ሰኞ 2 ማርች 2020

ስኬታማ ተቋም ለመፍጠር Part one


ስኬታማ ተቋም

ተቋም ፡- ማለት የብዙ ግብአት ዉህደት ሲሆን አንድን ተቋም ስኬታማ ለማድረግ አለበለዚያም በመቋቋም ላይ ያለን ተቋም ከግንባታዉ ጀምሮ ስኬታማ ለማድረግ ከታሰበ እያንዳንዱ ግብአቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በእኩል በልዩ አትኩሮት መገንባት ግድ ይላል፡፡


ለዛሬዉ አንድን ተቋም ስኬታማ አድርጎ ከጅምሩ ለመፍጠር ጠቃሚ ከሆኑት ዉስጥ ጥቂቱን እንመለከታለን፡፡
1)    የሥራ አከባቢን ምቹ ማድረግ፡- በተለያዩ ቁሳቁስ ማሟላት/ ማደራጀት፤
2)    ሰዉ መፍጠር፡- ሰዋዊ ባህሪ ያለዉና ሰዉ ሰዉ የሚሸት ማንነት የተላበሰ ሰራተኛ በእዉቀት፣ በክህሎት እና በቀና አመለካከት የዳበረ መገንባት፤
3)    የሚተገበር ራእይ ማዘጋጀት፡- ራእይ የሌለዉ ተቋም በዉሃ ላይ እንደሚንሳፈፍ ኩበት አለበለዚያም ወንዝ ዳር እንደበቀለ ሸንበቆ ነፋስ ወደ ነፈሰበት የሚሄድ መሆን ነዉ፤
4)    የሚያሰራ መዋቅር መዘርጋት/መፍጠር፡- ወጥነት ያለዉ፣ መነሻና መድረሻ ያለዉ መዋቅር ወሳኝ ነዉ፤
5)    መፈተሸ፡- ከላይ የተጠቀስናቸዉ ነገሮች ወደምንፈልገዉ ግብ(ስኬታማነት) ያደርሱናል አያደርሱንም? እስከ ዛሬ በመጣነዉ ለምንፈልገዉ ግብ እየቀረብን ነዉ? ወይንስ ገና በብዙ ርቀት ላይ ነን?
6)    እርምት መዉሰድ፡- ጉዞአችን ወደ ግባችን የማያደርሰን ከሆነ ፈትሾ ማስተካከያ መስራት ግድ ነዉ፤ ሁሌም በአንድ መንገድ / አካሄድ መጓዝ አግባብ ስላልሆነ፡፡



ስኬት ምንድን ነዉ?
 


ስኬት ማለት የአንድ ዓላማ አፈፃፀም ማለት ነዉ፡፡አንድ አላማ አፈፃፀም በስኬትም በዉድቀትም ሊጠናቀቅ ይችላል፤ ለዛሬ የምንዳስሰዉ ስለ ስኬት ስለሆነ እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚቻል እና ስለ ስኬት እንዳስሳለን፡፡
ፀሐፍት የስኬትን ምሥጢራት እንዲህ አስቀምጠዉልናል፡-
                              I.        ተነሳሽነቱን መዉሰድ/ስኬታማ ለመሆን ሃላፊነቱን ለራስ መዉሰድ
                             II.        የመጨረሻዉን/መድረሻችንን በአእምሮአችን ይዘን /አስቀምጠን መጀመር
                           III.        ቀዳሚ ነገሮችን ማስቀደም (ቅድመ ሁኔታዎችን ማሟላት)
                           IV.        ሁለቱም ወገን አሸናፊ ስለሚሆንበት ማሰብ
                            V.        ቅድሚያ ሌሎች እርስዎን እንዲረዳዎት ሳይሆን እነርሱን ለመረዳት ጊዜ ይስጡ
                           VI.        ቅንጅትን /አብሮነትን መፍጠር/ከአንድ ሁለት ይሻላልና/
                          VII.        መጋዙን መሳል/ ዘወትር ለመቁረጥ ስለት ያለዉ ለመሆን መዘጋጀት

እንግዲህ እነዚህ ምሥጢራት በአግባቡ ከተገበርን ስኬት የምርጫ ጉዳይ ነዉ፡፡
ስኬት አጥብቆ የመፈለግ እንጂ የምኞት  ዉጤት አይደለምና አጥብቀዉ ይፈልጉ፤ ጠንክረዉ ይስሩ፡፡
ስኬት የህልምም ዉጤት ስለሆነ ህልምዎ እንዳይደናቀፍ ህልምዎን አጋርዎ ካልሆነ ሰዉ ዘንድ ያርቁት፡፡ ( ህልምና ፅንስ መሬት እስኪይዝ ድረስ ሊጨናገፍ ይችላልና፡፡ እንደዉም እናቶች ሲያረግዙ ፅንሱ ሶስት ወር እስኪሞላዉ ለማንም አይናገሩም)
̎ ስኬት የቀና አመለካከት ፅንስ የጠንካራ ተግባር ልጅ ነዉ፡፡ ̎   

                                                     1.    ሥራ አከባቢን ምቹ ማድረግ

የሥራ አከባቢ ሥንል ሥራን ለማከናወን ብቻ መሆን የለበትም ምክንያቱም በየዕለት ተዕለት ህይወታችን ዉስጥ ከ37% በላይ ጊዜያችንን የምንኖረዉ የመኖሪያ ሥፍራችን መስሪያ ቤታችን አከባቢ ነዉና፡፡ ስለዚህ የመስርያ ከባቢያችን ለመኖር ምቹ መሆን ይኖርበታል፡፡

ምቹ፡- ፅዱ፣ አረንጓዴ፣ ማራኪ፣ ሰላማዊ፣ ከክፋት፣ ከተንኮል፣ ከቂም፣ ከጥላቻ፣ ከአላስፈላጊ አለመግባባት፣ ወዘተ በአንፃራዊነት የፀዳ መሆን ይጠበቅበታል፡፡
1.1.   ለሠራተኛ ምቹ፡- ለመስራት የሚጋብዝ
መሰረተ ልማት የተሟላለት፡- ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ኮምፒዉተር፣ ኔትወርክ፣ የጽህፈት መሳሪያ ቁሳቁስ፣ ወዘተ
 የመስርያ ቁሳቁስ፡- በስምና በቁጥር ኮምፒዉተር፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ … አንድ፣ ሁለት፣ ብለን የምንጠራቸዉ ሳይሆን በትክክል የሚሰሩ፣ የሚያገለግሉ፣ ተገልጋይን የማያጉላሉ፣ አገልጋይን ላሰበዉ ስኬት መንገድ ጠራጊ የሚሆን እንጂ እንቅፋት የሚሆኑ መሆን የለባቸዉም፡፡
እንደዚህ ዓይነት ቁሳቁስ ከመኖራቸዉ ይልቅ አለመኖራቸዉ ይጠቅማልና፤ ምክንያቱም ባለሙያዉ አለመኖራቸዉን አዉቆ ይሟላልኛል ብሎ በሥራ ተነሳሽነት እና በትልቅ ተስፋ ይጠብቃልና፡፡ አንድም በተቋማት ዉስጥ ትልቅ ትኩረት የሚያገኘዉ አንድን ያረጀ ነገር ከመቀየር የሌለን ነገር ማሟላት ስለሚቀላቸዉ፡፡ የለዉም ከሚለዉ ይልቅ ይቀየር ለሚለዉ ጆሮ ስለማይሰጡ፡፡
1.2.   ለሥራዉ ደህንነት፡- ምሥጢሩ ተጠብቆ ተኣማኒነት ተረጋግጦ መስራት አለበት፤
ደህንነቱ የተጠበቀ፡- ፋይል ማስቀመጫ፣ ለአደጋ ተጋላጭ ያልሆነ አከባቢ፣ ለዝርፍያ ተጋላጭ እና ሰነዶች ለመሰወር፣ ለመሰረዝ፣ ለመደለዝ፣ ተጋላጭ የማይሆን ሥፍራ ወዘተ

2.    ሰዉ መፍጠር

ሰዉ ማለት ሰባቱ ባሕርያት የተሟሉለት ቆሞ የሚሄድ ፣ ሮጦ የሚያመልጥ፣ አባሮ የሚይዝ፣ ወጥቶ የሚገባ፣ ሰርቶ የሚበላ፣ ወዘተ የሚለዉ እንዳለ ሆኖ ከዚህ ባሻገር ጭንቅላቱን ፣ አስተሳሰቡን፣ እዉቀቱን፣ ጉልበቱን፣ ሃብቱን፣ ወዘተ ተጠቅሞ ዓለምን መለወጥ የሚችል ፍጡር ነዉ፡፡



ይቀጥላል ...
for more information join my telegram channel
https://t.me/deressereta
 





እሑድ 19 ጃንዋሪ 2020

"ዳንኤልን" እንኳን ሰው ሠይጣንም ይፈራዋል (ክፍል 3)


በክፍል ሁለት ትዝታችን ነቢዩ ዳንኤልን የሥራ ባልደረቦቹ የሆኑ ሹማምንት በስልጣን ጥማት እና በሹመት ቅናት ከንጉሡ ጋር መክረዉ ህግ አዉጥተዉ ለርሱ ለመገዛት ወስነዉ ነገር ሸረቡ ዳንኤልም እንደጠበቁት ከወጥመዳቸዉ ገባላቸዉ፤ እዉን ንጉሥ ዳርዮስ እና ንግስተቱ ዳንኤልን እንደተባለዉ ወደ አንበሶች ጉድጓድ ይከቱት ይሆን? አናብስቱስ ይበሉት ይሆንን?
‘’ ንጉሡም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ በጣም አዘነ ያድነዉም ዘንድ ልቡን ወደ ዳንኤል አደረገ፤ ሊያድነዉም ፀሐይ እስኪገባ ድረስ ደከመ፡፡ ‘’ ዳንኤል 6÷14
ዳርዮስ ያስብ እንጂ አልተሳካለትም፤ አጣብቂኝ ዉስጥ አስገብተዉታልና፡፡
ዳንኤል ወደ አንበሶች ጉድጓድ ተጣለ፡፡
በስተመጨረሻ ንጉሡም ዳንኤልን  የሚያመልከዉ አምላኩ እንደሚያድነዉ ያምናልና
‘’ሁል ጊዜ የምታመልከዉ አምላክህ እርሱ ያድንህ አለዉ’’
ሹማምንቱም ጉድጓዱን እንዳይከፈት የሚቻላቸዉን ሁሉ አደረጉ፤ ንጉሡም እያዘነ ወደ ቤቱ ሄደ እራትም ሳይበላ እንቅልፍም በአይኑ ሳይዞር አደረ፡፡

እሑድ 12 ጃንዋሪ 2020

ዳንኤልን እንኳን ሰዉ ሰይጣንም ይፈራዋል፤(special)


ነብዩ ዳንኤል ላይ ሹማምንቱ ለምን አሴሩበት?
ሹማምንቱ ንጉሡን ወጥመድ ዉስጥ ማስገባት ለምን ፈለጉ?
ዳንኤል ለምን ከነሱ የተለየ አቋም ኖረዉ?
የዳንኤል ከሹማምንቱ የተለየ አላማዉ ምንድን ነዉ?
ነብዩ ዳንኤል እዉን በሹማምንቱ ወጥመድ ይወድቅ ይሆን?
ንጉሡሥ በነብዩ ዳንኤል ላይ ዉሳኔዉ ምን ይሆን?
ዳንኤል መጨረሻዉ ምንድን ነዉ?
ዳንኤል ያቺ ሰላሳ ቀን እስክታልፍ ድረስ የልቡን እግዚአብሔር ስለሚያዉቀዉ እነሱ ያሉትን ለምን አይፈፅምም?
ዳንኤል ሹማምንቱ እንዳሉት በእጃቸዉ ቢወድቅ ሕጉ ቢፀናበት እንዴት ያልፈዋል?
እነዚህንና ሌሎችን ጥያቄዎች ቀጣይ ክፍል ይመልሰዋልና ይጠብቁን፡፡

ሐሙስ 2 ጃንዋሪ 2020

ዳንኤልን እንኳን ሰዉ ሰይጣንም ይፈራዋል፤ (ክፍል ሁለት)


መፅሐፍ ስለምርኮ በሚናገረዉ በዘመኑ ስለተደረጉት ዋና ዋና ድርጊቶች ሲተርክ በባቢሎን በስደት መኖርን ሲያነሳ ታላላቅ ሰዎች ብሎ ካነሳቸዉ መካከል ሕዝቅኤልና ዳንኤል ተጠቃሾች ናቸዉ፡፡

ብልጣሶር፡- ትርጉሙ ቤል (የባቢሎን ጣኦት) ንጉሥን ይጠብቀዉ ማለት ነዉ፤ ትንቢተ ኢሳይያስ 46÷1
1)    የናቡከደነፆር የልጅ ልጅ የናቡናዲስ ልጅ፡፡ የአዲሲቱ ባቢሎን መንግሥት የመጨረሻ ንጉሥ፡፡
በመጠጥ ግብዣ ጊዜ በቤቱ ግንብ ላይ ፅሕፈት የምትፅፍ እጅ ታያቸዉ ፅሕፈቱም ፡- ̎ማኔ ቴቄል ፋሬስ̎ የሚልነበረ፡፡
ንጉሡም ደንግጦ ትርጉሙን ሲፈልግ ዳንኤል እንዲህ ብሎ ተረጎመለት፡፡
̎ እግዚአብሔር መንግሥትህን ቆጠረዉ፣ ፈፀመዉ፣ በሚዛን ተመዝነህ ቀለህ ተገኘህ፤ መንግሥትህም ተከፈለ ለሜዶንና ለፋርስ ሰዎችም ተሰጠ፡፡̎ ዳንኤል 5÷25-28
በዚያ ሌሊት የባቢሎን መንግሥት በፋርስ እጅ ወደቀ፡፡ ይህም የሆነዉ በ539 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነዉ፡፡ ዳንኤል 5÷1-30፣ 8÷1
  
2)    ለዳንኤልም የተሰጠ ሥም ነዉ፡፡ ዳንኤል 1÷7 በሥም እኩል በግብር ሥንኩል ማለት እንዲህ ነዉ፡፡

ዳንኤል ማን ነዉ?
የስሙ ትርጓሜ ፡- ̎ እግዚአብሔር ፈራጅ ነዉ̎ ማለት ሲሆን
ትዉልዱ፡- መጻሕፍት እንደሚሉት የተወለደዉ በ618 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ትዉልዱም ከይሁዳ ነገድ  ስለሆነ ከንጉሳዊ/ከመሳፍንት ቤተሰብ እንደሆነ ይገመታል፤ የዮናኪር የልጅ ልጅ ነዉና፡፡ ምነዉ ቢሉ ዮናኪር የንጉሡ የኢዮአቄም (የእስራኤል ንጉሥ) ልጅ ስለሆነ፡፡ የኢዮአቄም ዘመነ ንግሥናዉም ከ609 እስከ 598 ከክርስቶስ ልደት በፊት ማለት ሲሆን የነገሠዉም በ18 አመቱ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አንዳንዶችም በ25 አመቱ እንደነገሠ ይናገራሉ፡፡ ዳንኤል ግን መሾሙን መጽሐፍ ይናገራል፡፡  ዳንኤል 1÷6

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...