ሕዝብ
፡ በቋንቋ:በሃይማኖት፡በሕገ መንግሥት፡በታሪክ፡በልማድ፡በኑሮ አንድነት ኅብረት ያንድ መንግሥት አጽቅነት ማለት ነዉ፡፡ከሣቴ ብርሃን
ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት እንደሚለዉ፤
የኢትዮጵያ
ህዝብ የራሱ የሆነ ቋንቋ ፣ሃይማኖት፣ሕገ መንግሥት ፣ታሪክ ፣ልማድ፣ኑሮ፣ባህል፣ያለዉ ቢሆንም ለረጅም አሥርት ዓመታት እየተፈራረቁ
ሲገዙት ወይም ሲያስተዳድሩት ከነበሩት መንግሥታት ( ነገሥታት ) ክፋት እና በጎ አሳቢነት ከማጣት ፣ከልማት ይልቅ “ ረሃብ ” ሲጫወትበት ኖሯል፡፡ ከዚህም ባሻገር አገሪቱ በዉስጥም
ሆነ በዉጭ ጠላቶቿ ሠላም በማጣት ልጁን ለጦርነት እየማገደ ፣ ራሱም በረሃብና በበሽታ አለንጋ እየነደደ 21ኛዉ መቶ ክ⁄ዘመን ላይ
ደርሷል፡፡ይሁን እንጂ ኑሮዉ ያልተሻሻለ ፣ ስላሙ ያልተረጋጋለት የህብረተሰብ ክፍል በሃገሪቱ ላይ በብዛት ይገኛል፡፡ እንኳን የገጠሩ
የከተማዉ ነዋሪ የተሻለ ኑሮ ይኖራል፣ የተሟላ ነገር አለዉ፣ ለዕድገት እና ለለዉጥ ቅርብ ነዉ፣ … ወዘተ የተባለዉ ህይወቱ የሃዘን
እንጉርጉሮ የበዛበት ነዉ፡፡ መፈጠሩን እስኪጠላ ይማረራል፡፡እንደ ትናንቱ ለመሬት ከበርቴዉ እና ለወኪሉ የጉልበት አገልግሎት አይስጥ
እንጂ ዛሬም ህብረተሰቡን ሙስና አቅሙን አሳጥቶታል፡፡ አጥር ማጠር፣ቤት ማደስ፣የወር ተራ ገብቶ በዘበኝነት ማገልገሉ፣ በእርሻ መሳተፉ
ቢቀርለትም በየቢሮዉ ጉዳዩን ለማስፈፀም ደፋ ቀና ማለት፣ነገ ተመለስ፣ ጉዳዩን የሚያከናዉንልህ አለቃ ስብሰባ ላይ ነዉ፣ ማኅተም
የምታደርገዋ ፀሐፊ ዛሬ ስራ አልገባችም፣ እገሌ የሚባሉት ሰዉ ዛሬ ⁄ ሰሞኑን የሉም፣ … ወዘተ የሚሉ ምክንያቶች ደሃዉን ሆነ ሃብታሙን
የህብረተሰብ ክፍል ቀና ብሎ እንዳይሄድ አድርገዉታል፤ ከትላንት የተሻለ ቀንም እንዳይወጣለት አድርገዉታል፡፡ከዚህም ባሻገር በየተቋማቱ
ያሉ ( የተንሰራፉ ) ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ በፖለቲካ የልዩነት ፍጭት፣ ትልቅ የራስ ምታት እና ሰፊዉ ህብረተሰብ አገልግሎት ለማግኘት
ሁለተኛ እዚህ ስፍራ ብደርስ ብሎ እንዲማረር አድርጎታል፡፡ ( ዝሆኖች ሲራገጡ ሳሩ ይጎዳልና ህብረተሰቡ ትልቅ በደል እና ጉዳት
ደርሶበታል ) ከትናንት በስትያ ፣ ትናንት እና ዛሬም ድረስ የዘለቀዉ ዘመን ተሻጋሪ ነቀርሳ ኢትዮጵያ ሰፊ መሬት ያጣች ይመስል
በልማት ሰበብ የህዝቡ ለዓመታት ይኖርበት ከነበረ ፣ ተወልዶ ካደገበት ማፈናቀልና በየሄደበት ቦታ ከነባር ነዋሪዉ ጋር ግጭት መፍጠር፣
አልነሳም ትነሳለህ በሚል ክርክር ከገዢዉ ጋር እሰጣገባ ዉስጥ መግባት፣ ሃብት ንብረቱን ብቻ ሳይሆን ድበደባ ፣ እስር ፣ እንግልት፣
ጤናዉን ማጣት፣ሰደት፣ አልፎ ተርፎም ሞት ይደርስበት ነበር፡፡
በቀደሙት
ስርዓት አርሶ አደሩ ካረሰዉ እና ከሚያረባዉ ለከበርቴዎች እንደሚገብረዉ ሁሉ ዛሬም ህብረተሰቡ ትናንት በወጣዉ የግብር ተመን መሠረት
( ህብረተሰቡን ለሞት ለእስር ለእንግልት ) የዳረገዉን የተለያየ ቁጣ ያስነሳዉን የግብር ተመን አሁንም ያለምንም ማሻሻያ ገበሬዉም ነጋዴዉም የመንግሥት ሠራተኛዉም የቀን ሠራተኛዉም ሁሉም እኩል እንደ ገቢዉ መጠን እስከ 35% ድረስ
ይገብራል ( ይበዘበዛል)፡፡