ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክፍሎች “ ጠላትን
” ስለመዉደድ ጥቂት ነገር ብለናል በዛሬዉ ፅሁፋችን ደግሞ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የመጨረሻዉን ክፍል እንመለከታለን፤ እግዚአብሔር
“ጠላቶቻችን” እንድንወድ ያስችለን፡፡
ጠላቴን ለመዉደድ የሚያስችለኝ ነገር ምን ላድርግ?
(ምን መደረግ አለበት?)
ጠላትህን ለመዉደድ እነዚህን ነገሮች ሳታወላዉል አድርግ!
ምናልባት
እነዚህን የተዘረዘሩትን ነገሮች በሙሉ በአንዴ ለማድረግ ይከብዱ ይሆናል፤ ይከብዳሉም፡፡ ነገር ግን የሚከብደዉን ሁሉ እንተወዋለን
፣ እንሸሸዋለን ማለት አይደለም፡፡ ማንኛዉም የዓለማችን ነገሮች የመለማመድ ዉጤት ናቸዉና ዘወትር በድርጊታችን ዉስጥ እንለማመዳቸዉ፡፡
በእርግጠኝነት ለዉጥ እናመጣባቸዋለን … ለዚያዉም በጣም የሚያስደንቅ … ነገር ግን ብዙ መንገድ ያስጉዙናል፡፡ቢሆንም ግን ጥቂቶች
ለእኔ እስከ አሁን ጠቅመዉኛል በእርግጠኝነት አንተንም ይጠቅማሉና ሞክራቸዉ፤ ከታች በዝርዝር የተቀመጡትን ፈፅማቸዉ፡፡
i.
ጠላቴ ስለምትለዉ ሰዉ ከዚህ ቀደም የሚሰማህን ነገር ማሰብ
አቁም፡ በፊት ስለሚሰማህ ስሜት ደጋግመህ አስብ ( አስር ጊዜ
)፤ አሁን ደግሞ የሚሰማህን አስብ እዉነት ያንን ነገር ማቆምህን ራስህን ገምግመዉ እርግጥ ነዉ በአንዴ ሃሳብህን መቆጣጠር ሊከብድህ
ይችላል ነገር ግን ደጋግመህ አድርገዉ ( እርሳዉ )
ii.
ራስህን በእርሱ ቦታ አድርገህ አስብ፡ ያኔ በዉስጥህ የሚመጣዉን ጥላቻ ታስወግደዋለህ፤ እርሱ ያደረገዉን ድርጊት አንተም እርሱ
ቦታ ብትሆን ታደርገዋለህና፡፡በቃ አሁን ያ ሰዉ ማለት አንተ ነህ፡፡ ያ ሰዉ እንደ አንተ ትክክለኛ ሰዉ የነበረ ነዉ ያ አጋጣሚ
በርሱ ላይ ይህን ክፉ ድርጊት አመጣበት እንጂ፤ ስለዚህ ይህን ሰዉ ከመጥላት ያንን ክፉ ድርጊት ጥላ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የለጠልህ
ጥሩ ሰዉ ሁን፡፡ የሰዉ ልጅ በጠቅላላ ጥሩ ነገር ለማድረግ ይጥራል ነገር ግን ስህተት ይሰራል፡፡ ስህተት እና ጥፋት ይለያያል፡፡
እንኳን ለተሳሳተ ላጠፋም ይቅርታ ማድረግ ግድ ይለናል፡፡ አለበለዚያ በድርጊቶች ላይ የተለያየ አመለካከት አለዉ፡፡ አንድን ነገር
ከተለያየ ቦታ ላይ መመልከት እጅግ ይከብዳል ግን እጅግ ይጠቅማል “ 6 ” ይህን ቁጥር አንተ ስትፅፈዉ ስድስት ስትለዉ ከፊት ለፊትህ
ለተቀመጠዉ ደግሞ “ 9 ” ሆኖ ስለሚታየዉ ዘጠኝ ሊለዉ ይችላል፡፡ ችግሩ ከቁጥሩ ወይንም ከሰዉየዉ ሳይሆን ሰዉየዉ ከተቀመጠበት ቦታ ነዉ፤ ስለዚህ አንድን
ነገር ከመወሰናችን በፊት ራሳችንን ከሰዉየዉ ቦታ አድርገን ብንመለከተዉ መልካም ነዉ፡፡
iii.
ልትረዳዉ ሞክር፡ በርሱ ቦታ ራስህን የማስቀመጥ ዋና ዓላማዉ ይህ ነዉ፤ እርሱ ያደረገዉን ነገር ለምን እንዳደረገዉ
ከተረዳኸዉ ቀጣዩ ድርጊትህ መረዳት ይሆናል፡፡ እዉነት እልሃለዉ ጠላቴ የምትለዉን ሰዉ ከምንም በፊት ችግሩን ልትረዳዉ ሞክር እዉነቱን
ታገኛለህ፤ ምናልባት ይህ ሃሳብ ላይዋጥልህ ይችላል ነገር ግን አድርገዉ፡፡