁስላችን ዳንን … …፡፡ ተብሎ ተጽፎ ነበርና ትንቢት እንዲሁም ኦሪታዊ መርገመ መስቀል እንዲያከትም አምላክ ወልደ አምላክ ደዌያችንን ተሸክሞ በቀራንዮ ዋለልን፡፡ት.ኢሳይያስ53፡4-5 ዮሓንስ 19፡1-42
ቅዱስ ጳዉሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈዉ መልዕክቱ ምዕራፍ 8፡3 ላይ «ወኮነና ለይእቲ ኋጢያት በነፍሰቱ ኋጢአትን በሰዉነቱ ቀጣት፡፡»ያለዉን እንደነ ቅዱስ አትናትዎስ የመሰሉ አበዉ ሊቃዉንት ደግሞ
«ወአስተሐፈረ ኋጢአት በዲበ ምድር፤ ወአበ ጠለ ሞተ በዉስተ ሲኦል ወሰዐረ መርገመ በዲበ ዕፀ መስቀል ወነሰተ ሙስና በዉስተ መቃብር፡፡ወዘኢየሐምም ሐመ በሥጋ ሐማሚ ተዋህዶ ቃል ምስለ ሥጋ ወገብረ ዘንተ ከመይፁር ሕማመ ዚአነ ወያእትቶ እምኔነ ወየሀበነ ዘዚአሁ ሕይወተ፤ ወአዕረገ ርእሶ መሥዋዕተ በእንቲአነ»
በምድር ላይ ኋጢአትን አሰፈረ፤ በሲኦልም ሞትን አጠፋ፤በመስቀል ላይ መርገምን ሻረ፤ በመቃብር ዉስጥም ሙስና መቃብርን አጠፋ፡፡ የማይታመመዉ በሚታመምዉ ሥጋ ታመመ ቃል ከሐማሚ ሥጋ ጋር ተዋሐዶ ሕማምን ከሥጋ ያርቅ ዘንድ፣ ከእኛም ያርቀዉ ዘንድ የርሱንም ሕያወት ይሰጠን ዘንድ ይህን አደረገ፡፡ስለኛም ራሱን መሥዋእት አድርጎ አቀረበ በማለት ይገልጹታል፡፡
ሃይማኖተ አበዉ ዘቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ 30፡40 ንፁሐ ባህርይ ክርስቶስ ከሥራዉ ስህተት ከአንደበቱ ሐሰት ሳይገኝበት፣ በኋጢአተኞች ዘንድ፣ ኋጥእ በደለኛ ተብሎ መስቀል ላይ ዋለ መባሉ እዉነት ነዉ፡፡ሆኖም ክርስቶስ መስቀል ላይ የዋለበት አንድ ዐብይ ምክንያት እንዳለ ግን መዘንጋት የለበትም፡፡ይኸዉም ዕዳ በደላችንን ደዌ ኋጢአታችንን ተሸክሞ በደሙ ካሣ መርገማችንን ሽሮ ከኋጢአት ባርነት ነፃ ያወጣን ዘንድ መሆኑን ነዉ፡፡ ስለዚህም፤