ዓርብ 7 ሴፕቴምበር 2012

‹‹ጌታ አግኝቶሃል?››

-->
-->
ሁለት ሰዎች በካፍቴሪያ ተቀምጠዋል በዚህ መሆን የዕለት ተዕለት ሥራቸው ነው ጨዋታቸውን ድምፃቸውን ከፍ እያደረጉም መጫወትም ልዩ ምልክታቸው ነው፤ ቶሎ ገብቶ የመውጣት ልምድ የላቸውም ብዙ ሰው ይተዋወቃሉ ይግባባሉ ለጨዋታቸውም ይጋብዛሉ፡፡ ምናልባት አብረው ሻይ ቡና ብለው ከሆነ በይሉኝታ ሂሳብ ከፋይ እርስዎ ይሆናሉ ፀባያቸውን ካላወቁ፡፡
ከዕለታት በአንደኛው ቀን እንደልማዳቸው ተቀምጠ ትኩስነገር እየተጎነጩ ሳለ አንድ ለግላጋ ወጣት እነርሱ ከተቀመጡበት ፈንጠር ብሎ ይቀመጣል እርሱም ቡና ያዛል፤ ስልክ ይደወልለታል ተንቀሳቃሽ የመነጋገሪያ ሥልኩን አውጥቶ "ሃሎ" ይላል ደዋይም ያወራዋል ሰላምታ ይለዋወጣሉ ወጣቱም "እግዚአብሔር ይመሰገን ደህና ነኝ" በማለት ስለጤናውም ስለ ሥራም ሌላም ሌላም ያወሩና ሥልኩ ይዘጋል፡፡
ከሁለቱ የካፍቴሪያ ተስተናጋጆች ይገረማል! ይገርማል! ይባባላሉ፡፡ ወዳጄ ይህ ቃል ከጆሮው ጥልቅ ትላ  ለወጣት ይልቁንም ብቻውን ለተቀመጠ አጨዋች ለሌለው የሚገርም ነገር ሲገኝ እጅጉን ይገርማል ሳንቲም ቅጭልታ እና የሚገርም ነገር ጀሮውን የማይገዛው የለምና፡፡
እነዚህ ሁለት አጥማጆች የጣሉት መረብ ሠው ያዘላቸው ለዚያውም ወጣት እግዚአብሔር የሚያመሰግን፤ ትህትና የተላበሰ፤ ብቻውን የተቀመጠ፤ ….. ሰላምታ ተለዋውጡ እርሱም እንደልማዱ እግዚአብሄርን ይመስገን ብሏቸው ሳያስበው ከብቸኝነት ወደ ሶስተኛ ሰው ተቀላቀላቸው “ደስ ይላል …. በዚህን ሰዓት ከጐረምሳ አንደበት እግዚአብሔር ሲመሰገን” ወዘተ ይሉትና ያሞጋግሱታል ያቺን በስልክ ሲነጋገር “እግዚአብሔር ይመስገን” ብሎ የተናገራትና ካአፉ ነጥቀው በማውራት (ለነገር መነሻ ወይም መግቢያ) ሲያደርጓት፡፡
እነርሱ በዚች ትንሸ ቀዳዳ ገብትው ያጣደፉት ገቡ በመሃልም እነዚህ ወጣቶች ይሰብኩት ጀመር ከሚያነሷቸውም ቃላቶች መካከል “ጌታ አግኝቶሃል?” የሚለው አንድና ዓብይ አጀንዳቸው ነበር፤ይኸው ለግላጋ ወጣት እግዚአብሔርን አመስጋኝ “የጌታ ልጆች” መሆናቸው ይገባዋል፡፡ አልተጣላቸውም አልተቃወማቸውም….በጸጥታ ያዳምጣቸዋል አንዳችም  ቃላት ከአንደበቱ አይወጣም እነርሱ ግን እየተቀባበሉ ቃላት ይወረውራሉ ተናግረው ተናግረው ሲጨርሱ ልጁ ምንም አይልም ቢሉት አሁንም አንዳች ቃላት አይናገረም ተደናገጡ እርስ በርስ ተያዩ እርሱንም አዩት ዝም ሏል አንዳችም ክፉ ነገር ከአፉ አይወጣውም የተለየ ነገር አጋጠማቸው በዚህ ቤት እንዲህ ዓይነት ባነሱ ቁጥር የሚያጋጥማቸው ዓይነት  ባህርይ ዓይደለምና የርሱ ፀባይ ሌላው ተሰማምቷቸው ጌታ ይባርካችሁ ብሎ የሚወጣ ወይም በጌታ የሚባርክ ሲሆን ሌላኛው ወገን ደግሞ  ተሳድቦ “ጌታ ይገሰፅህ” ብሎ የሚወጣ በዛዋል፡፡ ይህ ወጣት ግን እግዚአብሔርን ከማመስገን በቀር አንዳች ነገር አላገኙበትም ጌታ እንዲባርከው ወይም ጌታ እንዲገስፀው፡፡
በዋዛ ሊለቁት አልፈልጉምና “ምን ትላለህ” አሉት
“ምኑን?”
“ስለጌታ፤”
“ስለጌታ ምን?”
ድፍን ቅል ሆነባቸው ቢሉት ቢሰሩት ቢከረኩሩት አንዳች ነገር አልገናገር አላቸው፡፡
“ወንድሞቼ ሥለምን እንደምታወሩኝ:ምንስ እንደምትፍልጉ አልገባኝም ምንስ ፤ማንንስ ትፈልጋላቸሁ?በዚህ የተቀመጣችሁት እኔን ፍለጋ ነውን?” ይላቸዋል፡፡
“ወንድማችን የምናወራህ ስለ ጌታ ነው ሥለ ኢየሱስ ጌታ መሆን”
“አዎ ኢየሱስ ጌታ መሆን”
“በጌታ በኢየሱስ እመን ጌታ ያድንሃልና”
“አዎ ያድናል አምናለሁ!”
ጨዋታቸው እንዲህና እንዲህ እየደራ ድምፃቸው ከፍ እያለ ተመልካችን ቀልብ እየገዛ ከሶስት ወደ አራትነት እየጨመረ ንግግሩ እየከረረ በካፍቴሪያነት ወደ ኤማሁስ መንገድነት ተቀየረ ሥብከቱ ዳራ መረብ ተዘረጋ አንም ዓሣ ግን ወደ መረቡ አልገባም መረባቸው ወደ ባህር ግን ከመወርወር ግን አልቦዘኑም፡፡ ለዘብ እያሉ ድምፃቸው እየወረደ ሥሜታቸው እየበረደ መጣ “ለማንኛውም ጌታ ይወድሃል….”፤ “ጌታ ይባርክህ”፤ “መዳን በጌታ ብቻ ነው፤ “በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ”……ወዘተ የሚጠቀሟቸው ጥይቶች ነበሩ፡፡
ይኽ ደካማ የመሰለ ሰው፤የማይናገር ሰው መናገር ጀመረ “ሞኝ ካመረረ...” እንደሚባለው ማለት ነው በጥያቄ በቃላት ያጣድፋቸው ጀመር፡፡
“ወንድቼ ጌታ አገኝቶሀል ነው ያላችሁኝ?”
“አዎ!”
“እናንተንስ አግኝቷችኋል?”
“እኘ የጌታ ነን …….” በልበ ሙሉነት
“ለነገሩ የጌታ ልጅ መሆናችሁን አለባበሳችሁ፣ ደፋርነታች፣ወዛችሁ ……. ይናገራል” ከነረሱ ግን በተራቸው የሚመልስ ጠፋ ዝምታ ነገሰ እርሱ ከመናገር ሌሎች ተመልካቾች በተመስጦ ከማዳመጥ እነዚያም ሁለት ባልንጀሮች ግራ በመጋባትና እጃቸውን በአፋቸው ላይ በመጫን ከማዳመጥ አልቦዘኑም፡፡
“አንድ ነገር ልጠይቃችሁ እስኪ ዕድሜዬ ሥንት የሚሆን መስላችኋል?”
እነርሱም የሚመስላቸውን ገምተው ነገሩት “ጥሩ የሚገርማችሁ ይኸን ዘመን ሙሉ ጌታን አውቀዋለሁ፤ አይደለም ጌታን እናንተንም አውቃችኋለው በሥራችሁ በቃላቶቻችሁ …… የጌታ ልጅ መሆናችሁን በሥራችሁ ግን አይደለም….. ለመሆኑ ከእኔ ምን ትፈልጋላችሁ?....በዚህ የሆናችሁት ከጌታ ልታገናኙኝ ነው?...ወንድሞቼ እኔ ሥራ አለኝ ጌታ ደግሞ ሥራ ያለውን አይፈልግም ሥራ ላይ ያሉትን አይደለም የሚጠራው ሥራ የፈቱትን ነው…..ቅዱስ ጴጥሮስን በጠራው ጊዜ ያገኘው ዓሣ ማጥመዱን ትቶ ሥራ ፈትቶ በተቀመጠ ሰዓት ነው እኔ እድሜ ዘመኔን የጌታ ነበርኩ አሁንም ነኝ ወደፊትም ከርሱ የሚለየኝ የለም እናንት ግን ስራ ፈታችሁ በመርቢቷ ላይ ቁጭ ብላችኋልና ኑ ለጌታ ታስፈልጉታለችሁ ኢየሱስ ጌታ ነው ጌታም ብቻ አይደለም የጌቶች ጌታ፡ የዓለም መድኃኒት: የአብ የባህርይ ልጅ:ወልደ አብ ወልደ ማርያም: የሰውን ልጅ ለማዳን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ወዲዚህ ምድር የመጣ ደግሞ ለፍርድ ወደዚህ ዓለም በግርማ ሞገስ በክ ትስብዕት የሚመጣ አምላክምነው: ጌታ ብቻ አይደለም ሰው አይደለም ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ እንጂ: ሠይጣን አዳምን ለማሳት የእባብን ሥጋ እንደለበሰ ኢየሱስ ክስቶስም አዳምን ለማዳን የሠውን ልጅ ሥጋ የለበሰ…..” 
በዚያ ሥፍራ ዝምታ ነገሰ አግራሞት ጨመረ::
“ወንድሞቼ ከእኔ የምትፈልጉት አለን?” በዚህ ሆናችሁ እኔን ነው ወይንስ ጌታ ትፈልጉታላችሁ? …. አንድ ነገር ልንገራችሁ በዚህ ቁጭ ብላችሁ ጊዜአችሁን በዋዛ በፈዛዛ ሥታባክኑ አባቶቻችሁ ሲያርግ ያዩት ጌታ በዚህ እንዳተቀመጣች ለፍርድ መጣልና ንቁ ንስሐም ግቡ ልባችሁን መልሱ መንገዳችሁንም አቅኑ...” ብሏቸው የቡናውን ሂሳብ ከፍሎ ወደየት እንዳገባ ሳይታወቅ ከፈታቸው ተሰወረ፡፡
ይህን ታሪክ በኢየሩሳሌም ጉዳና ላይ ሐዘን በነገሰበት ሰዓት ስለተሰቀለውና ሥለምተው ኢየሱስ ክርስቶስ ልባቸው ተነክቶ እየተጫወቱ ሲጓዙ እንደ ነበሩትና በመንፈስም ራሱ በመሃላቸው ተገኝቶ እየተጫወቱ ሲጓዙ እንደነበሩትና በመንፈስም ራሱ በመሃላቸው ተገኝቶ ሲያጫውታቸው ሲያፅናናቸው ሲያበረታታቸው እንደነበረው የኤማሁስ መንገዶኞች ታሪክ ይመስላል ሉቃስና ቀላዮጳ ምንም እንኳን ልባቸው ተነክቶ እያዘኑ እየተከዙ በመንገዳቸው ቢያወሩት ያ የተሰቀለው ማን እንደሆነ ገና አላወቁም በመሃላቸው ተገኝቶም ያወረቸው አልተረዱትም የአገሬ ሰው 'ለቀባሪው አረዱት' እንደሚባለው ከራከሩት ነበር እንጂ:: እነዚህም ወንድሞቼ ምንም እንኳን ደጋግመው በመንገዳቸው በህይወታቸው በመቀመጫቸው በመድረካቸው…….ወዘተ ቢያወሩት ቢጫወቱት ገና ጌታ ምን እንደሆነ አላወቁትም ጌታ ነው ሲሉ ጥቂቱን አብዝቶ ሲመግብ ተመልከተው ባዕለ ጸጋ ነው ብለው፤ ተዓምራቱን (ለምፃምን ሲያነፃ ጎባጣ ሲያቀና ሽባ ሲተረትር፤ አጋንንት ሲያወጣ) ተመልከተው ለማድነቅ ነው:ግን ይኸን ሁሉ መንገድ ይኸን ሁሉ ዘመን ሲከተሉ ከባለፀግነቱ (ጌታነቱ)፤ ከተዓምር ሰሪነቱ በስተቀር አምላክ መሆኑን አላመኑም አላወቁም ለዚህ ነው “አማላጅ” ብለው የሚሟገቱት ሎቱ ሰብሐት፡፡
አንባቢ ሆይ! መቸስ በመንገድህ በመቀመጫህ፤ በህይወትህ…….ወዘተ እንደዚህ አውቅልሃለሁ ባይ: እኔ የምልህን ብቻ ሥማ እኔ የምሰጥህን ብቻ ተቀበል የሚልህ ብዙ ነው ሠላምህን ነስቶ ሰላሙን ካልተቀበልከኝ ብሎ የሚያስገድድህ በግህን ውሻ ነው ብሎ ሊያስጥልህ የሚያባብልህ: ... ብዙ ነውና ተጠንቀቅ፡፡ ሲጠይቁህ ለመመለስ የተዘጋጀህ ሁን በከንቱ የምትበሳጭ ለመስማት ብቻ የማትፈልግና በደህና የምሮጥ አትሁን እወቅ ጠይቅ ስለምታምነው ነገር ጠንቀቅህ እወቅ ሰዎች ሲናገሩ ግራ እየገባህ ራስህን የምትወዘወዝ ብቻ አትሁን የምትወዘውዘው ራስህ ይታዘብሃልና፡፡
እንግዲህ ወገኔ በየመንገዱ በየመስሪያ ቤቱ በየሻይ ቤቱ እንዲህ የተቀመጡ “ወንድሞች” አይታጡምና እንጠንቀቅ የሚገርመው ይህ ሰው ሌላ ቀንም ብቻውን ቡና ለመጠጣት ወደዚህ ቤት ሲመጣ ሶስት ሆነው ተቀምጠው አገኛቸው እነርሱም ተመልክተውት ለሶስተኛው ጓደኛቸው አወሩለት ዝ ባለ ድምፅ የማያያቸው የማይሰማቸው መስሏቸው እርሱ ግን ቡናውን ጠጥቶ ሂሳቡን ከፍሎ ወጥቶ ሄደ፡፡
ሲወጣ ግን አንድ ነገር አላቸው “በዕድሜ ዘመኔ ይኸንን ጆርዬን ተሸክሜው ሲሄድ ጆሮዬ ይሰማል የእናንተም አንደበት ይናገራል” ብሏቸው ወጥቶ ሄደ፡፡
ምን ማለት ነው ተርጉምልን እንዳይሉ እርሱ በዚያ የለም፤ ወንደሞቼ ዛሬም የሚናገረውን የሚሰማውንም ተሸክመውት የሚናገሩበትን ብቻ እንጂ መስሚያቸውን የይጠቀሙበት በርከት  ብለዋልና እኛም ከነርሱ ወገን እንዳንሆን ለመናገር የዘገየን ለመስማት ግን የፈጠንን እንሁን፡፡
ጊዜ ጊዜን እየተካ ዘመኑ ይፈጥናል ይኸው ወጣት እንደተለመደው ወዲዚህ ቤት ይመጣል ቡና ሊጠጣ ሂሳቡን ከፍሎ ሊወጣ እነዚያም ጓደኛሞች ከሶስት አራት ሆነው እዛ አገኛቸው፡፡ እነርሱም መግባቱን ተመለከቱ ሶስተኛው ሰው ወደብቸው ወጣት በማምራት እንደተለመደው ወደ ወንበሩ እያለከተ “ሠው አለው?” ይለዋል ይኽም ወጣት በፈገግታ እየቀለደ “ለእኔ የሚታየኝ የለም” ይለዋል
“ምናልባት የተያዘ ከሆነ ብዬ ነው”
“የአራት ኪሎ ወንበር ሳይሆን የካፍቴሪያ ወንበር ስለሆነ ተቀመጥ” ይለውና ይቀመጣል ሠላምታም ይለዋወጣሉ እንግዳው ሰው “ጨዋታውን” (ሥብከቱን) ይጀምራል፡፡ ወደጓደኞቹ በጣቱ እያመለከተ “ባለፈውኮ ጓደኞቼ ሥለአንተ አውርተውለኝ በጣም ገርሞኝ …..” እያለ ሲቀጥል “እናንተ ሠዎች ለምን አተውኝም እኔ ጌታን አውቀዋለሁ አምነወለሁ…እኔ የማምን ከሆነ ኢየሱስ ጌታ ነው፤ ኢየሱስ ያድናል፣….. ወዘተ ሥትሉኝ አንዳች ነገር ካልተቃወምኳችሁ ሥለምን ትፈራረቁብኛላቸሁ ልታሳምኑኝ ነው ወይስ ልታስቱኝ እኔ ክርስቲያን (ኦርቶዶክስ ) ነኝ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳምን ከሆነ ጥረታችሁ እኔ የጌታን አዳኝነት የኢየሱስን ጌትነት አምናለሁና ኢየሱስ ጌታ ነው ሥትሏቸው አይደለም ነቢይ ነው የሚላችሁ በዚያ በዚህ ቤት በአፍአ (በውጭ) አሉላችሁ ወደነርሱ ሂዱ ቢያምኑላችሁ ዋጋ ታገኛላችሁና” ብሎ የቡናውን ሂሳብ ከፍሎ ወጣ::
አዎ! ለምንድን ይሆን እነዚህ ወንድሞች ያመነውን የሚያሳድዱ? ለማሳመን ወይስ ለማስካድ? እነርሱስ እርስ በርስ በተገናኙ ቁጥር ሥለሰው አውርተው ከሚገረሙ ይልቅ ስለጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት አውርተው የማይደነቁትና የማይደመሙት? መቼስ ይህን እዚህ ወንድሞች ሥራ ፈተው ከተቀመጡበት መርከብ ላይ መጥቶ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ የሚያገኛቸውና ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የራሱ የሚያደርጋቸው? 
የእናንተን አላውቅም ይኼ የእኔ ጥያቄ ነው፡፡
 አንባቢ ሆይ! እስኪ ህይወታችን ወደኃላ ወደ ትናንት እንመለስ በትናንትናው ዕድሜያችን በትናንትናው ህይወታችን በትናንትናው ማንነታችን ምን አደረግን? ምን አሳለፍን? ዛሬስ ምን እያደረግንበት ነው? ነገስ ምን ልናደርግ ተዘጋጅተናል?(ሁለት ሶስት አራት…… ሆነን በተቀመጥን ጊዜ ሰዓቱን ምን ተጠቀምንበት? ምን አወራንበት?) ዕውቀታችንንስ ዕምነታችንንስ ራሳችንን ምን ተጠቀምንበት? ለሰው ሥናወራ ራሳችንን ምን አልነው? ሰዎች እንዲያምኑ “የጌታ” እንዲሆኑ ከአልባሌ ቦታ ርቀው የጌታ እግር ሥር በጌታ ቤት እንዲገኙ ቃሉን እንዲሰሙ በጌታ እንዲያምኑ ግድ ንላቸው እኛ የት ቆመን ነው ? ካፍቴሪያ? መንገድ ላይ? …..ግን ለምን? እኛ እርስ በርስ ሥለ ሠው እያወራን እየሳቅን እና እያፌዝን ሌላው በተመሥጦና ልብ ተነክቶ ሥለ ጌታው እንዲያወራ መጋበዝ ማነሳሳት ክፋት ባይኖረው አግባብ ነው? "ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ መልካም ነው" የተባለው ወሬ ለማውራት ቢቀመጡ መልካም ነው:የተባለው ወሬ ለማውራት አይደለም፤ ሌላው ፍጹም አማኝ እንዲሆን እና እኛ ግን "የእምነት መልክ" ያለን ነገር ግን የማናምን በማሳመን ሥራ የተጠመድን መሆን የለብንም ማመናችን በወሬ በአውቅልሃለሁ ሳይሆን በሥራ ቢገለጥ መልካም ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ባለአመኑት መካከል እየተመላለ በሚያስተምርበት ሰዓት ያላመኑትን ሰዎች ልብስ እያለበሱ ለጣኦት የተሰዋውን እየተመገቡ እነርሱን እየመሰለ ሲኖር ምንም እንኳን የነርሱን ልብስ ቢለብስ ምግባቸውን ቢበላ ባልንጆሮቹም ወደ ጥንት ምግባሩ ተመለሰ ብለው ቢለምኑት እርሱ ግን በወንጌል የልጅነት ልብስ የክብር ልብን ኢየሱስ ክርስቶስን አለበሳቸው ለጣኦት የተሰዋውን እየበላ ሥጋውን እያረከሰ ነፍስንም ስጋንም የሚቀድሰውን የእግዚአብሔርን ቃል መግቦ የእግዚአብሔር አደረጋቸው፡፡ በጨለማ ውስጥ እየተመላለሰ አበራላቸው የእነዚህ ወንድሞቼ አካሄድ ወዴት ይሆን እንደሻማ እየቀለጡ ለሰው ብርሃን መሆን ወይንስ የሻማን ብርሃን እየጋረዱ ማጨለም? የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” እንዳለው በህይወታቸው ያብራላቸው የሚያወሩት ብቻ ሳይሆን የሚኖሩት ይሁንላቸው፡፡ አውቅልሃሁ ከማለት ለራሳቸው የሚያውቁ ያድረጋቸው ያብራላቸው የሚያወሩት ብቻ ሳይሆን የሚኖሩት ይሁንላቸው፡፡ አውቅልሃለሁ ከማለት ለራሳችን የሚያውቁ ያድርጋቸው ተናጋሪ እንደበት ብቻ ሳይሆን አድማጭ ጆሮንም ይስጥልኝ ሥራ ፈተው ከተቀመጡበት መጥቶ ከሚፈርድባቸው ሥራ ፈተው ከተቀመጡበት መጥቶ ጌታ ያግኛቸው የራሱ ያድርጋቸው ለንሰሐ ያብቃቸው፡፡ እኛንም በቤቱ ፀንተን ከማታልፈው መንግሥቱ ያስገባን ፡፡ ባለፈው ይቅር ብሎ በሚመጣው ጠበቆ ቀሪውን ለዘመናችን የወሬ ሳይሆን የስራ የኃጢያት ሳይሆን የንሰሐ ዘመን ያድርግልን፡፡ የአባቶቻችን በረከታቸው ድል የማትነሳ ጥርጥር የሌለባት ተዋህዶ እምነታቸው በኛ ትደርብን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የቅዱሳን መላዕክት የቅዱሳን አባቶች ተራድኢነት አይለየን አሜን ይቆየን፡፡

መታሰቢያቱ ለጓደኛዬ ለአዳነ ይሁንልኝ
  God bless Ethiopia!

“አንተም እንደዚሁ አድርግ”

በአዲስ አበባ ከተማ ሲኖሩ ከመጠለያ ችግር አስከትሎ የትራንስፖት ችግር ደረጃውን በመቀጠል ይይዛል፡፡ የመኖሪያ ችግር ዛሬዛሬ መንግሥት እየሰራ ካለው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባሻገር የተለያዬ ሪል እስቴቶች ችግሩን ለመቅረፍ ትልቅ ሚና እየተጫወቱ ቢገኙም በመዲናይቱ የተለያዬ አቅጣጫ የሚገኙ አከራይና ተከራይን በማገናኘት የሚተዳደሩ “ደላላዎች” የመኖሪያ ችግሩን እያጦዙት ይገኛ፡፡ ይኽንንም ችግር ከዕለት ወደ ዕለት እያባባሱት የሚገኙት ርህራሄ በጎደለውና ሰብአዊነት በራቀው ተግባራቸው ተከራይን በየጊዜው ከተከራየበት ቤት ለአከራይ ሻል ያለ ክፍያ ነገር ግን የተቸገረ ተከራይ ሻል ያለ ክፍያ እንዲከፈል በማድረግና አከራይን በጥቅም በማማለል ችግረኛውን ተከራይ ገንዘቡን ከፍሎ እስከ ቤተሰቦቹ እንዲጉላላና እንዲሰቃይ ያደረጉታል እቃውን ተሸክሞ ላይ ታች ሲል ዘመኑን ይፈጃል መላው ቤተሰብ እግዚአብሔርንና መንግሥትን ሲያማርሩና ሲወቅሱ ይኖራሉ፡፡ ይሁን እንጂ እ/ርም መንግሥትም ዝም ያሉ ይመስላ ነገር ግን ሁለቱም ያልታየንን ብዙ ነገር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ መንግሥት ካለበት የዜጎች ኃላፊነት አንፃር አስፈላጊውን የአከራይና የተከራይ፤ የአከራየነ የደላ፤ የደላላ እና የተከራይ….. ግንኙነትን በተመለከተ ህግ ሊያበጅ ቁጥጥሩንም ቢያጠናክር የተሻለ  ነው እላለሁ ምክንያቱም በመንግሥት ሥራ ላይ ተቀጥረው የሚገኙት ተከራይተው ነዋሪዎች በየጊዜው ቤት በለቀቁ ቁጥር ለሚከራይ ቤት ፍለጋ የሚያባክኑት ጊዜ ዞሮ ዞሮ ከመንግሥት የሥራ ሰዓት ላይ ነውና፡፡ አንድም ችግሩን ሽሽት ራቅ ብለው ሲከራዩም ከዚህ ተነስተው ወደ ሥራ ገበታቸው በሚጓዙበት የዕለት ዕለት የሥራ ሠዓታቸው አርፍደው የሚገቡት ሲሰላ የባክነውና የሚሰረቀው ጊዜ የመንግሥት የሥራ ሰዓት ነውና፡፡ በሌላ ጎኑ ከተመለከትነውም በአከራይ በተከረይና በደላላዎች መካከል እየተፈጸመ ያው መጨካከን መቸስ አገር ሰላም ለሕብረተሱም ፍቅርና አያዳብርም ፍፃሜውም ሠላምና ፍቅር አይጠፋ በሄደ ቁጥር ለመንግስት ትልቅ የራስ ምታትና የቤት ስራ ይሆንበታል ስለዚህ መንግሥት የመጠለያን ችግርና የዳላሎችን ከመጠን ያፈ ሥገብግብነት አጥብቆ ሊከታተለውና መጠን ሰፊ  ስራን ሊሰራበት ግድ ይለላ፡፡ ከዕለት ወደ ዕለት የተከራይ መጠን እየጨመረ እየሄደ ነውና መጨካከኑም የዚያኑ ያህል ጨምሯልና፡፡
ከመጠለያ ባሻገር የትራንስፖት ችግር ዓብይ ጉዳይ ነው ይህ ደግሞ  ተከራይንም የቤት ባለቤቶችንም ደላላውንም ሥራ ያለውንም የሌለውንም ተማሪውንም የቤት እመቤቶችንም ሁሉ ያካተተ የማኀበረሰብ የዕለት ተዕለት ሳይሆን በየደቂቃዎቹ የሚፈጠር ችግር ነው መንግሥት ችግሩን በደንብ ተመልክቶት የባቡር ትራንስፖርትን እንደ መፍትሔ አስቀምጦ እየሰራ ቢሆንም እስከ አሁን በተደረጉ በግሉ ዘርፍም ይሁን በመንግስት በኩል እተደረጉ ያሉት ጥረቶች አመርቂ ውጤት ሊያመጡ አልቻሉም፡፡ የከተማ አውቶብስ (አንበሳ).፤ ሚኒባሶች፤ ሀይገር (ሚዲባስ)፤ ባጃጆች፤ ጋሪዎች ፤ የተለያዩ  የሠራተኛ ሰርቪሶች…… ወዘተ ብዙ ጥረዋል ደክመው ከመሸነፍ በስተቀር ችግሩን ሊቀረፉት አልቻም፡፡ ከእጥረቱምባሻገር ከጥቂት ጊዜወዲሀ እንደ መፍትሄ የቀረበው የስምሪት ስራ ችግሩን አባብሶታል የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡
ከምንም በላይ ጠዋትና ማታ በሥራ መገቢያና መውጫ ሠዓት ችግሩ በጣም ጎልቶ ይታያል ወቅቶች ሲቀያየር ደግሞ ችግሩን የባሰ ጎልቶ እንዲወጣ ያድገዋል በተለይ ክረምት ሲመጣ፡፡ በመጠለያም ሆነ በትራንሰፖት ችግር ተጠቂዎች ውስጥ አንዱ እኔ ነኝ፤ የተለያዩ ችግሮች ሲገጥሙኝ የተለያዩ ገጠመኞችም እንዲሁ አስተናግዳሁና ከዕለታት በአንደኛው ቀን ያጋጠመኝን የትራንስፖት ላይ ገጠመኝ እነሆ!
ከስራ ወጥቼ ወደቤቴ በመሄድ ላይ ነኝ አንደኛውን ትራንስፖት ተጠቅሜ የሚቀጠለውን በመጠባበቅ እገኛለሁ ወቅቱ ክርምት ስነበር ሰዓቱ ገና ቢሆንም ጨላሟል በዚህ ላይ ከባድ ዝናብ እየመጣ ስለሆነ ጨለማውን እጥፍ ድርብ አድርጎታል፡፡ ለዓይን የሚታይ የትርንስፖርት መገልገያ አንድም መኪና አልነበረም የትራንፖርት ፈላጊና ጠበቂ ቁጥ ግን በየደቂያቆቹ ልዩነት ይጨምራል፡፡ ለትራንስፖርቱ መጥፋት ምክንያት ይሆናል የሚለውን ግምት ከተሳፋሪዎች ብዙ ብዙ ነገር ይሰማል ነዳጅ ሊጨምር ስለሆነ ነው የጠፉት፣ ታፔላ ስለሚቀይሩ ነው ጾም ስለሆነ ነው…..ወዘተ  ጊዜውም እየገፋ ነው ሰውም ከመጠን በላይ ጨምሯል ድንግት “ልዬ” የሚል የከተማ አውቶብስ ከየት መጣ ሣንል ከፊታችን ተገተረ ያለወትሮው የታክሲዎች መጫኛና ማውረጃ ቦታ ላይ መጥቶ ሲያቆም ለሁለታችንም መገረምን ፈጥሮብና፡፡ ይህ ጉዳይ የኛ ስላልነበረ ሁላችንም ወደ ትኬት ቆራጩ እጃችንን ዘረጋን ሁለት ብሮችን ከኪሳቸን እየመዘዝን አንዳንድ ብራችንን እና ትኬታችንን ይዘን ወደ ውስጥ አመራን አንድ ብር ነበርና፤ ያለማጋነን ያ የከተማ አውቶብስ ከመቶ በላይ ሠዎችን በውስጡ ይዟል ያለውን መጨናነቅ የሠውን በሠው ላይ መረማመድና መገፋፋት መግለፅ ይከብዳል፡፡ ደቂቃዎች እየጨመሩ በሄዱ ቁጥር ትንፋሸ እያጠርዎት ይሄዳል፡፡ ገና መኪናው ጭኖ ሳይጨርሽ ትንፋሽ አጠረኝ መቆም አቃተኝ መውደቅ አማረኝ አስጠግቶ የሚያስቀምጠኝ ሰው በዓይኔ አማተርኩ ማን ሠው ና! ቁጭ በል ይበለኝ መባልም ካለበት ከኔ በዕድሜ የሚልጡ አባቶችም እናቶችም ብዙ ናቸው ሆኖም ግን የኔ ድካምና መዛል አቅም አሳጣኝ ጥርሴን ነክሼ ሃሳቤን ወደሌላ ቦታ ወስጄ ቆሚያሁ የሆነ እጅ  ሲናካኝ ታወቀኝ ዐይኔን ወደ ነካኝ እጅ ወርወር አደረኩ አንዲት ወጣት ልጃገረድ እየተጠጋች  እንድቀመጥ ጋበዘችኝ ብቻዋን ተቀመጠችበት የአንድ ሰው መቀመጫ ወንበር ላይ አልተግደረደርኩም ለማንም ዕድሉን አልሰጠሁም ፈጥኜ ተቀመጥኩ ከዚያ በኋላ ያለውን ልንገራችሁ አልችለም በጣም ደስ አለኝ ፊቴ ላይ ያለውን የደስታ ፀዳ በቃላት መግለጽ ከምቸለው በላይ ነው፡፡
መልስ ብዬ ታክሲ ከምንጠብቅበት ሥፍራ ህሊናዬን ላኩት እስከ አሁን እዚያው ብቆምስ አልኩኝ አሁን ከተቀመጥኩ በኋላ ያለውን ቀሪ ድካሜን እያስብኩ፡፡ የኔን ድካምና የሌሎችንም ድካም አሰብኩ ዘወር ብላ ተመለከተችኝ የምንተ ፍረቴን “አመስግናሁ” አልኳት፡፡
“ለምኑ ነው ምስጋናው ?”
“ሥላስቀመጥሽኝ!
በኋላኮ ለቅቄው እወርዳለሁ!?
ቢሆንም ይህንንስ ማንስ አስቦ ያደርገዋል
“ደስ አለህ ማለት ነው ያደረኩልህ ነገር”
አዎ! በጣም …. አልኳት፡፡
“ደስታውን እስኪ አጣጥመው” አለችኝ ግራ ቢገባኝም ወደ ማጣጣም ሄድኩኝ ድካሜንና ደስታዬን ተመላለስኩበት ይበልጥ ከድካሜ መበርታቴን ፤መቀመጫ ማግኘቴን፤ ቀንንቷን፤ ጥሩ አሳቢነቷንን ባደረገቸውመልካም ነገር አለመመፀደቋን፤ ….. ሁሉ አሰብኩ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ሆነ መልካምነትን አስተማረችኝ፡፡
“አጣጣምከው?”
አዎ!
“በጣም ደስ ብሎሀል?”
አዎ!
“ደስታ ምን ያህል ደስ እንደሚል አየኸው?”
አዎ!
“ሠው ማስደሰትስ ምን ያህል ደስ እንደሚል ታውቃለህ?”
በጭራሽ አስቤው የማላውቀው ነገር ለነበር ግራ ገባኝና ማሰብ ጀመርኩ የማውቀውን ነገር መመለስናመዋሸት አልፈልኩም ዝም አልኳት
“አትጨነቅ እኔ እነግርሃለሁ በጣም ደስ ይላል ከሠው ከምታገኘው ደስታ የበለጠ ደስታን ታገኝበታለህ እኔ ባደረኩልህ ጥቂት ደስታ ከልብህ ተደስተህ ከሆነ አንተም እንደዚሁ አድርግ ያኔ እውነተኛውን ደስታ ትደሰታለህ”
አንተም እንደዚሁ አድርግ አንተም ….ደጋግሜ ለራሴ ነገርኩ የበለጠ ማብራሪያ የህይወት ተሞክሮ ፈለኩኝ ምን ላድረግ?
“አየህ የማያውቁትን መጠየቅ፤ ምን ማድረግ እንዳለብን ማወቅ ብልህነት ነው፡፡ ከምናውቀው ጥቂት እውቀት የማናውቀው ብዙ ነገር ነው ህይወታችንን የሚጐዳንን መምህራችን መድኃኒዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ሲመላለስ የአገሩ ሠዎች ሥለራሱ ማወቅ መሥማት አይፈልጉም ነበር የእጅን በረከት ማየት የቃሉን ትምህርተ መሥማት አይፈልጉም ነበር፡፡ እናውቀዋለን የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ እይደል እናቱሰ ማርያም አየምተባለዋ አይደለች ይሉ ነበር…. እናውቀዋን ይላሉ አንጂ አያውቁትም ቢያውቁትማ ኖሮ አዳኝነቱን አውቀው ይከተሉት ነበር፣ እውነተኛ መምህርነቱን አውቀው የቃሉን ትምህርት ተከትለውት ይማሩ ነበር፣ አድርጎ የተባሉትንም ያድርጉ ነበር፤ …… እንኳንስ ቀርበው ያልተማሩ ሲማሩ የነበሩት የእጁን በረከት የተቋደሱት እንደ ይሁዳ ያሉት ገና አላወቁትምና ሸጡት፣ አሳልፈው ሰጡት የዘለዓለም ህይወትን በሞት ለወጡት፡፡ እርሱ ግን በመጨረሻው ሳምንት የእውቀትን መጨረሻ  ሲያስተምራቸው እግራቸውን አጥቦ ሲያበቃ……” እናንተም እርስ በርስ እንዲህ አድርጉ” ብሎ አስተማራቸው እውቀት የሚለካው በተግባር ነውና እኔም እንደዚሁ አንድታደርግ ነገረኩህ፡፡ እኔ ያደርኩልህን መልካም ነገር፤ ሠዎች ያድጉልህን መልካም ነገር፤ አምላክህ ያስተማረህን (ያደረገልህን) መልካም ነገር ያለ አንዳች ዋጋ እንዲሁ ያለዋጋ (ውለታ) አድርገው ያኔ እውነተኛውን ደስታ በነፍስም በሥጋም ትደሰታለህና፡፡”
በሥሜት ይሁን እውቀቱ ከልቤ ዘልቶ ገብቶ ይሁን እንጃ ትንሽ ፌርማታ ቢቀርም ከፊት ለፊቴ ቆመው የነበሩትን የዕድሜ ባለፀጋ እናት እንዲቀመጡ ተነሳሁላቸው እያመሰገኑኝ እየመረቁኝ ተቀመጡ መምህሬም ተነሰችላው የበለጠ እንዲመቻቸው አሁንም ወደጆሮዬ ቀርብ ብላ “እውነታኛውን ደስታ የበለጠ አሁን ታገኘዋለህና አጣጥመህ ልዩነቱን ንገረኝ፡፡” ደግሜ ደጋግሜ አጣጥምኩት ልዩነቱን ተመለከተኩት ልዩነቱ የሰማይ እና የምድር ያህል ነበር፡፡ “እንዴት ነው?” አለች መልስ አልነበረኝም መግለጫ ቃላት አጣሁ ምን እንደምላት ግራ እየተጋባሁ እያለሁ “አየኸው አይደል ልዩነቱን ጣዕሙን ለየኸው አይደል? ከኔ ያገኘኸውን ደስታ በቃላት ገልፀኸዋል ከራስህ ያገኘኸውን ደስታ ግን የሥራህ ውጤት ሥለሆነ መግለጽ ከበደህ?”
“በጣም ትልቅ ትምህርት ነው ያስተማርሽኝ በጣም ነው የማመሰግነው”
“መማር  ከፈለክ የሁላችን መምህር እግዚአብሔር በህይወት ዘመንህ በሙሉ ያስተምርሃልና እንደ ሣሙኤል “ባሪያህ ይስማልና ተናገር” በለው ይነግርሃል”
የፌርማታው መጨረሻ ላይ ደርሰን ሥለነበርን ወረደች እኔም ወረድኩ ሠላምታ ተለዋውጠን ተለያየን ከዓይኔ እይታ ርቃ እስከምትሰውር ድረስ ቆሜ በአይኔ ሸኘኋት ገና ወጣት ነች ግን በሳልና አስተዋይ ዕድሜዋን ለቁም ነገር የተጠቀመችበት አንድ ነገር አስታወስኩ “Be a man of your age” የእድሜህ ሰው ሁን! የዕድሜ ሠው መሆን እንደዚሁ ነው ምን ዋጋ አለው የእድሜን ዘውድ በእናታቸው ላይ ደፍተው የማያስተውሉ የጉብዝና ዘመን ጠንካራ ጉልበት ይዘው የሚዝሉ በሞሉባት ዓለም እንዲህ ዕድሜን መጠቀም ሲቻል ደስ ይላል፡፡

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...