ጊዜ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ይታሰባል ይከወናል ትናንት ዛሬን እየሆነ ይቆጠራል፤ ትናንትናና ዛሬ ተደማምሮ ሳምንት ሳምንታትና ቀናት ተደማምረው ወራትና ዓመታትን /ሦስት መቶ ስልሳ አምስት ቀናትን/ ይሰጣሉ፡፡ ከአዳም ጀምሮ ዓመት ይቆጠራል፡፡ የዓመታት ጥርቅም ዘመን ተብሎ ይጠራል ዘመን ረጅም ጊዜ ነው ወይም አንድ አይነት አገዛዝ አምልኮ ሌላም የተደረገበት ጊዜ መጠሪያ ነው፡፡
ዘመን የተፈጠርንበት /የተወለድንበት/፣ ትምህርት የጀመርንበት፣ ሥራ የያዝንበት፣ መከራን ያየንበት፣ ከውድቀታችን የተነሳንበት፣ የተማመንበት፣ የተፈወስንበት … ወቅት ማስታወሻ /መጠሪያ/ ሊሆን ይችላል፡፡
ወደ ፍሬ ነገሩ ልምጣና ከብዙ ሰዎች አንደበት ስሰማና ከብዕራቸው የዕምባ ጠብቃ ሳነብ ብዙዎች ዘመንና ጊዜን ሲደግፉ በከንቱ ስሙን ሲያጠፉ ሲኮንኑ አዳምጣለሁ አነባለሁ ‹‹አይ ዘመን፣ አይ ጊዜ››፣ ‹‹ጊዜው ነው፣ ዘመኑ ነው›› ሲሉ ነገር ግን ጊዜና ዘመን ምን አደረገ ምንስ በደለ ጊዜና ዘመን በራሱ ምን ያመጣው ለውጥ ምንስ ያደረሰው ተፅዕኖ አለ? አንዳንድ ፀሐፍት እንደሚሉት ዘመንና አህያ አንድ ነው ይላሉ አህያ እንዳሸከሟትና የጫኑባትን ይዛ እንደምትገኝ ዘመንም