ማክሰኞ 28 ኦገስት 2012

ፍቅር በFace book ክፍል አንድ


ፍቅር በFace book

     ወላፈኑ ይጋረፋል የጸሐዩ ብርሃን ለዓይን ያጥበረብራል፡፡ ጥናንሾቹ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫዎች ባጃጆች ላይ ታች ይላሉ፡፡ ከትናንሽ ዓይኖቼ ሥር ጥቂት እንፋሎቾች ይመነጫሉ ትንፋሼ ይፋጃል ወዴት መሄድ እንዳለብኝ አላውቅም የት እንደማርፍም የማውቀው ነገር የለም የመጣሁበት ሚኒባስ የጫነው ለማራገፍ አሁን ዕቃ ሥላለ ነው እንጂ የምታርፍበትን ቦታ አስመርጥህና አስይዘህ ከተማውንም አስጎብኝህ ነበር›› ብሎኝ ለማንኛውም ወፊት አስጠጋህና እንደታጠፍኩ ትወርዳለህ አለኝ›› የሾፌሩን ድምጽ ስሰማ ይባስ ፍርሃት በውስጤ ነገሰ የመኖሬ የመጨረሻ ድምጽ መሰለኝ፡፡
      ወደ ከተማው ለመግባት ሥንታጠፍ ከዚህ በኋላ አስራ ስምንት ኪሎ ሜትር ብቻ እንደቀረን ሲነግረኝ ተጉዤ ከመጣሁት ሶስትና አራት መቶ ኪሎ ሜትር በላይ ራቀብኝ፡፡ እህ›› አልኩት በመዳናገጥ ‹‹18 ኪሎ ሜትር አለኝ፡፡ ቁጥቁጦ የበቀለባት ምድር የመኪናው ጎዳና እንደ ዕባብ በዚህች ምድር ላይ በደረቱ ተጠማዞ የተኛባት ይመስላል፡፡
      የመኪናው አሽከርካሪ የህይወት ታሪኩን ያወጋኛል መጋላ ተወልዶ ያደገ ነምበርዋን ተከራይቶ የሚኖር ቀን ከሌሊት በሥራ ተጠምዶ ያደገ ተወልዶ በአደገባት ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ የሚያፈቅራትን ጓደኛውን አግብቶ ሁለት ልጅ ወልዷል፤ ‹‹ስምንት ነን ሰባቱ የሉም እኔ ብቻ ነኝ አገሬ ላይ ተጣብቄ የምኖረው ሌሎች አዲስ አበባ አራቱ በተለያየ የአውሮፓ አገሮች ይገኛሉ፤….››
      ጊዜው እኩለ ቀን ስለ ነበር ሙቀቱ ጨምሯል ወላፈኑ አይሏል የፀሐይ ብርሃን ሳይሆን እሳት ያህላል መንገዱ ሲታይ ነፍስ የተለየው ዘንዶ ይመስላል፡፡ አስራ ስምንቱን ኪሎ ሜትር ቀስ በቀስ እያጋመስን ወደ ከተማው እየተጠጋን መሆኑን የሚያመለክት ከመንገድ በስተ ግራ እየተገነባ ያለው የሲሚንቶ ፋብሪካ አመላከተን ናሽናል ሲሚንቶ በሃገራችን ላይ እዚህ ግንባታ ለመገንባት አሸዋ የሚያሳስብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ምድሩ በጠቅላላ አሸዋማ ነውና፡፡
      በግራር ዛፎች መካከል ቤቶች ተመለከትኩ ወደ ከተማው መግባታችንን መጠየቅ አልነበረብኝም አመላካች ነገር እያየሁ ስለነበረ ‹‹ይሄ የምታየው ህንፃ የጁቡቲው ፕሬዘዳንት ናቸው ያስገነቡት የሥልጣን ዘመናቸው ሲጠናቀቅ በዚህ ለመኖር….›› Delight Hotel ይባላል፤ የሆነ ነገር በውስጤ አቃጨለ የሥልጣን ዘመናቸው ፍፃሜ እንዳለው ለቀሪዎቹም የአፍሪካ መሪዎች ሥልጣን ዕድሜ እንዲኖረው ‹‹በነገራችን ላይ እኚህ ሰው ተወልደው ያደጉት እዚህ ነው ይባላል፤….›› ድንገት ያገኙት የመኪና አሽከርካሪ ሳይሆን የግል አስጎብኚዬ መስሎ ተሰማኝ ‹‹ እንደታጠፍን አውርድኃለሁ›› ያለኝ ነገር ትዝ እንዳለኝ መሪውን ወደ ቀኝ በመጠምዘዝ ታጥፎ ፍሬኑን ያዘና በእጁ እያመለከተኝ ‹‹ቀጥ ብልህ በዚህ በኩል ሂድ ከፈለክ ባጃጅ መያዝ ትችላለህ ቅርብ ስለሆነ ግን በእግርህ ውረድ ነዳጅ ማደያ ታገኛለህ እሱጋ አደባባይ አለ ከእሱ አጠገብ ደግሞ ራስ ሆቴል ታገኛለህ እዚያ ደግሞ መኝታ ከሞላብህ እዚያው አካባቢ ቆንጆ ቆንጆ ሆቴሎች አሉ….. በል ደህና ሁን ጥሩ የመዝናናት ጊዜ እንዲሆንልህ እመኛለሁ›› ከትራንስፖርት የወረድኩ ሳይሆን በአሥራ ስምንት ዓመቴ ከቤተሰብ ተነጥዬ ከቤት የወጣሁ ያህል ተሰማኝ አንገቴን እንደደፋሁ ሻንጣዬን እየጎተትኩ መንገድ እያቋረጥኩ እያለሁ  ‹‹ማን ነበር ሥምህ?›› የሚል ድምጽ ከኋላዬ ስሠማ ዘወር አልኩ ያ አሽከርካሪ ከቦታው አልተንቀሳቀሰም ሥሜቴን ተረድቶታል መሰል መነፅሩን አውልቆ ልብን እንደሚመራመር መሳሪያ ተመለከተኝ ‹ሳሚ አልኩት ቀና ብዬ ዓይኖቹን ማየት እየከበደኝ በርሬ ደረቱ ላይ ልጥፍ ብዬ ሥቅስቅ ብዬ በለቅሶ አንገቱን አቅፌ ሥሜ ብሰናበተው ደስ የሚለኝ መስሎ ተሰማኝ ግን ትናንት የማላውቀውን ዛሬ መንገድ ላይ ያወቁትን? ብዬ ይሉኝታ ተሰማኝ ቀና ብዬ ተመለከትኩት ‹‹ቴዲ እባላለሁ እዚህ ባለህበት ሰዓት ሁሉ ችግር ሲኖር ደውልልኝ ስልኬን ያዘው›› በማለት የተንቀሳቃሽ ስልኩን ቁጥር ሠጠኝ መዘገብኩት ‹‹ደውልልኝና እይዘዋለሁ በድጋሚ መልካም ጊዜ ብሎኝ ሞተሩን አስነስቶ ተፈተለከ መኪናው ከእይታዬ እስኪሰወር ተከተልኩት እርሱ ወደሚያውቀው እኔ ወደማላውቅ ሰፈር ….ወደ ራሴ ተመለስኩ እጄን ወደ ኪሴ በመስደድ ተንቀሳቃሽ ስልኬን አወጣሁ Address book ከፈትኩ የቤትና የሞባይ ስልኳን E-mail አድራሻዋን የምትሰራበትን ድርጅት የልደት ቀኗን …. በድጋሜ ተመለከትኩት የማጥናት ያህል የልብ ምቴ ለጆሮዬ እስኪሰማ ድረስ ይመታል ፍርሃት ሥጋዬን ጨምድዶ ያዘኝ ነፍሴን ፍቅር ያስጨንቃታል….. ድው ድው ድው ትር ትር ትር….. ይላል ደረቴ ስር ጥገኝነት ጠይቃ የምትኖረዋ ልቤ፡፡ 
      Face book Account መቼ እንደከፈትኩ ማሰላሰል ጀምርኩ እ.ኤ.አ 2010 ወርሐ መጋቢት አሁንም ብዙ ጓደኞች ባይኖሩኝም ያኔ እጅግ በጣም ጥቂቶች ነበሩና ጓደኛዬ አድርጌአታለሁ፡፡ አገሯ ፍቅር፣ ትውልዷ ፍቅር፣ እርሷም ፍቅር………በማለት አስቤ የ  Face book ጓደኛ ሆንን፡፡ chat እናደርጋለን ፣ ቢሮ በE-mail ብዙ ነገር እናወራለን፣…. እንዲህ እና እንዲህ እያልን ጥቂት ጊዜያትን አስቆጠርን ትውውቃችን ከፌስ ቡክ ጓደኝነት መጠነኛ ለውጥ አሳየ ምሥጢር ማውራት ልብ ለልብ ማውራት፣ በነገሮች መመሳሰል፣ ፍላጎቶቻችን አንድ መሆን ጀመረ፣ በፌስ ቡክ የመጀመርነውን ወሬ እጅግ ስላሰፋነው መፈላለጋችን መነፋፈቃችን እየጨመረ ሲመጣ ተንቀሳቃሽ ስልክ መለዋወጥ ግድ ሆነብን አልቀረም ተቀያየርን በቀን አንዴም ሁለቴም እንገናኛለን እናወራለን ጤናዋን እጠይቃታለሁ ሥለቤተሰቧ ሥለ ቤተሰቤ አወራታለሁ ታወራኛለች ቀናት እየገፉ ፍላጎታችን እየጨመረ መጣ ሳስባት የሚሰማኝ ሥሜት እየተቀየረ መጣ ዝብ ብላ ትናፍቀኝ Face book በከፈትኩ ቁጥር እርሷን on line ባገኛት ደስ ይለኝ ጀመር እርሷ የሆነውን ነገር ባትነግረኝም እንደማትናፍቀኝ ሳገኛት ደስ እንደሚለኝ እነግራታለሁ አትንገረኝ እንጂ እርሷ ውስጥም ተመሳሳይ ስሜት እንዳለ ሁኔታዋ ይናገራል እንኳንስ ሳልደውል መዋል እና ማደር ሳረፍድ እንኳን ‹‹ምን ሆነህ ነው? እየተጨነኩ ስጠብቅክ ነበር…… ትለኛለች በሥራ ምክንያት ቸኩዬ ቶሎ ልዘጋው ከሆነ ቅር ይላታል ‹‹ትንሽ አውራኝ….›› የሚሉትን ቃላት የምትጠቀማቸው ነበሩ ፍቅር ፍቅር የሚሸቱ ቃላቶቹ ለፌስቡክ ጓደኛዬ በቀን የአምስት፣ የአስርም፣ የሃያ አምስት ብር የሞባይል ካርድ መጠቀም ወቅታዊ ግዴታዬ ነበር፡፡ ለኢንተርኔት ቤት በገባሁ ቁጥር እንደዚያው ቀን ከሌሊት ቁርኝታችን እየጠበቀ መጣ ከእንቅልፍ ስነቃ ወይም እንቅልፍ እምቢ ሲለኝ ሞባይሌን አብርቼ በኢነተርኔት እናወራለን አለበለዚያ የፅሑፍ መልዕክት እንላላካለን….. የመዋደዳችንን ያህል አልፎ አልፎ ደግሞ እንጋጫለን ግን አንኳረፍም የሚገርመው ነገር የጓደኝነት ዕድሜያችን ሶስት ወር አይሞላም አዲስ አበባ እንደምትመጣ እና ከእኔ ጋር መገናኘት እንደምትፈልግ ነገረችኝ እርሷን የማግኘት ጉጉቴ እየጨመረ መጣon line ሆነ በስልክ እያወራኋት በአካል ትናፍቀኝ ጀመረች ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር ሁለት ደቂቃ ማውራት የማልችለው ሰውዬ ከእርሷ ጋር ሲሆን ስሜቶቼ በጠቅላላ ጨዋታ ያመነጩ ይሆን እንጃንጂ በጣም እናወራለን ፡፡ ‹‹ምንድን ነበር የምታወሩት?›› ብትሉኝ እኔ አይደለሁም እርሷም የምታውቀው አይመስለኝም ግን በጣም ደስ ይለኝ ነበር፡፡
      ድንገት በአጋጣሚ ወደ መተሐራ የምትሄድበት ጉዳይ ተከስቶ መተሐራ ለውስን ቀናት መጣች ናፍቆታችን ኪ.ሜትሩ እየቀረበ ሲመጣ የናፍቆት መጠናችን ጨመረ መጓጓታችን እየጦዘ ሂዴ መሽቶ ሲነጋ እንነፋፈቃለን እንዳንገናኝ የሚያደርጉትን ነገሮች ከፊታች ማስወገድ እንዳለብኝ ታወቀኝ ‹‹እንገናኝ አልኳት ሳትጠብቀው ‹‹መቼ? የት? በማለት በጥያቄ ክው አደረገችኝ የተቃውሞ ድምጽ ሳተሰማ ‹‹ነገ አዳማ›› ላይ አልኳት መቼ እንደመሸ መቼ እንደነጋ የማይታወቀው ቀን ሊመሽና ሊነጋ አልቻለም በጣም ረዘመብኝ ተኝቼ ስነቃ ሰዓቴን ብመለከት ረዥሙ ሰዓት 15 ደቂቃ ነበር ተኝቼ በድጋሜ የምነቃው ሰፈሬ መሳለሚያ ወደ አማኑኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ነበር ከቤተሰቦቼ ጋር ነው የምኖረው ያለምክንያት ከቤት ወጥቼ አድሬ ከከተማ ራቅ ብዬ አላውቅም ከንጋቱ አስራ አንድ ሰዓት ላይ እቤት አልነበርኩም የአዳማ ትራንስፖርት መያዣ ለገሃር መናኸሪያ እያመራሁ ነው ጠዋት 1፡15 አዳማ ከተማ ውስጥ ነበርኩ 15 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አጠገቤ አገኘኋት በአካል የማይተዋወቅ አንመስልም ነበር ትቅፍቅፍ ተደራርገን ተሳስምን እንደገና ታቃቅፈን እንደገና ተሳስመን ስሙን ለጊዜው ወደ ዘነጋሁት ካፍቴሪያ ገብተን እንደነገሩ ቁርስ ተመገብን ናፍቆት እየተናነቀን የምነበላውን መዋጥ ይደሳነን ነበር ቀስ በቀስ ተደብቀን ስንተያይ ዓይን ለዓይን እንጋጫለን እንደገና ዓይናችንን ሰበር እናደርጋለን አሁንም ደግሞ ሰረቅ አድርገን እንተያያለን፡፡
      ወደየት መሔድ እንደነበረብን አልተነጋገርንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ወደ ሆቴሉ አመራን ጊዜያዊ የማረፊያ መኝታ ክፍል ተከራየን፤ በአዳማ ሙቀት ላይ ተደማምረን አንዳችን በአንዳችን ውስጥ በፍቅር ወላፈን እየቀለጥን አንዳችን ከአንዳችን አፍ ውስጥ መንጠባጠብ እንዳችን በአንዳችን ውስጥ እንደቸኮሌት መሟሟት፣ መጣፈጥ፣ ተግባራችን ሆነ፡፡
እኔም በፍጽም የማውቃት ነው የሚመስለው ጊዜው እየተሻማን ፍቅር እያደወርን የፍቅር ሻማ እየሸመንን ልብሳችንን አውልቀን የፍቅርን ሸማ ለበስን እንደሻማ ክር እየነደድን አበራን ቀለጥን የልባችንን ድቅድቅ ጨለማ በፍቅር ብርሃን አደመቅን ናፍቆታችንን ሳናገባድድ ሰዓቱ እየነጎደ የልባችን ርካታ ሳይሞላ የምንለያይበት ሰዓት በፍጥነት እየገሰገሰ ከፊት ለፊታቸን ድቅን አለ፡፡ መለያየት ግድ እየሆነ መጣ እኔ ወደ አዲስ አበባ እርሷም ወደ መተሃራ መተማመናችን ጨምሮ የፍቅር ጡዘት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ለፍትወተ ሥጋ አለመሸነፋችን እያስገረመን ዳግመን ዳጋግመን እየተሳሳምን እተሳሳምን እየተሳሳምን ተለያየን፡፡
      ከአዳማ ሞቃታማ የምድር ክፍል ወደ ተለየችው የኢትዮጵያ መገናኛ ከተማ አዲስ አበባ ጉዞዬን በሚኒባስ በትካዜና በናፍቆት አጅቤ መጓዝ ጀመርኩ ከአገራችን የምሥራቁ ክፍል ረዣዥም ኪሎ ሜትሮችን አቁርጠው ከፍተኛ የቶን መጠን ያዘሉ ትላልቅ ተሸከርካሪዎችን እያለፍን ምድርን ለሁለት እየሰነጠቅን አደጋን እየፈራን በህሊናች ሰውረን እያልን እየፀለይን ጉዞ ወደ አዲስ አበባ፤
      በደቂቃዎች ልዩነት የተንቀሳቃሽ ስልኬ የጥሪ ድምጽ ከሃሳብ ይቀሰቅሰኛል ‹‹የት ደረስክ?›› የሚሉ ድምጾቿን እየሰማሁ ወደኋላ በሃሳብ እየተመላለስኩ ወደ ፊት እየገሰገስኩ በናፍቆት እየተብሰለሰልኩ ሳይነጣጠል መጓዝ ያልለመዳውን የአዲስ አበባን መንገድ የመኪና ጭራ እየተከተልን ጉዞአችንን እያፋጠንን ዱከም ደረስኩ ትራንስፖርት ላይ በድምጽ ብዙ ማውራት ስለማይቻል በጽሁፍ መልክት ሀሳቤን አስጥሬ ‹‹I miss you! አልኳት ‹‹me too, I Love you›› የሚል ምላሽ ወዲያው ነበር የደረሰኝ አስከትለም እንደ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከትራንስፖርት እንደምትወረድን ልትደውልልኝ እንምትችል የፅሁፍ መልዕክት ላከችልኝ፡፡
      ሌት ለንጋት ንጋት ለቀን ቀኑ ለምሽት ጊዜውን እየለቀቅ ናፍቆት ለፍቅር ፍቅር ለደግሞ ትዝታና ትውስት ስፍራውን በመተው መሃል ላይ እኔ እየተጨነኩ አስነባበቴን አዋዋሌን እየከለስኩ በመኪና ግርግር እየተመሰጥኩ አዳማን ተሰናብቼ አቃቂን እያቋረጥኩ ወደ ሸገር የጥሪ መመለሻ ቁልፉን ተጫንኩት የሞባይል ስልኩን መልዕክት ለመስማት ‹‹miss love›› ይላል የሞባይሉ ጥሪ ሥም
‹‹ሃሎ ሃኒ››
‹‹ሃሎ የኔ ቆንጆ!
‹‹የት ደረስክ››
እየገባን ነው አቃቂ ገብተናል
‹‹ እስካሁን ምነው ቆያችሁ አልቃመም እንዴ?
ቢቅም ምን ያመጣል?
‹‹ይዥልጠው ነበራ አይንቀራፈፍም ነበር፤
መጣደፉ ምን ዋጋ አለው ብለሽ ነው ዋናው ነገር በሰላም መግባት ነው አደጋው በከፋበት ሰዓት…››
‹‹እንዳወራህ ነበራ፣ አቦ ምኑ ነው?..››
አውሪኝ ችግር የለውም
‹‹ተመቸህ››
ምኑ?
‹‹ውላችን ነዋ!
ኧ በጣም በጣም ደስ ብሎኛል አንቺስ?
‹‹እኔም …. አንተ ግን ደስ ያህል አይመስለንም፤
እንዴት እንደዛ ለማለት ቻልሽ እኔ በበኩል በጣም ደስ ብሎኛል ቅር ይለኝ መለያየታችን ነው፡፡
‹‹እሱማ ግድ ነው ሌላ ጊዜ አዲስ አበባ ሥመጣ አብረን እናድራለን ግን እንትን ባለማድረጋችን ቅር ብሎሃል አይደል? ለምን መሰለህ መመርመር ስላለብን ብዬ እንጂ ላለማድረግ ብዬ አይደለም በዚያ ላይ እንትን ይዘህ አልመጣህም ታዲያ ምን ላድርግ? አውቄ አይደለም ይቅርታ እሺ በቅርብ ቀን እዚያ ስመጣ ተመርምረን እናደርጋለን እሺ ሃኒ››
እሺ!
‹‹አታወራም እንዴ ምን እሺ እሺ ብቻ ትላለህ?››
ትራንስፖርት ውስጥ ስላለሁ እኮ ነው
‹‹በቃ ደውልልኝ ቻው!››
      ቻው! እሺ
‹‹እወድሃለው!››
እኔም
      ስልኩ ተዘጋ አወራሬ የኔም አስገርሞኛል ያደኩበት ሥነ ሥርዓት ያሳደጉኝ ቤተሰቦቼ ፈጣጣ እንዳልሆን ሰዎች እንደከብር ባህል እንድጠብቅ፣ እንዳፍር፣ ተቆጥቤ እንዳወራ አድርገውኛል ማለት ነው አንድ የሰማሁትን ነገር አስታወሰኝ ‹‹ሰውየው በጠዋት ተነስቶ ልጆቹንና ሚስቱን ስሟቸው ደህና ዋሉ ብሎ ወደ ስራ ይሔዳል ቢሮ እንደደረሰ የሥራ ባልደረቦቹ መስብሰቢያ ክፍል ገብተው የሥብሰባውን መጀመርና እርሱን እየጠበቁት እንደሆነ ፀሐፊው ነገረችው የሥብሰባው መሪ ነበርና የተለመደው ቤተሰቡን ደርሻለሁ የሚለውን ስልኩን መልዕክት ሳያከናውን ወደ ሥብሰባው አዳራሽ ይገባና ታዳሚውን በማርፈድ ይቅርታ ጠይቆ ስብሳባው ይጀመራል ተንቀሳቃሽ ሥልኩ በድንገት ጠራ ሲያነሳው ከቤት ነበር፡፡ ይቅርታ ጠይቆ የማነጋገሪያ ቁልፉን ተጭኖ ያነጋግራል
‹‹ሃሎ ውዴ››
ሃሎ ይቅርታ ሳልደውል ቀረሁ አይደል?
‹‹ሰላም ገባህ?››
አዎ ገብቻለሁ ስብሰባ ላይ ሆኜ ነው እደውላለሁ
‹‹ቻው በቃ እወድሃለሁ!››
      እኛ ጋም እንደዚያው ነው አላት አሉ ያስለመዳት ‹‹እውድሻለሁ›› የሚለውን ቃል በተሰብሰቢው ፊት መድገም አፍሮ እኔንም ይኸው ዞሮ አጋጠመኝ
      ‹‹ ያፈቀረና ያበደ አንድ ነው ›› ይባል የለ ፍቅራችን ገደብ አጣ አውርተን አውርተን አንጠግብም እንዳለችው አዲስ አበባ መጥታ አንድ ወር በተቀመጠችበት ጊዜ ሥራ መሥራት አልቻልኩም መግባት መውጣት ሆነ ሮጥ ብዬ አግኝቻት እመጣለሁ ከተገናኘን መለያየት ጭንቅ ይሆነብናል የቆየንበትን ሰዓት የምናውቀው የምር ሥንሰነባበት ብቻ ነው፡፡ ፍቅር በፌስ ቡክ ጀምረን አንድ ቀን ለሠዓታት በአካል ተገናኝተን ፍቅራችንን በመሳሳም ተቃቅፎ በመተኛት አጠንክረን በናፍቆት ከጦዝን በኋላ የአዲስ አበባ የአንድ ወር ቆይታ በተለያዩ ፔኔስዮኖች የጫጉላ ሽርሽር አድርገን የተሰበረውን ብር አምባር እንክትክቱን አወጣነው፡፡
      ፍቅር በወጣትነት ሲሆን ደስ ይላል ጥንቃቄ ሲሞላበት ደግሞ የበለጠ ያምራል እፍ ያለው የፍቅራችንን እሳት ከጭናችን ሥር ለኩሰን ያቀጣጠልነውን ማብረድ እስኪ ሳነን እጅግ ተቀጣጠለ ከቁጥጥራችን ውጭ በሆነ ስሜት በተገናኘን ቁጥር ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ አንሶላ መጋፈፍ ስራችን ሆነ ስንጨርስ ግን እንመረመራለን መባባሉ ከዛቻ ያለፈ አልነበረም ፤…
      አስቀድማ ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ጓደኛ እንደነበራትና በአንድ ቀን ሥህተት ክብረ ድንግልናዋን እንደገሰሰው ከዚያ በኋላ ግን ከርሱም ጋር ይሁን ከሌላ ሰው የግብረ ስጋ ግንኙነት እንዳልፈጸመች ምርመራም እንዳላካሄደች ያጫወተችን ትዝ ያለኝ የመጀመሪያ ቀን አንሶለ ከተጋፈፍን በኋላ ነበር ውስጤ ጥርጣሬ ስለፈጠረብኝ ‹‹ከሌላ ሰው ጋር አድርጌ አውቃለሁ ብለሽኛል አልነበር›› ብዬ ጠየቋት ደንገጥ ብላ ‹‹አዎ ምነው ታዲያ ምናጠፋሁ? ብላ በሚያሳዝኑ ዓይኖች ቀና ብላ ተመለከተችኝ ‹‹እርግጠኛ ነሽ በትክክል አድርጋችኋል? ብዬ ጥያቄዬን አጠናከርኩባት ‹‹ቅር አለህ? ወይኔ ጉዴ….›› ብላ ተጨነቀች ፍቅሯ ነበር ያስጨነቃት በጣም እንደወደደችኝ ዓይኗ ያሳብቃል የኔ ፍቅር ግን ይበልጣል፡፡ ከአረጋጋኋት በኃላ ለኔ ዛሬም ድንግል ክብረ ንጽህናዋን የጠበቀች ልጃገረድ እንደሆነች ነገርኳት በጣምም እንደምወዳት በቃሌ አረጋግጥኩላት በደሌን የተካስኩብሽ የፍቅር ምትኬ፣ ሃዘኔን ያስወገድሽልኝ ፋሲካዬ ነሽና ልቤ እስኪጠፋ እወድሻለሁ በሴቶች ቂም ይዤ ዳግም ላላፈቅር እርም ብዬ ነበርና በሰጠሽኝ ፍቅር ምህራትን አድርጌአለሁ በማለት ቃል ገባሁላት ቃል ለሰማይ ቃል ለምድር፡፡
      የስም ማውጫ ላይ የመረጥኩትን የሞባይል ቁጥር መደወል ቁልፉን በመጫን ሞባይሉን ጆሮዬ ላይ አስቀመጥኩት ‹‹ይቅርታ የደወሉላቸው ደንበኛ ማግኘት አይችሉም›› አለችኝ፣ ደግሜ ተጫንኩት ‹‹ መስመሮች ሁሉ ተይዘዋል›› አለችኝ፤ትንሽ ቆይቼ ሞከርኩት ‹‹ይቅርታ …›› ብላ ሳትጨርስ ተበሳጭቼ ዘጋሁት፡፡ ከበዙ ድካም በኋላ ግን ተሳክቶልኝ አገኘሁት ጠራልኝ አንስታ አናገረችኝ እመጣለሁ ብዬ ቃል ገብቼ የነበረውን በአካል ከተለያየን ከሶስት ወራት በኋላ ቃሌን ጠብቅ አገሯ ላይ መገኘቴን ነገርኳት ምንም አልመሰላችም፤ የት ማረፍ፣ የት ሆቴል አልጋ መያዝ እንዳለብኝ ጠየኳት ጥያቄዎቼን እንደተራ ነገር ቆጠረችው ደጋግሜ ጠየኳት ‹‹ፀሐይ ሆቴል› እና ‹‹ቱሪስት ሆቴል›› የሚባል ጠቆመችኝ ከዚያስ የት የሚል ባጃጅ ይዤ ልምጣ? አልኳት ‹‹የት?›› በማለት በሚየስደነግጥ ሁኔታ ጠየቀችኝ፡፡ መልስ ነበረኝና ግራ አልገታባሁም ግን ያልጠበኩት ጥያቄ ነበር ‹‹አንቺ ጋር÷እናንተ ሰፈር›› በማለት ግልጽ አደረኩላት በልበሙሉነት አይኗን በጨው አጥባ ምን ልትሰራ? አለችኝ ‹‹ላገኝሽ ልጠይቅሽ ….የአዳማውን እና የአዲስ አበባውን የፍቅር ጊዜ ድሬ ላይ ልንደግም›› መልስ አላገኘሁም ፀጥታ ሰፈነ የፀሐይ ሐሩር አናት አናቴን እርሷን ህሊናዬን ተረባረቡብኝ ሥልኩን ዘጋሁትና ወደተባለው ሆቴል አመራሁ አንደኛው ተይዞ አልቋል አንደኛ አልተመቸኝም ወደ ራስ ሆቴል በማምራት የቀረችውንና እኔን በመጠበቅ ላይ የነበረችዋን አንድ የመኝታ ክፍል ተከራይቼ አረፍ አልኩ የሥጋዬን ድካም ባበረታም የህሊናዬን የዘመናት ድካምና ዝለት ማጠንከር ማበርታት አልቻልኩም ደጋግሜ ብደውልም መልሷ አንድ ነበር አንድ ቀን ግን የት ነሽ ስላት ሰው ታሞ ለመጠየቅ ‹‹ጃጎል ጮራ ሆስፒታል እንደሆነች ስትነግረኝ በር ላይ ነኝ አንዴ ወጥተሽ ሰላም ልበልሽ ብዬ ለመንኳት ወጥታ አምስት ደቂቃ ላልሞላ ጊዜ ‹‹ሰላም›› ብቻ ብላኝ ተመለሰች እኔም ሲባል የሰማሁትን ‹‹ጉም የዘገነ ሴት ልጅን ያመነ ብዬ እዚህ ቆዝሜ ታገነኛለህ በማለት ለሠዓታት ሆቴል ውስጥ የእንግዳ መቀበያ ላይ ሆነን እውነተኛ ታሪኩን አጫውቶኛል፤ እኔም ይህንን እውነተኛ ታሪክ በስነ ጽሁፍ ሥርዓት አንደኛውን ክፍል እንዲህ አቅርቤላችኋለሁ ሁለተኛውን ክፍል ደግሞ ከድሩ አብረን አዲስ አበባ ገብተን እናወጋዋለን፡፡ ቸር ያቆየን በፍቅር ይጥመደን ፍቅር በFace book

   
God bless Ethiopia!

ይቅርታ!

God bless Ethiopia!

እሑድ 15 ጁላይ 2012

ትላንትንፈለኩት


አንዳንዴምናለ? ትላንት ተመልሶ
እንግዳ በሆነ
ህመምቁርጥማቴን መጥቶ በጠየቀኝ፣
                                                        ሆድብሶቴን አይቶ
እንባዬን ባበሰኝ፣
ያጣሁትንተስፋ መልሶ በሰጠኝ፡፡
እነግረው ነበረ ፀፀቴን ቁጭቴን፣
ሥህተቴን ውድቀቴን፣
ያንድቀን መዘዜን፣
በዚያው እንዲተወኝ ፣
                    ለዛሬ አሻግሮ በፀፀትይገድለኝ፡፡
visit us again!

ጦማሩን ስለጎበኙ አመሰግናለሁ!

መልካም ነገርን ለሌሎች ማጋራት ባህላችን እናድርግ፤ ላልደረሰዉ በማጋራት ድርሻችንን እንወጣ፡፡

ትቶ እና ችሎ

  ትቶ እና ችሎ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ በደረሰ ረታ ብጹዕነታቸው ለሶስት አሥርት አመታት እኛ በማናውቀው እግዚአብሔር በሚያውቀው በብዙ መከራ በብዙ ፈተና ውስጥ ነው ያሳለፉት። ...